ሥነ ፈሳሽ

ከውክፔዲያ
ፓስካል ሕግን ተጠቅሞ፣ በትንሽ ጉልበት ትልቅ ጭነትን ማንሳት እንደሚቻል የሚያሳይ የሥነ ፈሳሽ ጥናት ፍሬ

ሥነ ፈሳሽ የተፈጥሮ ኅግጋት (ፊሲክስ) ጥናት ክፍል ሲሆን ትኩረት ሰጥቶ የሚመራመረው ስለ ፈሳሽአየር እና ፕላዝማ ቁስ አካላት ሥነ እንቅስቃሴ ነው። የዚህ ዕውቀት መስራች ተብሎ የሚታዎቀው የጥንቱ ግሪክ አርኪሜድስ ነው። አርኪሜድስ «ጠጣር ነገሮች በፈሳሽ ነገር ውስጥ ለመንሳፈፍ ምን ምክንያት አላቸው?» የሚለውን ጥያቄ ለመፍታት ሞክሮ፣ በኋላም ስለዚህ ጉዳይ መሪ ሃሳብ ሲያገኝ፣ ዩሬካ እያለ በደስታ በግሪክ አገር መንገዶች እራቁቱን እንደሮጠ ትርክት አለ።