ሥነ ውበት

ከውክፔዲያ

ሥነ ውበት (aesthetics) ስለ ስሜታዊ ግንዛቤ የሚመረምር የፍልስፍና ዘርፍ ነው። ያንድን ነገር ጥቅም፣ ይዞታ፣ ምክንየት ወዘተ... ከመመርመር ይልቅ፤ የዚያን ነገር ስሜት ቀስቃሽነት የሚያጠና ክፍል ነው። ከዚህ አኳያ፣ የሥነ ውበት ፈላስፋዎች አጥብቀው የሚያጠይቁት ሰዎች ምን መስማት፣ ማየት፣ ማሽተት፣ መንካት እና መቅመስ እንደሚወድዱ ነው።

ለስሜት ተፈላጊ የሆነ ነገር ውበት አለው ይባላል። ይሁንና ውበት በራሱ ከነገሮች የሚፈልቅ ሳይሆን ከሰው ልጅ ኅሊና ውስጣዊ ሁኔታ የሚመነጭ ነው። የተለያዩ ሰዎች አንድን ነገር ውብ ወይንም ፉንጋ ብለው ሊረዱ ይችላሉ። ምክንያቱም ውበት ከነገሩ ጋር ያለ ሳይሆን ከታዳሚው አዕምሮ የሚፈልቅ ስለሆነ።

ውበት ከተፈጥሮ ብቻ ሳይሆን ከሰው ስራም ይመነጫል። ይህም የሚከናወነው በኪነ ጥበብ ነው። «ኪነ-ጥበብን ለማመንጨት የውበት ድርሻ ምንድን ነው?» «ውበትስ እንዴት ሊፈጠር ይችላል?» የሚሉት ጥያቄዎች በዚህ የፍልስፍና ዘርፍ ይመረመራሉ።


በመጀመርያ ሥነ ውበት ማለት እግዚአብሔር በ፮ቱ ቀናት ውስጥ የፈጠራቸዉ ውብ የእጆቹ ስራዎቾ ናቸው። ከነዚህ ውስጥም የእፅዋትን የአበቦችን ሥነ ውበት በምንመለከትበት ጊዜ አስደናቂ ቀለማት፣ አስደናቂ የቅርፅ አጨራረሶች፣ ወቅቶችን እየጠበቁ እራሳቸውን ለእይታና መአዛቸውን ለሰው ልጅ ደስታን የሚያጎናፅፉ፣ ልዮ የስነ ውበት መድረኮችና መታያዎች፣ ዘመን የማይሽራቸዉ ዘናጮች ሊባሉ ተቻለ። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይም የእግዚአብሔር ቃል ስለ አበቦች ስነ ዉበት ሲናገር «ጠቢቡ ሰለሞን ከእነዚህ አበቦች እንደ አንዱ አለበሰም» ተብሎ ተፅፏል ።

የወፎች ዉበት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አሁንም ሥነ ውበትን ስንመለከት የወፎች ሥነ ውበት በጣም ያስደንቃል። የወፎች ሥነ ውበት ከአበቦች ሥነ ውበት ጋር ብዙ ተመሣሣይነት አላቸው። ሁለቱም የብዙ የተፈጥሮ ህብረቀለማት ባለቤቶች ናቸው።

የአበቦችን የወፎችን ሥነ ውበት ለመመልከት በዐይነ ህሊናችን ወደ አንድ ሰፊ የአበባ መስክ ከጥዋቱ ፩ ሰአት እስከ ፫ ወይም ከሰአት በኋላ ከ፲ እስከ ፲፪ ባለው ሰአት ብንሂድ በደንብ አይነ ህሊናችን ሊከፈት ይችላል··· አበቦችን ስንመልከት ፡ የተለያየ ቀለማቸውን፣ ቅርፃቸውን ፣ ወፎችን ስንመልከት፤ የተለያየ ቀለማቸውን፣ ቅርፃቸውን ፤ ወፎች አበቦችን እየቀሰሙ በተለያየ ውብ ድምፅ ሲያቀነቅኑ ሲያፏጩ ሲያዜሙ ስናዳምጥ ሲደንሱ ስንመለከት ፤ አበቦች ፀጥታን ተላብሰው በወፎች ሙዚቃ የሚያውደውን ውብ ጠረናቸውን ከግራ ወደቀ፣ በውዝዋዜ እየነሰነሱ ዳንሳቸውን ስንመለከት ፤ የዚህ ሁሉ ጥምር ሥነ ዉበት ይባላል።