Jump to content

ሰማያዊ አረንጓዴአማ ዋቅላሚዎች

ከውክፔዲያ
ሲሊንድሮስፔርመም
ሰማያዊ አረንጓዴአማ ዋቅላሚዎች

ሰማያዊ-አረንጓዴአማ ዋቅላሚዎች ወይም ሲያኖባክቴርያዎች ኦክስጅን አመንጪ በሆነ ብርሀናዊ አስተፃምሮ ሂደት አማካኝነት የራሳቸውን ምግብ ማምረት የሚችሉ ግራም-ኔጌቲቭ ባክቴርያዎች ናቸው። [1]

ሲያኖባክቴርያዎች መጀመሪያ የተገኙት በንጹህ ውሃ ወይም በየብስ አካባቢ እንደሆነ የሚታመን ሲሆን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የታዩትም በመካከለኛው "አርኪያ ኢዮን" [2](Archean eon) ዘመን ነበር።እነዚህ ፍጥረታት በምድር ላይ እስካሁን ከኖሩ ሕይወት ያላቸው ፍጥረታት ዝርያዎች ሁሉ በቁጥር ቀዳሚዎቹ ሳይሆኑ አይቀሩም።[3]

"ሲያኖባክቴርያ " የሚለው ስም "ሰማያዊ" ትርጉም ካለው ጥንታዊ የግሪክ ቃል κύανος (kúanos) የተገኘ ሲሆን፣ ይህም ሰማያዊ-አረንጓዴአማ (cyan) ቀለማቸውን[4] [5]ያመለክታል። ይህም "ማያዊ-አረንጓዴአማ ዋቅላሚዎች" (blue-green algae) ለሚለው መደበኛ ያልሆነ የጋራ መጠሪያ ስማቸው መነሻ ሆኗል።

  1. Sinha RP, Häder DP (2008). "UV-protectants in cyanobacteria" (PDF). Plant Science. 174 (3): 278–289. doi:10.1016/j.plantsci.2007.12.004. Archived from the original (PDF) on 15 April 2021.
  2. Sánchez-Baracaldo, Patricia (December 2015). "Origin of marine planktonic cyanobacteria". Scientific Reports. 5 (1) 17418. Bibcode:2015NatSR...517418S. doi:10.1038/srep17418. PMC 4665016. PMID 26621203
  3. Stal LJ, Cretoiu MS (2016). The Marine Microbiome: An Untapped Source of Biodiversity and Biotechnological Potential. Springer Science+Business Media. ISBN 978-3-319-33000-6.
  4. Harper, Douglas. "cyan". Online Etymology Dictionary. Retrieved 21 January 2018.
  5. κύανος. Liddell, Henry George; Scott, Robert; A Greek–English Lexicon at the Perseus Project.