Jump to content

ርቢ ስብስብ

ከውክፔዲያ

ስብስብ S ርቢ ስብስብ የምንለው ማናቸውንም የስብስብ S ታህታይ ስብስቦች አቅፎ የሚይዝን ስብስብ ነው። ማለት ከ S አባላት የሚሰሩ ማናቸውንም ስብስቦችና ባዶ ስብስብን ይይዛል። አንድ ብዛቱ አእላፍ ያልሆነ (አባላቱ የሚያልቁ) ስብስብ ብዛቱ n ቢሆነ የርቢ ስብስቡ ብዛት 2n ነው። የርቢ ስብስብ እንዲህ ይወከላል P(S).

ለምሳሌ፡

{1, 2, 3} ስብስብ ቢሰጠን፣ ርቢ ስብስቡ ይሄ ነው {{1, 2, 3}, {1, 2}, {1, 3}, {2, 3}, {1}, {2}, {3}, ∅}. የመጀመሪያው ስብስብ ብዛት 3 ሲሆን የርቢ ስብስቡ ብዛት 23 = 8 ነው።