ማን ደፍሮ ይገባል

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ማን ደፍሮ ይገባል

(25) አለቃ ሚስታቸው የቂጥኝ በሽታ ይዟቸው ወሸባ ገብተው (የቤት ውስጥ ህክምና ) ከቤት ተኝተዋል። በሽታውን ማን እንዳስያዛቸው ሲመረመሩ ማንደፍሮ የሚባል የመንደር አውደልዳይ መሆኑን ሰምተዋል። ታዲያ አንድ ወዳጃቸው የሆነ ሰው «ኧረ ለመሆኑ ከርስዋ ቤት ማን ገብቶ ነው ሚስትዎን ቂጥኝ ያስያዛቸው?» ብሎ ቢጠይቃቸው «አዬ ወንድሜ ያስያዛትንማ ማን ብዬ ልንገርህ ከኔ ቤት ማን ደፍሮ ይገባል?» ብለው መለሱለት ያስያዛት ማንደፍሮ ነው ማለታቸው ነው።