Jump to content

ሞንጎልኛ

ከውክፔዲያ

ሞንጎልኛ (, Монгол) ከሞንጎሊክ ቋንቋ ቤተሠብ ሁሉ የታወቀውና ለአብዛኛው የሞንጎልያ ኗሪዎች ዋና ቋንቋ እንዲሁም የሞንጎልያ መደበኛ ቋንቋ ነው። ደግሞ በአካባቢው ባሉት የሩሲያና የቻይና አውራጃዎች ውስጥ ሲናገር የሩሲያ ክፍላገር ቡርያትያ እና የቻይና ክፍላገር ውስጣዊ ሞንጎልያ መደበኛ ቋንቋ እሱ ነው። በሞንጎልያ ውስጥ ካሉት ተናጋሪዎች ብዙኃን የሓልሓ ቀበሌኛ ይናገራሉ። በቻይናም ዋናው ቀበሌኛ ቻሃር ይባላል።

አንዳንድ ሊቃውንት ሞንጎልኛን ለቱርክ ምናልባትም ለጃፓንኛኮሪይኛም ዝምድና እንዳለው ይቆጠሩታል። እርግጥ የተዛመደ ቋንቋ በሩሲያ የተገኘው ካልሙክኛ ነው። በሞንጎልያ ከ2 ሚሊዮን በላይ ተናጋሪዎች ሲኖሩ በአገሮቹ ሁሉ በጠቅላላ 5.7 ሚልዮን ያሕል ይችሉታል።

"ሞንጎል" በባሕላዊ ፊደል

ባሕላዊ የሆነው የሞንጎል ፊደል በ12ኛ ምዕተ አመት ከሶግዲያን ፊደልኡይጉር ሕዝብ አማካይነት ወጣ። እስከ ዛሬ ድረስ በቻይና ውስጥ ሞንጎልኛ ለመጻፍ የሚጠቀመው ጽሕፈት እሱ ነው። በሞንጎልያ ግን በ1935 ዓ.ም. ይህ ባሕላዊ ጽሕፈት በቂርሎስ አልፋቤት ተተካ። ከዚህ በላይ በቻይና በኦይራት ሕዝብ ዘንድ ቶዶ ጽሕፈት በተሰየመ በሌላ አይነት ባሕላዊ ፊደል ነው ቋንቋቸው የሚጻፈው።

ጠቃሚ ዘይቤና ቃላት በሞንጎልኛ
  • አዎ — ጢም
  • አይደለም — ኡጒ
  • አመሰግናለሁ — ፓያርላ
  • ይቅርታ — ሑን ጓይ
  • ሰላምታ — ሳይን ፓይኑ
  • ደህና ሁን — ፓያርጣይ
  • አልገባኝም — ፒ ኦይልጎሕጒ ፓይን
  • እርስዎ... ይችላሉ? — ጣ...ያይርታጉ?
  • እኔ — ፒ
  • እኛ — ፒት
  • አንተ / አንቺ — ጣ
  • እናንተ — ጣ ናር
  • እሱ / እሷ — ጠር
  • እነሱ — ጠት ናር
  • ስምዎ ማን ነው? — ጣኒ ነር ሔን ፐ?
  • እንደምን ነዎት? — ሳይን ፓይኑ?
  • ጥሩ — ሳይን
  • መጥፎ — ሙ
  • ሚስት — ኤሕነር
  • ባል — ኖሖር
  • ሴት ልጅ — ኦሒን
  • ወንድ ልጅ — ሑ
  • እናት — ኤች
  • አባት — አው
  • ጓደኛ — ናይጽ
  • ሽንትቤት ወዴት አለ? — ኡጋልጊን ኦሮ / ቾርሎንግ ሓን ፓይን ወ?
  • ይህ ስንት ዋጋ ነው? — ኤን ያማር ኡንጠይ ወ?
  • ይህ ምንድነው? — ኤን ዩ ወ?
  • እኔ... መግዛት እወድ ነበር — ፒ...አውማር ፓይን
  • እርስዎ...አለዎት? — ጣናይድ...ፓይኑ?
  • ክፍት — ኦንጎርሖይ
  • ዝግ — ሓልጣይ
  • ተምበር — ማርክ
  • ጥቂት — ጫሓን
  • በካታ — ኢሕ
  • ሁሉ — ፑሕ
  • ቁርስ — ኦግሎኒ ኡንት
  • ምሳ — ኡቲን ሖል
  • እራት — ኦሮይን ሖል
  • ሂሳቡ እባክዎ — ጦጾጎ ፖቱሊ
  • ዳቦ — ጣልሕ
  • መጠት — ኡንታ
  • ቡና — ኮፊ
  • ሻይ — ጻይ
  • ጭማቂ — ቹስ, ሹስ
  • ውኃ — ኡስ
  • ቢራ — ጲው
  • ጠጅ — ታርስ
  • ጨው — ታውስ
  • በሬ ሥጋ — ኡሕሪን ማሕ
  • ዐሣማ ሥጋ — ጋሓይን ማሕ
  • ዐሣ — ዛጋስ
  • ዶሮ — ጣሕያኒ ማሕ
  • አትክልት — ኖጎ
  • ፍራፍሬ — ቺምስ
  • ሰላጣ — ኖጎን ጹሽ, ሳላት
  • ...የት አለ? — ...ሓን ፓይን ወ?
  • የጉዞው ዋጋ ስንት ነው? — ፒለጥ ያማር ኡንጠይ ወ?
  • ቲኬት — ፒለጥ
  • አንድ ቲኬት ወደ... — ነግ ፒለጥ...
  • ባቡር — ጋልጥ ጠረግ
  • አውቶቡስ — አውቶቡስ
  • አይሮፕላን ማረፊያ — ኒሰሕ ኦንጎጽኒ ፑታል
  • ባቡር ጣቢያ — ጋልጥ ጠርገኒ ፑታል
  • አውቶቡስ ጣቢያ — አውቶቡስኒ ፑታል
  • መነሻ — ያዋሕ
  • መድረሻ — ሑረልጸን ኢረሕ
  • መቆሚያ — ማሺን ፓይርላሕ ጋጻር
  • ሆቴል — ጾጪት ፑታል
  • ክፍል — ኦሮ
  • የይለፍ ወረቅት — ጋታት ጳስጶርጥ
  • ግራ — ጹን
  • ቀኝ — ፓሩን
  • ቀጥታ — ጪጌሬ
  • ወደላይ — ቴሼ
  • ወደታች — ቶሾ
  • ሩቅ — ሖል
  • ቅርብ — ኦይር
  • ረጅም — ኡርጥ
  • አጭር — ፖጊን
  • ካርታ — ጋጽሪን ጹራግ
  • የቱሪስት ቢሮ — ቹልጪኒ ጋጻር
  • ፖስታ ቤት — ሹታንጊን ሳልፓር
  • ቤተ መዘክር — ሙጸይ
  • ባንክ ቤት — ፓንክ
  • የፕኦሊስ ጣቢያ — ጻግታጊን ጋጻር
  • ሆስፒታል — ኤምነለግ
  • የመድኃኒት መደብር — ኤሚን ሳን
  • ሱቅ — ተልጉር
  • ገበያ — ጻሕ
  • ምግብ ቤት — ጾጎይ
  • ትምህርት ቤት — ሱርጉል
  • ቤተ ክርስቲያን — ሱም
  • ሽንት ቤት — ቾርሎን
  • መንገድ — ጉታምች
  • አደባባይ — ጣልባይ, ቲርዎልቺን
  • ተራራ — ኡል
  • ኮረብታ — ቶው
  • ሸለቆ — ሖንቲ
  • ሓይቅ — ኑር
  • ወንዝ — ጎል
  • መዋኛ — ፓሰይን
  • ድልድይ — ጉር
  • መቅደስ — ሱም
  • ገዳም — ሒት
Wikipedia
Wikipedia