ስቅለት (የማይክል አንጄሎ ቅርጽ)

ከውክፔዲያ
(ከስቅለት የተዛወረ)
ስቅለት
“የማይክል አንጀሎ የናዝሬቱ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉስ”


ስቅለት በማይክል አንጄሎ ቡናሮቲ

በ1492 ስቅለት የተባለውን ቅርጽ ከእንጨት በመቅረጽ የእንደገና መወለድ ዘመን ሰአሊ ማይክል አንጄሎ ቡናሮቲ በስጦታ አበርክቷል። ስቅለት የተባለው ቅርጽ አሁን የሚገኘው ቅድስት ማሪያም ዴላ ሳንቶ ስፒሪቶ ከሚባለው ቤተክርስቲያን ውስጥ ከመንበሩ በላይ ነው። ቅርጹ ብዙ ትኩረትን የሳበው ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ እርቃነ ስጋውን በመሆኑ ነው::

ታሪኩ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማይክል አንጄሎ ቡናሮቲ በቅድስት ማሪያም ሳንቶ ስፒሪቶ ቤተክርስቲያን (ፍሎሬንዝ) ስብሰባ ውስጥ በእንግዳነት ተጋብዞ ነበር እድሜውም አስራ ሰባት አመት ነበር። ከሎሬንዞ ደ ሚዲቺ ሞት በኋላ በዚህም የሰውነት ቅርጽን ትምህርቱን በሞቱ ሰዎች አስከሬን ላይ ልምምድ አድርጓል። ይህንንም ልምምድ ያደረገው በቤተ ክርስቲያኑ ንብረት ከነበረው ሆስፒታል ውስጥ ነበር። በአንጻሩም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስቅለት ከ እንጨት በመቅረጽ ለቤተ ክርስቲያኑ በስጦታ አበረከተ። ይህም ቅርጽ ዛሬ በቅድስት ማሪያም ሳንቶ ስፒሪቶ ቤተክርስቲያን ከመንበሩ በላይ ይገኛል።

መግለጫ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እርቃነ ስጋውን የቀርጸው ምንም ሳይጋነን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደሚለው የሮማን ወታደሮች ልብሱን ይከፋፈሉታል በእጀ ጠባቡንም እጣ ይጣጣሉበታል ብሎ የተጻፈው እንዲፈጽም ነው። መዝሙር 22፡18 በወንጌሎቹም ሁሉ ላይ ይህ ተጽፏል። ፓውሎስ ግን በዝርዝር ጽፎታል።


“ወታደሮቹ ኢየሱስን ከስቀሉ በኋላ እጀ ጠባቡ ሲቀር ልብሱን ወስደው ለእያንዳንዱ አንድ አንድ እንዲዳረስ ለአራት ተከፋፈሉት እጀ ጠባቡንም ከላይ አንድ ወጥ ሆኖ ያለ ስፌት የተሰራ ነበር። ስለዚህ ዕጣ ተጣጥለን ለሚደርሰው ይድረስ እንጂ አንቅደደው ተባባሉ። ይህም የሆነው ልብሴን ተከፋፈሉት በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ የሚለው የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው። ወታደሮቹ ያደረጉትም ይህንኑ ነው። “


ይህን የስቅለት ቅርጽ ልዩ የሚያደርገው ከመስቀሉ ላይ ያለው የጌታችን የመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክስ በ እብራይስጥ በግሪክ እና በላቲን ቋንቋ የተጻፈ ነበር። ቃሉም የሚለው ” የናዝሬቱ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉስ” የሚል ነበር። ማይክል አንጄሎ ቡናሮቲም ይህን ጽሁፍ የወሰደው ከዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ 19 19ነው። ጲላጦስም ጽሑፍ ጽፎ በመስቀሉ ላይ አንጠለጠለው። ጽሑፉም “የናዝሬቱ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉስ” የሚል ነበር ። የአይሁድ የካህናት አለቆች ጲላጦስን በመቃወም እርሱ “የአይሁድ ንጉስ ነኝ እንዳለ ጻፍ እንጂ “የአይሁድ ንጉስ ብለህ አትጻፍ አሉት ጲላጦስም በቃ የጻፍኩትን ጽፌአለሁ ብሎ መለሰ።

ከወታደሮቹ አንዱ ኢየሱስን በጦር ወጋው ወዲያውም ደምና ዉሃ ፈሰሰ ይህን ያየው ሰው ምስክርነቱን ሰጥቶአል ምስክርነቱም እውነት ነው እውነት እንደሚናገርም ያውቃል እናንተም እንድታምኑ ይመሰክራል። ይህም የሆነው መጽሐፍ ከአጥንቴ አንድም አይሰበርም ያለው እንዲፈጸም ሌላውም መጽሐፍ የወጉትም ያዩታል ስለሚል ነው። ከቀኑ ስድስት ስዓት ያህል ነበር እስከ ዘጠኝ ሰአት ድረስም በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ የፀሓይ ብርሃን ተከልክሎአልና። የቤተ መቅደሱም መጋረጃ ተቀዶ ለሁለት ተከፈል። ኢየሱስም ድምጹን ከፍ አድርጎ “ኤሎሄ!ኤሎሄ!ላማ ሰበቅታኒ?” እያለ ጮኸ ትርጉሙም “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ?” ማለት ነው። ኢየሱስም በታላቅ ድምጽ ጮኸ አባት ሆይ መንፈሴን በእጅህ እሰጣለሁ አለ ይህንንም ብሎ ሞተ።

በእንደገና መወለድ አርቲስት ማይክል አንጄሎ ቡናሮቲ የተሰራው ይህ የጌታችን መድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት መሰረት ያደረገው መጽሐፍ ቅዱሱን ነው።

አሁን የአለም የፍርድ ቀን ነው ። የአለም ንጉስ መከራን ይቀበላል። እኔ ከሞት እነሳለሁ ለአለም ሕዝብ ሁሉ ንስሓና የኅጢአት ስርየት በስሜ ይሰበካል።

ይህን ይመልከቱ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የማይክል አንጄሎ ስራዎች በከፊል