ሥነ ኑባሬ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎችፍለጋ

ሥነ ኑባሬ አንድ አካል መሰረት ነው። የዚህ ፍልስፍና ዋና አትኩሮት የ ኑባሬን ተፈጥሮ መመርመር ነው።

ኑባሬ ማለት የማንነት ተቃራኒ ነው። ምንም ሲባል ባዶ፣ አልባ ፣ ከኦና በላይ ዘልቆ፣ ቁስ አካልም ሆነ፣ ኅዋ፣ ጊዜም ሆነ ብርሃን የሌለበት፣ ባዶ ብቻ ሳይሆን የባዶ መጨረሻ ማለት ነው። ኑባሬ እንግዲህ ከምንም ተቃራኒ የሆነ፣ የሚኖር ወይንም ያለ ማለት ነው።

ይሁንና በአንዳንድ ፈላስፋዎች ዘንድ የኑባሬ ትርጉም ከላይ ከተሰጠው የጠበበ ሆኖ ይገኛል። ኑባሬ ማለት የክስተቶች ተሸካሚ ሆኖ ነገር ግን ክስተቶችን አይጠቀልልም። ለምሳሌ አንድ ሎሚ፣ ቀለሙ፣ ድብሉቡልነቱ፣ ሽታው፣ ወዘተ... የሎሚው ክስተት ሲሆኑ፣ ነገር ግን እነዚህም ባሕርዮች ሁሉ ተሸክሞ የሚገኘው ፣ መኖሩ ወይንም ኑባሬው ይባላል። ስለዚህ ኑባሬው የሎሚው ዲበ አካላዊ ባሕርዮት ሆኖ ይገለጻል ማለት ነው።