ሱሙ-አቡም
Appearance
ሱሙ-አቡም ከ1807 እስከ 1793 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የባቢሎን መጀመርያ ንጉሥ ነበረ።
በዚህ ወቅት የኢሲንና የላርሳ መንግሥታት ለሱመርና ለአካድ ላዕላይነት ሲወዳደሩ ብዙ ነጻ ከተማ-አገሮች ወደ ስሜን ተነሡ። ከነዚህ መካከል አንዱ ካዛሉ ሲሆን አሞራዊው ሱሙ-አቡም በ1807 ዓክልበ. ግድም የባቢሎን ነጻነት ከካዛሉ አዋጀ። ከዚህ በኋላ ከዓመት ስሞቹ ኢሊፕ (የ«ማናና» መንግሥት ከተማ)፣ ኪሽንና ካዛሉን ወደ ግዛቱ መጨምር እንደ ተቻለው ይመስላል።
ለዘመኑ ከ፲፬ የዓመት ስሞቹ ሁላቸው በሙሉ ታውቀዋል። ከነርሱም መካከል፦
- 1807 ዓክልበ. ግ. - «ሱሙ-አቡም ንጉሥ የሆነበት ዓመት» / «የባቢሎን ታላቅ ግድግዳ የተሠራበት ዓመት»
- 1805 ዓክልበ. ግ. - «የኢሊፕ ከተማ ግድግዳ የተያዘበት ዓመት»
- 1798 ዓክልበ. ግ. - «የኪሽ ግድግዳ የሠራበት ዓመት»
- 1795 ዓክልበ. ግ. - «ሱሙ-አቡም ካዛሉን ያጠፋበት ዓመት»
የሱሙ-አቡም ተከታይ ሱሙላኤል ነበረ።
ቀዳሚው የለም (አዲስ) |
የባቢሎን ንጉሥ 1807-1793 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ሱሙላኤል |