ሰርቲፊኬት ኦፍ ዲፖዚት
Appearance
ሰርቲፊኬት ኦፍ ዲፖዚት ወይንም ሲዲ እንደ ሴቪንግ አካውንት የቁጠባ አገልግሎት መስጫ መሳሪያ ነው። ሆኖም ከሴቪንግ አካውንት በተሻለ መልኩ ወለድ ሲያስገኝ፣ ሆኖም ግን የተቆጠበን ገንዘብ በቀላሉ ለማውጣት አያስችልም።
በሰርቲፊኬት ኦፍ ዲፖዚት የተቀመጠ ገንዘብ ለተውሰነ ጊዜ (3 ወር፣ ወይንም 6ወር...) ከባንክ እንዳይወጣ ይታገዳል። በዚህ ወቅት ገንዘቡ ቋሚ ወለድ ይወልዳል። ጊዜው ሲያበቃ ገንዘቡን ማውጣት ይፈቀዳል። አለበለዚያ ለቀጣዩ ጊዜ እንደገና ይቀመጣል። በነዚህ በተወሰኑ ጊዜያ ውጭ ደንበኞች ገንዘባቸውን ለማውጣት ቢሞክሩ፣ ከፍተኛ ቅጣት ተደርጎ ገንዘባቸው ይንቀሳቀሳል።