ሰይፉ በኢቢኤስ

ከውክፔዲያ

ሰይፉ በኢቢኤስኢቢኤስ ቴሌቪዥን ላይ በየእሑድ ሌሊት ከኢትዮጵያ አዲስ አበባ እስቱዲዮ የሚሠራጭ የሌሊት ውይይት ትርዒት ነው። ከ2006 ዓም ጀምሮ ለዘጠና ደቂቃ ከአስተናጋጁ ሰይፉ ፋንታሁን ይቀርባል። እንደ አሜሪካ አገር የሌሊት-ውይይት ልማድ በመምሰል፣ አስቂኝ ክፍሎች፣ የቀልድ ንግግሮች፣ ሙዚቃዊ ትርዕይቶችና የዝነኛ ቆይታዎችም ያቀርባል።

እንደ በርካታ አሜሪካዊ ትዕይንቶች ስልት፣ የተመሠረተውን ስድስት ክፍል ፎርማት ይከተላል። በዘልማድ እነኚህም ፮ ክፍሎች፡

  • ክፍል ፩ - ንግግር
  • ክፍል ፪ - አስቂኝ ክፍሎች
  • ክፍል ፫ - የዝነኛ ቆይታ 1
  • ክፍል ፬ - የዝነኛ ቆይታ 1 ተቀጥሎአል
  • ክፍል ፭ - የዝነኛ ቆይታ 2
  • ክፍል ፮ - ሙዚቃዊ ወይም ኮሜዲ እንግዳ፣ መጨረሻ

የሰይፉ መጀመርያ ንግግር ከወቅታዊ ጉዳዮች የሚለቀም ነው። አንዳንዴም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተገኙ ስዕሎች ወይም ክሊፖች ያሳያል።

በአስቂኝ ክፍሎቹ በዘልማድ ሰይፉ ከተመልካቾች ጋራ ጨዋታ ያደርጋል፣ ወይም ከእንግዳው ጋር አስቂኝ ትርዒት ያደርጋል።

ዝነኛ እንግዶቹ ከሰፊ ባሕላዊ ምንጮች የሚመጡ ሲሆን ተዋናውያን፣ ደራስያን፣ አትሌቶችና ፖለቲከኞች ሆነዋል።[1][2]

እንዲሁም ትርዒቱ የራሱን «ሀበሻ ባንድ» ይኖረዋል።

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Bogale, Samuel (25 July 2017). "Ethiopia: The Ailing State of Health Care in Ethiopia's State-Run Hospitals: Who Takes the Blame?". All Africa. http://allafrica.com/stories/201707251008.html. 
  2. ^ "Captain Guta Dinka, the Man Who Saved Mandela’s Life in Ethiopia". Awramba Times. December 19, 2013. http://www.awrambatimes.com/?p=11143.