ሥነ-ሐተታ አማልክት
ሥነ-ሐተታ አማልክት (ሚቶሎጂ) ሄርሜቴክ ፍልስፍና ዳግም ውልደት፦ ፯ቱ ጥንታዊያን መርሆዎች 1. የሥነ አእምሮ (ሜንታሊዝም) መርሆ፦ ሁሉም ነገር አእምሮ ነው፤ ሕዋም አእምሮ ነች። 2. የተዛምዶ መርሆ፦ ልክ ከላይ እንዳለው፣ ልክ ከታች እንዳለው ተመሳሳይ ይሆናል። ልክ ከታች እንዳለው ከላይ ያለው ጋር ተመሳሳይ ይሆናል። በመሃል ያለው ከመሃል ይወጣል፤ ከመሃል የወጣው ከመሃል ይሆናል። 3. የንዝረት መርሆ፦ ምንም ባለበት የሚጸና የለም። ሁሉም ነገር ይንቀሳቀሳል፤ ሁሉም ነገር ይነዝራል። 4. የተቃርኖ መርሆ፦ ሁሉም ነገር በሁለታዊነት የተዋቀረ ነው፤ ሁሉም ነገር ተቃራኒ አለው፤ ሁሉም ነገር ተቃራኒ ተጣማጅ አለው፤ የሚመሳሰል እና የማይመሳሰል አንድ ናቸው፤ ተቃራኒዎች በተፈጥሮ ዐይን አንድ ናቸው፤ ሆኖም ግን በመጠን ደረጃ ይለያያሉ፤ ጽንፎች መጨረሻ ላይ ይገናኝሉ፤ ሁሉም እውነት ነው ግን ግማሽ እውነት ብቻ፤ ሁሉም ተቃርኖዎች ሊታረቁ ይችሉ ይሆን ይሆናል። 5. የሥልተ ምት መርሆ፦ ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ ይፈሳል፤ ወደ ውስጥ እና ወደ ውጭ። ሁሉም ነገር የራሱ ሞገድ አለው፤ ሁሉም ነገሮች ይነሣሉ ደግሞ መልሰው ይወድቃሉ፤ የፔንዱለም ውዝዋዜ በሁሉም ነገር ውስጥ ይንጸባረቃል፤ በግራ በኩል ያለው የፔንዱለም ጉዞ ወደ ቀኝ ካለው የፔንዱለሙ ጉዞ ጋር እኩል ርቀት ነው፤ ሥልተ ምት ተቻችሎ ይቀጥላል። 6. የምክንያት እና ውጤት መርሆ፦ እያንዳንዱ ምክንያት የራሱ ውጤት አለው፤ እያንዳንዱ ውጤት የራሱ ምክንያት አለው፤ ሁሉም ነገር የሚሆነው “ዕድል ያልታወቀ ሕግ ስያሜ” ነው የሚለው ሕግ መሠረት ነው። በርካታ የተለዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ ሆኖም ምንም ከዚህ ሕግ የሚወጣ ነገር የለም። 7. የሥነ ጾታ መርሆ፦ ጾታ በሁሉም ነገር ውስጥ አለ፤ ሁሉም ነገር የየራሱ ተባዕታይ እና አንስታይ መርሆዎች አሉት፤ ጾታ በሁሉም ነገር ላይ ይንጸባረቃል።