ስልጤ

ከውክፔዲያ

የስልጤ በሀገራችን ከሚገኙ በርካታ ብሔሮች: ብሔረሰቦችና ህዝቦች አንዱ ነው: ብሔረሰቡ በአዲስ አበባ-ሆሳዕና መንገድ በ172 ኪ.ሜ ርቀት ከመንገዱ ግራና ቀኝ 60 ኪ.ሜ ያህል ገባ ብሎ በሚገኘው በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን በስፋት ይኖራል የዞኑ ጠቅላላ ስፋት 3ሺkm² ነው:: እኤአ 2004 በተደረገ ቆጠራ በዞኑ የሚኖረው 850ሺ በዞኑ መስደደር ቢቻ የነበረ ሲሆን የዞኑ ተወላጆች ያዞኑ ህዝብ በሁኑ ሰዓት ከ900ሺ በለይ ይሆናል ተቢሎ ይታሰበል ።ከዞኑ በተጨማሪ ከ1 ምሊዬን በለይ ከዞኑ ጎራቤት ካጉራጌ፣ካሀድያ ፣ካኣለበ ና ካኦሮሞ ቤሔራሰቦች ታቀለቅሎ ሳፍሮወል እነም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎችና የውጪ ሀገራትም በስፋት ተሰራጭተው ይኖራሉ:: ከብሔረሰቡ 45% የሚሆነው የእስልምና ዕምነት ተከታይ ነው::0.9 % የኣመራና የሌላ ብሔርሰብ ኦርቶዶክስ ክርታን ይኖርበታል ።ከዞኑ ውጭ የሉ ስልጤዎች 100% የስልምና ተካታይ ሲሆኑ በታጫር ከ99 % በለይ በከፍል ስልጤ ሙስልሞች ነቸው። መለትም በኣበት ዎይም በእነት የስልጤ ዝርየነት የለቸው ነቸው።ግብርና ዋነኛ የኢኮኖሚ መሠረት ሲሆን ከብት አርባታና ንግድም እንዲሁ የብሔረሰቡ የሀብት ምንጭ ናቸው:: .. ዞኑ አሁን በስምንት ማለትም:- ምዕራብ አዘርነት:ምስራቅ አዘርነት:አልቾውሪሮ:ዳሎቻ:ላንፎሮ:ሳንኩራ :ሁልባረግና ስልጢ ወረዳዎች የተዋቀረ ነው::የብሔረሰቡ ቋንቋ ስልጢኛ ሲሆን ከሴማዊያን ቤተሰቦች ይመደባል .. የቋንቋው ስፋት ከሀረሪኛና የዛይ ቋንቋ ጋር በጣም ሲመሳሰል በበርካታ የቃላት ትርጉዋሜ ደረጃ ከአረብኛ: አማርኛ ትግርኛ አርጎቢኛና ኦሮምኛ ጋርም ይገናኛል:: "ስልጤ" የሚለው ስም በዞኑ በሚገኙ በዋነኛነት አምስት ማኅበረሰቦች ማለትም ስልጢ:መልጋ:ሁልባረግ:አዘርነት በርበሬና አልቾውሪሮ የጋራ መጠሪያ ሲሆን ማኅበረሰቦቹ በታሪክ: በማኅበራዊ ኑሮ :በባህል: በቋንቋና በሀይማኖት እንዲሁ ተመሳሳይ ናቸው የስያሜውን መነሻ በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎች ያሉ ሲሆን ስያሜውን ያገኘው ከሀጂ አሊዬ 5ተኛ ልጅ ከሆኑት ገን-ስልጤ አልያም ሱልጣኔት ከሚለው አረብ ኢስላማዊ መንግስት ጥንታዊነት እንዲሁም ነባር ኢስላማዊ መንግስታትና ማኅበረሰቦች የታሪክ ወራሽነትን በማሰብ ነው የሚለው በስፋት ይገለፃል:: ስልጤ የምጣረበቸው ታጨመር ስሞች `` እስላም``ታብሎ ስጣራ ፡ ቋንቋቸው` እስለምኛ `በመበል በደቡብ ክፍል እስከ ዘሬ ይታዎቀል .ክሰሜን' ጉራጌ` ታብሎ የምታዎቅ ብሆንም ስልጤ የረሱን ዞን ከመሰራተ ጀምሮ ስሙ ለይመለስ ቀርቶዎል። የስልጤ ብሔረሰብ ብሔረሰቡ በዋናነት በክልሉ በስልጤ ዞን ውስጥ በሚገኙ ስምንት ወረዳዎች በሀገር ውስጥ ፣ በዎላይታ፣ በሲዳማ እና ጌዲኦ ዞኖች፣ በሀዋሣ ከተማ እና በሀላባ ልዩ ወረዳ እንዲሁም ከክልሉ ውጪ በጂማ፣ በወለጋ፣ በናዝሬት /አዳማ/ ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በአደስ አበባ ከተሞች ከሌሎች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ጋር በስብጥር ይኖራሉ፡፡ ብሔረሰቡ በዋናነት የሚኖርበት ሥፍራ በሰሜን እና በሰሜን ምዕራብ የጉራጌ ዞን፣ በደቡብ የሀዲያ ዞን እና የሀላባ ልዩ ወረዳ፣ በምዕራብ የሀዲያ ዞን ፣ በምስራቅ የኦሮሚያ ክልል ያዋሰኑታ፡፡ የብሔረሰቡ ዋነኛ መገኛ ሥፍራ መልክዐ ምድራዊ አቀማመጥ በአብዛኛው ሜዳማ ሲሆን የተወሰነው በተለይም ምዕራባዊው ክፍል ተራራማነት ያለው ነው፡፡ የአየር ንብረቱ በተለያዩ ደረጃ ደጋማ፣ ወይናደጋማ እና ቆላማ ሲሆን አብዛኛው ክፍል ወይናደጋማ ነው፡፡ የሕዝቡ ኢኮኖሚ የተመሰረተው በዋናነት በእርሻ ሲሆን ከዚሁ ጐን ለጐን የተወሰነው ክፍል የከብት እርባታን፣ ንግድን፣ እና አንዳንድ የእደ ጥበብ ውጤታችን በማምረት ኑሮአቸውን ይመራሉ፡፡ በዋናነት ከሚመረቱ የእርሻ ምርቶች መካከል በርበሬ ፣እንሰት፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ ፣ ገብስ፣ አተር፣ ባቄላ፣ ቦሎቄ፣ አደንጓሬ፣ ቡና፣ ጫት፣ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ቋንቋ የስልጤ ብሔረሰብ አፍ መፍቻ ቋንቋ ስልጢኛ ሲሆን ከሴማዊ የቋንቋ ቤተሰብ ይመደባል፡፡ ቋንቋው ከአረብኛ፣ ከጉራጊኛ ፣ ከሐረሪ፣ ቋንቋዎች ጋር ይመሳሰላል፡፡ የብሔረሰቡ አባላት ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ በከተሞች አካባቢ ያሉ አማርኛን እንዲሁም እንደ አጐራባችነታቸውና ቅርበታቸው የሀድይኛ፣ የማረቆኛ፣ የጉራግኛ፣ የኦሮምኛ እና የሀላብኛን ቋንቋዎች በሁለተኛ ደረጃ ይናገራሉ፡፡ ሌሎችም አጐራባች ብሔረሰቦች እንዲሁ የስልጢኛን ቋንቋ እንደየቅርበታቸው ለመግባቢያነት ይጠቀማሉ፡፡ ስልጢኛ ከ6ዐ ዓመት በፊት የአረብኛ ፊደልን በመጠቀም ለጽሑፍ የዋለ ቋንቋ ቢሆንም ከ1967 ዓ/ም ጀምሮ ልዩ ልዩ አዋጆች እና የመሰረተ ትምህርት ማስተማሪያ መጽሐፍት የሳባ ፊደልን በመጠቀም በቋንቋው ተተርጉመዋል፡፡ ከ1987 ዓ/ም ጀምሮ የ1ኛ ደረጃ የመጀመሪያ ሣይክል የመማሪያ መጽሐፍት በቋንቋው ተዘጋጅተዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የትምህርት ቋንቋ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ እንደዚሁም የሣባ ፊደልን በመጠቀም የመማሪያ መጽሐፍት፣ የስልጢኛ መዝገበ ቃላት፣ የስልጤ ሕዝብ ታሪክ እና ሌሎች መጽሀፍቶች በቋንቋው ተጽፈው አገልግሎት እየሠጡ መሆናቸው ቋንቋው በማደግ ላይ ያለ ስለሚሆኑ የሚገልፁ እውነታዎች ናቸው፡፡ ታሪካዊ አመጣጥ የስልጤን ብሔረሰብ ታሪካዊ አመጣጥ በተመለከተ በብሔረሰቡ የዕድሜ ባለፀጋዎች የሚነገሩ የትውፊት እና አንዳንድ የተገኙ የጽሑፍ መረጃዎችን በሁለት መልኩ ከፍለን እንመለከታለን፡፡ የመጀመሪያው የትውፊት መረጃ እንደሚያመለክተው በጥንት ጊዜ ዛሬ የብሔረሰቡ አባላት በሚኖሩበት ሥፍራ "ዡራ" ወይንም "ሀርላ" በመባል የሚታወቁ ሕዝቦች ይኖሩ እንደነበር ይገልፃል፡፡ ሌላው መረጃ ደግሞ በ8ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ የተወሰኑ ቀደምት የብሔረሰቡ አባላት ከምድረ ሣውዲ አረቢያ ተነስተው የኤደን ባህረ ሰላጤን አቋርጠው በስተምስራቅ አቅጣጫ በዘይላ ደሴት በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ያመለክታል፡፡ እነዚህ ሕዝቦች በፀሐይ መውጫ አቅጣጫ ወደ አገሪቱ ክፍል ከገቡ በኋላ በሐረር ጀበርቲ ዛሬ “አደሬ” ወይንም "ሐረሪ" በሚባለው አካባቢ ቆይታ አድርገው ወደ ዛሬው መገኛ ሥፍራ በመምጣት ከነባሩ ሕዝብ ጋር ተቀላቅለው መኖር እንደጀመሩ ይነገራል፡፡ የነዚህ ክፍሎች አመጣጥ በአብዛኛው እስልምናን ከማስተማር ጋር የተያያዘ እንደነበር የተገኙ የትውፊት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የተወሰኑ የብሔረሰቡ አባላት ደግሞ የግራኝ መሀመድ ወረራ ካበቃ በ1ዐኛው ዓመት ገደማ ከ1553/63 በሀጂ አልዬ መሪነት የተለያዩ ቦታ እየሠፈሩ አሁን በዋናነት ወደ ሚኖሩበት አካባቢ እንደደረሱ ይነገራል፡፡ ሀጂ አልዬ በአባታቸው ኢትዮጵያዊ በእናታቸው የአረብ ዝርያ እንዳላቸው የሚነገር ሲሆን በስፍራው ሲደርሱ በመጀመሪያ መቀመጫቸውን ያደረጉት አልቾ ወሬሮ ላይ እንደነበር በታሪክ ይነገራል፡፡ በዚያን ወቅት የነበረው የስልጤ ሕዝብ ወደአሁኑ ስፍራ ከመድረሱ በፊት ገደብ ዝዋይ / ላቂ ደንበል/፣ ሲዳማ፣ አሊቶ ዳገት /ቡልቡላ አጠገብ/ በሚባሉ አካባቢዎች ቆይታ እንዳደረገ የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በወቅቱ ለሕዝቡ እንቅስቃሴ እንደምክንያት የሚገለፀው በግራኝ መሀመድ የተነሣ ጥሩ የመኖሪያ አካባቢ ለመፈለግ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በታሪክ አጥኚዎች ደሞ እንደሚነገረው ስልጤ ጙራጌ እና ሌሎች በአካባቢው የሚገኙ ብሄረሰቦች፥ በቋንቋቸው፡ በደማቸው ጥናት (ጀነቲክስ)፡ በስነ ልቦናቸው፥ በባህላቸው ወዘተ፥ ከሰሜን ኢትዮጵያ በተለይ ከዐማራ ብሄር በ8ኛው-10ኛው ክፍለ ዘመን ፈልሰው በአካባቢው የሰፈሩ ሰፋሪዎች እንደሆኑ ያመላክታል። ይህም ጊዜ ከኦሮሞ ፍልሰት 5መቶ-7መቶ አመታት በፊት ነው።