ሜሪ አርምዴ
ሜሪ አርምዴ የኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ስትሆን ባህላዊ ዘፈኖችን በወፈረ ድምጽ በማቅረብ ትታወቃለች። ማርታ አሻጋሪም ከሜሪ አርምዴ ጋር ተመሳሳይ ድምጽ እንዳላት ይነገራል።
ሜሪ አርምዴ
----------------
-
ቤተሰቦቿ ያወጡላት ስም ሜሪማ የሚባል እንደነበር ይነገራል፡፡ ኋላ ላይ ዘመናዊነትን ስትነግሥበትና ፒያሳን ስትደምቅበት በራሷ ጊዜ ስሟን ሜሪ ብላ አስተካከለቸው፡፡
-
ሜሪ የተወለደችው በ1910 ዓ. ም. በአዲስ አበባ ከተማ ዶሮ ማነቂያ ከሚባለው ሰፈር ነው፡፡
-
ቤተሰቦቿ ፈረንሳይኛን የተማሩ ሲሆኑ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ይሰሩ እንደነበር ሜሪ በ1973 ዓ. ም. ለኢትዮጵያ ሬዲዮ በሰጠችው ቃለ መጠይቅ ላይ ተናግራለች፡፡
-
ምክንያቱ ባይታወቅም ሜሪ ገና በልጅነቷ አዲስ አበባን ለቃ ወደ ራያ ኮረም የሚባል ቦታ ሄዳለች፡፡ የልጅነት ጊዜዋንም በዚያው አሳለፈች፡፡
-
ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወር ሜሪ የ13 ዓመት ልጅ ነበረች፡፡ መዝፈን፣ ማንጎራጎርም በዚያ ወቅት ጀምራለች፡፡
-
አምባላጌ ላይ የኢትዮ - ጣሊያን ጦርነት ሲጧጧፍ ሜሪ ብላታ ኅሩይ ከተባሉ አርበኛ ጋር አብራ ዘምታ ነበር፡፡
-
የአምባላጌውን እልህ አስጨራሽ ጦርነትን ጨምሮ ሌሎችም በአርበኞችና ፋሽስት ጣሊያን መካከል የሚደረግን ፍልሚያ በቅርበት አይታለች፡፡
-
በአንድ አውድ ላይም እግሯን ተመትታ የጦርነትን ዋጋ ከፍላለች፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥም ግን በእንጉርጉሮ ፣ በዘፈንና ሽለላዋ የአርበኞቹ የደስታ ምንጭ ነበረች፡፡
1. ዘመናዊ ዳንስ
2. ዘመናዊ የልብስ ስፌት
3. የፀጉር ተኩስ ስራ ሙያዎች
በአዲስ አበባ ሜሪን ቀደምትና ታዋቂ አድርገዋታል ፡፡
-
በዚያ ላይ ታንጎራጉራለች፣ ክራር ትጫወታለች፣ የዳንስ ቤት ከፍታለች፡፡ በወቅቱ ስላልተለመደ ብዙዎች ባይወዱላትም የፀጉር ተኩስ ስራን ለብዙዎች ቀስ በቀስ እንዲወዱትና እንዲለምዱት አድርጋለች፡፡ በዚህም ሜሪ በከተማው ዝናዋ የናኘ ነበር፡፡
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |