ምሳሌዎች
Appearance
- ሆድና ግንባር አይሸሸግም፤ ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው፤ ሕግን መናቅ በሽቦ መታነቅ፤
- ለሂያጅ የለውም ወዳጅ፤ ለሰው ሞት አነሰው፤ ለሰባቂ ጆሮ አትስጠው፤ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ፤ ልጅ ታርጣጣ እህል ከዘበጣ፤
- መልካም ሚስት ለባሏ ዘውድ ናት፤ ምናልባት ቢሰበር አናት፤ ሞኝ የእለቱን ብልህ የአመቱን፤
- ሰው ለአማኙ እግዜር ለለማኙ፤ ሰው ያለአገር መሬት ያለዘር፤ ሰው በወሬ ዱቄት በሙሬ፤ ሰው በአገሩ ዘፈን በትብብሩ፤ ዘመድ ከዘመዱ አህያ ካመዱ፤ ሰው ወጣኝ እግዚአብሔር ፈጻሚ፤ ሰነፍ ሳል ያበዛል፤ ሰርገኞች መጡ ብቅል አስጡ፤ ሰይጣን ለወዳጁ ድርብ ነው አሉ፤ ሰምቶም ዝም አይቶም ዝም ወይ የምድር ሰው በሆድ ያለ አይነቅዝም፤ ሳይፈሩ እውነት ሳይጠራጠሩ ዕምነት፤ ሳይቸግር ጤፍ ብድር፤ ሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ጸሎት፤ ስሙን ለሰው አወረሰው፤ ስንቅና አባይ እያደር ይቀላል፤ስትግደረደሪ ጦም አትደሪ፤ ስንተዋወቅ አንተናነቅ፤ ሥራ ያጣ ገበሬ ይሞታል በሰኔ፤ ሥራ ከመፍታት ልጄን ማፋታት፤ ሥጋ ለጥጋብ አጥንት ለትካዜ፤
- ቀጥኜ ቢያየኝ ጅማት ለመነኝ፤
- ረጅም ባይፈራ አጭር ባይኮራ፤
- በአፍ ይጠፉ በለፈለፉ፤ በወረት ኮሶ ይጣፍጣል፤ በገቡበት አይወጡበት፤ በፊት እውቁኝ - እወቁኝ በኃላ ደብቁኝ፤ በዝና የለም ጤና፤ በዳቦ ላይ ሙልሙል፤ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ፤ በትንሽ ያልታመነ በብዙ አይታመንም፤ ቢሄዱ አገር ቢተኙ ነገር፤ ቢከማች ዕዳው የአንቺ፤ ባለፀጋ በሀብቱ ድሃ በጉልበቱ፤ ባልቤት ካልጮኸ ጎረቤት አይረዳም፤ ባትዋጋ እንኳን ተሰልፍ ፤ ብዙ መላ እምብዛም አይበጅ፤
- ተለማማጭ አልማጭ፤ ተግደርዳሪ ጦም አዳሪ፤ ታሞ የተነሳ እግዜርን ረሳ፤ ታጉል ጥንቆላ የሰው ልጅ መላ፤
- ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ፤ ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም፤ ነገርን አዳምጦ እህልን አላምጦ፤ ነገረኛ ናቸው በጣም ፍሯቸው፤
- አንድነት ያለው ጠላቱን ያሸንፋል፤ አተርፍ ባይ አጉዳይ፤ አምላክ ሲሰጥ ምክንያት ያዛል፤ አበልጅ አትቁም ከደጅ፤ አታላይ ጉድጓድ ዘላይ፤ አላዋቂ ወሬ ጠያቂ፤ አለኩያ ጋብቻ ቆይ ብቻ፤ አባይ ለእለቱ ደስ ያሰኛል፤ አባት ሲታማ ልጅ አይስማ፤ እኛ በሃገራችን ዳቦ ነው ፍሪዳችን፤ እጅግ ሞኝነት ያደርሳል ከሞት፤ እንደገና ይሞታል በገና፤
- ከነገሩ ጦም እደሩ፤ ከሰጪው አሰጪው፤ ከመቸገር ሰርቆ ማደር፤ ከሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል፤ ከተሰቀለ አይወርድ ከተሳለ አይበርድ፤ ከአያያዝ ይቀደዳል ከአነጋገር ይፈረዳል፤ ከስብ ስም ይሸታል፤ ከራስ በላይ ንፋስ፤ ካልዘለሉ አይሰበሩ፤ ካልታረደ ስባቱ ካልተሞከረ ብልሃቱ፤ ክርና ነገር ባጭር፤
- ወዳጅ ሲከዳ ይቀላል እዳ፤ ውሻ ከሸሹለት ልጅ ከሳቁለት፤ ውሻ በበላበት ይጮሃል፤
- ዘንዶ የዳገት በረዶ፤
- የሴት ላብ ወንድ ሊበላ፤ የበላ ቢያብል ገላው ይናገር፤ የበላ ዳኛ የወጋ መጋኛ፤ የቀበጡ ዕለት ሞት አይገኝም፤ የዘነጋ ቤቱን ዘጋ፤ የተከፋ ተደፋ፤ የማታ ማታ እውነት ይረታ፤ የሰውን ነገር አለመናገር፤ የድሃ ጉልበቱ በገበያ ያልቃል፤ የድሃ ብድር አይውል አያድር፤ የቸኮለ አፍሶ ለቀመ፤ የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው፤ የሴት አመዳም የአሮጌ ሆዳም፤ የወፍ ወንዱ የሰው ሆዱ አይታወቅም፤ የቸገረው እርጉዝ ያገባል፤ የሮጠ አመለጠኝ የበላ በለጠኝ፤ የአፍ ብልሃት ጌትነት የእጅ ብልሀት ባርነት፤ የራበው ሰው ይጠግብ አይመስለው፤ የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል፤ ያለአንድ የላት ጥርስ በዘነዘና ትነቀስ፤ ይሆን ቢሆን ዝሆን ይበላ ቢሆን፤
- ደስታ በሽታ፤ ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት፤
- ገባር የአህያ ግንባር፤ ገንዘብ ከጅ ከወጣ ያመጣል ጣጣ፤
- ጠጅ የወረት ወዳጅ የበላ ዕለት፤ ጥሩ ወዳጅ ጠላት ይሆናል፤ ትንሽ ሥጋ እንደመርፌ ትወጋ፤
ከልደት እስከሞት፤ ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን፤ 1964 ዓ.ም. http://www.selamta.net/Amharic%20Literature/Keldet%20Eskemot.pdf