ሶሀባ (sahabah)/አስማ ቢንት አቡበክር(ረ.ዐንሁማ)

ከውክፔዲያ

🎀አስማ ቢንት አቡበክር

ረዲየላሁ ዐንሃ📤

<<ከአክስቴ አዒሻና ከናቴ አስማ የበለጡ ርኀሩኀ ሴቶች እስካሁን አላየሁም>>(አብደላህ ኢብኑ

ዙበይር ረዲደላሁ ዐንሁ)

✍አስማ ቢንት አቡበክር ረዲየላ ሁ ዐንሃ ከተከበረ ሙስሊም ቤተሰ ብ የተገኘች ሴት ስትሆን አባቷ-አ ቡበክር-የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወ ሰለም የልብ ወዳጅና ወራሽ (ኸሊ ፋ)ነበሩ።እህቷ-አዒሻ ረዲየላሁ ዐን ሃ የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሚስትና ከኡሙ ሙእሚኒን (የምእ መናን እናት)አንዷ ነበረች።ባለቤቷ ዙበይር ኢብን አል አዋም ረዲየላሁ ዐንሁ የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰ ለም ልዩ አማካሪዎች ከነበሩት አን ዱ ሲሆን፥ልጇ አብዱላህ ኢብኑ ዙ በይር ረዲየላሁ ዐንሁ ለሐቅ በነበረ ዉ ቀናዒነትና ጥንካሬ እጅግ የታወ ቀ ሰዉ ነበር።

✍አስማ ረዲየላሁ ዐንሃ ኢስላምን ለመጀመሪያ ጊዜ ከተቀበሉት ሙስ ሊሞች ጋር ትመደባለች።ወደ ኢስላ ም በመግባት ወንዶችንና ሴቶችን ጨምሮ አስራ ሰባት ሰዎች ብቻ ና ቸዉ የሚቀድሟት።አስማ ረዲየላሁ ዐንሃ፥የነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰ ለም የመዲና ጉዞ ዕቅድ ሚስጥር በነበራቸዉ ዝግጅት ምክንያት የጉ ዞዉ ሚስጢራዊነት በከፍተኛ ጀረ ጃ የተጠበቀ ነበር።በስንብታቸዉ ምሽት አስማ ረዲየላሁ ዐንሃ በአን ድ አገልግል ምግብና በሁለት ከረ ጢቶች ዉኃ ሞላች።ለከረጢቶቹ መ ቋጠሪያ ገመድ በማጣቷም የወገ ቧን መቀነት (ኒታቅ)ፈታች።አባቷ አ ቡበክርም ረዲየላሁ ዐንሁ ለሁለት እንድትሰነጥቀዉ ነገሯት።ነብዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተግባሯን አደነቁ።በዚህ ምግባሯ ነበር <<ባ ለሁለት መቀነቷ>>(ዛት አን-ኒታቀይ ን)በመባል የታወቀችዉ።

✍የመጨረሻዉ ሂጅራ በነብዩ ሰለ ላሁ ዐለይሂ ወሰለም መካን መልቀ ቅ ከተፈፀመ በኃላ አስማ ረዲየላ ሁ ዐንሃ አረገዘች።እንደሌሎቹ የነ ብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሃባ ዎች ሁሉ፥እርሷም ሆነች ባልተቤቷ ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስ ደት በኃላ በመካ የመኖር ፍላጎት አልነበራቸዉም።እርግዝናዋም ሆነ የመንገዱ እርቀት ሳይበግሯት ወደ መዲና ጉዞ ተነሳች።በመዲና ዳርቻ ላይ ከምትገኝ ቁባ ከምትባል ሥፍ ራ እንደደረሱ ፥አብደላህ የተባለ ወ ንድ ልጅ ወለጀች።የልጁ መወለድ ታራካዊነት ስለነበረዉ በሙስሊሞ ች ዘንድ በተክቢራና ተህሊል የገለ ፁትን ደስታ ፈጠረ።

✍አስማ በመልካም ሥነ-ምግባሯ ና በልበ ብርሃንነቷን በዘመኑ የታወ ቀች ሴት ነበረች።ርኀራኄዋን በተ መለከተ ልጇ አብዱላህ በአንድ ወ ቅት እንዲህ ሲል የአማኝነት ቃሉን ለግሷል።<<ከአክስቴ ከአዒሻና ከእ ናቴ ከአስማ የበለጡ ርኀሩኀ ሴቶች እስከአሁን ድረስ አላደሁም።የሁለ ቱ ሴቶች ርኀራሄ የተለያየ ገጽታ ነበ ረዉ።አክስቴ በቂ የመሰላትን ያህ ል ማጠራቀሟን ካረጋገጠች በኃላ ለችግረኞቹ ታከፋፍለዋለች።እናቴ በ በኩሏ ለነገ የሚል ሐሳብ የላትም። እጇ ላይ የገባዉን ሁሉ ወዲያዉኑ ለተቸገረ ትለግሳለች።>>


✍የአስማ ረዲየላሁ ዐንሃ ልባምነ ት እጅግ የሚደንቅ ነዉ።ለቤተሰባ ቸዉ አንዳች ነገር ላይተዉ ስድስት ሺህ ዲርሃም የሚቀልጥ ንብረታቸ ዉን ጠራርገዉ ነበር ወደ መዲና የ ተጓዙት።በዚያን ጊዜ ሙሽሪክ የነበ ሩት የአቡበከር አባት አቡ ቁሓፋህ የልጃቸዉን ወደ መዲና መጓዝ እን ደሰሙ ቤታቸዉ ድረስ በመሄድ ለአ ስማ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ አሏት፦

<<ካለ ገንዘብ ትቶሽ እንደሄደ እር ግጠኛ ነኝ።>>አስማም ረዲየላሁ ዐንሃ <<አይደለም፥አያቴ ሆይ፥(አባ ቴ)በቂ ገንዘብ ትቶልን ነዉ የሄደዉ ።>> ስትል መለሰችላቸዉ።ጥቂት ገንዘብ መሰል ጠጠሮችን በገንዘ ብ ማስቀመጫ ትንሽ ሳጥን ዉስ ጥ አኖረቻቸዉ።በጨርቅ ከሸፈነቻ ቸዉ በኃላ አይነ ስዉሩ አያቷ በእጃ ቸዉ እንዲሳስሱት በማድረግ <<አ የህ!ምን ያህል ገንዘብ አባቴ ትቶል ን እንደሄደ>> አለቻቸዉ።

✍አስማ ረዲየላሁ ወንሃ ይህንን ስልት የተጠቀመችዉ ሙሽሪኩ አ ያቷ ገንዘብ የላቸዉም በሚል ከኔ ዉሰዱ እንዳይሉ በመስጋቷ ሲሆን ከርሳቸዉ መዉሰዱን የጠላችበት ምክንያትም ምንም እንኳን አያቷ ቢሆኑ ከሙሽሪክ (አጋሪ)ሰዉ እርዳ ታ መቀበል ኢስላማዊ ሰብዕናዋን እንደማዋረድ ስለቆጠረችዉ ነዉ።

✍አስማ ረዲደላሁ ዐንሃ በእናቷ ም ላይ ተመሳሳይ አቋም ነበራት። ክብሯን እና ኢማኗን ለድርድር የማ ቅረብ ዝንባሌ በጭራሽ አልታየባት ም።በቅድመ ኢስላም ከአባቷ ጋር የተፋታችዉ እናቷ ቀቲለህ አንድ ወ ቅት በመዲና ሳለች ልትጎበኛት መ ጣች።ኢስላምን ያልተቀበለችዉ እና ቷ ወደርሷ ስትመጣ ደረቅ ኮምጣ ጤ፣የተጣራ ቅቤ...ይዛላት ነበር።አ ስማ ረዲደየላሁ ዐንሃ አስቀድማ ለ እናቷ የመግባት ፍቃድ አልሰጠች ም፥ያመጣችዉን ስጦታም አልተቀ በለችም።አንድ ሰዉ ወደ አዒሻህ ረ ዲየላሁ ዐንሃ በመላክ መዉሰድ ስ ለሚገባት ርምጃ ከነብዩ ሰለላሁ ዐ ለይሂ ወሰለም ጠይቆ እንዲመጣ አደረገች።ነብዩም ሰለላለሁ ዐለይ ሂ ወሰለም እናቷን ወደቤት እንድታ ስገባ፥ስጦታዋንም እንድትቀበል አ ዘዟት።በዚህን ጊዜም የሚከተለዉን የቁርኣን አንቀፅ ተደነገገ።

  1. ከነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏች

ሁ፥ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋች ሁ (ከሓዲዎች)፥መልካም ብትዉሉ ላቸዉና ወደነርሱ ብታስተካክሉ አላ ህ አይከለክላችሁም፤አላህ ትክክለ ኞችን ይወዳልና።አላህ የሚከለክላ ችሁ፥ከነዚያ ከሃይማኖት ከተጋደሉ ዋችሁ፥ከቤቶቻችሁም ካወጡዋች ሁ፥እናንተንም በማዉጣት ላይ ከ ረዱት (ከሓዲዎች)፥እንዳትወዳጁ ዋቸዉ ብቻ ነዉ።>>[አል ሙምተ ሒናህ፡8-9)

✍ለአስማም ረዲየላሁ ዐንሃ ሆነ ለበርካታ ሙስሊሞች የመጀመሪያ ዉ የመዲና ኑሮ ቀላል አልነበረም። ባሏ ችግረኛ ነበር።ቀደም ሲል ከገ ዛዉ ፈረስ በስተቀር አንዳችም ሀብ ት አልነበረዉም።ያንን ጊዜ አስማ ረ ዲየላሁ ዐንሃ እንደሚከተለዉ ትገ ልፀዋለች፦ <<ለፈረሱ ድርቆሽና ዉ ሃ ከሰጠሁ በኃላ የሰዉነቱንም ጽዳ ት እጠብቅለታለሁ።ዱቄት ፈጭቼ ም እጋግራለሀ።ግና ጋግሬም የተ ዋጣ ስለማይሆንልኝ ብዙዉን ጊዜ የአንሷር ሴቶች ይጋግሩልኛል።በጣ ም ጥሩ ሴቶች ነበሩ።ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለዙበይር ረዲየላ ሁ ዐንሁ እንዲያደርሰዉ ከወሰኑለ ት መሬት ላይም እህል በራሴ ተሸ ክሜ እመጣለሁ።ይህ የእርሻ ቦታ ከከተማ ወደ ፈርሰኽ (18 ኪ•ሜ ያህል ይርቃል)።>>

✍አስማ ረዲየላሁ ዐንሃ እጅግ ጥ ንቁቅና ታታሪ ሴት ነበረች።ችግራቸ ዉ ቀስ በቀስ እስኪወገድላቸዉ ድ ረስም ከባሏ ጋር ጠንክረዉ ሰሩ።ዙ በይር ረዲየላሁ ዐንሁ ቀስ በቀስ ከ ሶሃባዎች ሁሉ እጅግ የታወቀ ባለፀ ጋ ሆነ።ሀብት ማግኘታቸዉ አስማን ረዱየላሁ ዐንሃ ቅጥያጣ ኑሮ እንድ ትከተል አላረደጋትም።እንደወትሮ ዋ ሁሉ በኢማኗ ላይ የፀናች ሴት ነ በረች።አንድ ወቅት ልጇ ሙንዚር ዋጋዉ ዉድ ከሆነ ክር የተሰራ ድን ቅ ቀሚስ ከኢራቅ ላከሊት።በጊዜ ዉ አይነ ሥዉር የነበረችዉ አስማ ረዲየላሁ ዐንሃ ቀሚሱን ዳብሳ ድን ቅነቱን በተረዳች ጊዜ ከፍተኛ ሐዘን ተሰማት፤ለመልእክተኛዉም ሰለላ ሁ ዐለይሂ ወሰለም <<ይህ ለኔ የ ሚገባ አይደለምና ወደርሱ መልስ ለት።>> ስትል አዘዘችዉ።ሙንዚር በሁኔታዉ ተበሳጭቶ <<እማማ፥ሰ ዉነትን የሚያሳይ ቀሚስ አይደለም ።>>ሲል ገለፀላት።

✍እርሷንም በቁጣ <<የሰዉነትን መልክ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል፥ነ ገር ግን ጠባብ ስለሆነ የሰዉነትን ቅርፅ ያሳያል።>> ስትል መለሰችለ ት አልሙንዚር የእናቱን አለመስማ ማት እንዳረጋገጠ ከእርሷ ፈቃድ ጋ ር የሚሄድ ሌላ ቀሚስ ገዛላት።

✍የአስማን ረዲየላሁ ዐንሃ የኢማ ን ጥንካሬ የሚያሳይ ከላይ የጠቀ ስነዉ ገጠመኟ በቀላሉ ሊረሳ ይች ል ይሆናል።ነገር ግን ከልጇ ከአብ ደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ ጋር ለመጨ ረሻ ጊዜ በተገናኙበት ወቅት ያሳየ ችዉ ጥልቅ አስተዋይነት፣ታጋሽነት ና የኢማን ጥንካሬ ከቀደምት ሙስ ሊሞች ታሪክ ዉስጥ የሚዘነጉ አይ ደሉም።

✍ከየዚድ ኢብን ሙዓዉያህ ሞት በኃላ የኸሊፋዉን ቢሮ የመራዉ አ ብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ ነበር።የሂ ጃዝ፣የምስር (ግብፅ)፣የኢራቅ፣የኹ ራሳን አብዛኛዉ የሶሪያ ህዝብ የር ሱ አፍቃሪ ስለነበሩ የኸሊፋነት ስል ጣኑ ለእርሱ እንዲረጋ ወሰኑ።ነገር ግን በኑ ኡመያዎች ድርጊቱን በመ ቃወምና ኸሊፋዉን በመንቀፍ አል-ሃጃጅ ኢብን ዩሱፍ በተባለዉ ሰዉ የሚመራ ትልቅ ሰራዊት አንቀሳቀ ሱ።በሁለቱም ወገኖች መካከል ጠ ንካራ ዉጊያ ተደረገ።በዚህም ፍል ሚያ አብዱላህ ኢብን ዙበይር ረዲ የላሁ ዐንሁ ብዙ የጀግንነት ተግባ ራትን አሳየ።ነገር ግን አብዛኞቹ አጋ ሮቹ የጦርነቱን ፈታኝነት መቋቋም ስለተሳናቸዉ ጥለዉት ሸሹ።በመ ጨረሻ እሱም ዉጊያዉን ትቶ መካ በሚገኘዉ ቅዱስ መስጊድ ለጥገ ኝነት ገባ።


✍ በዚያን ጊዜ ነበር እርጅና ተጭ ኗት አይነ ሥዉር የሆነች እናቱን ለ መጎብኘት ወደ አስማ ረዲየላሁ ዐ ንሁ ዘንድ የሄደዉ።ከዚያም እንደደ ረሰ፦ <<እማማ፥የአላህ ሰለም ርኀ ራሄና በረከት በአንቺ ላይ ይሀን>>( አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ)አላት።እርሷም <<በአ ንተም ላይ ሰላም ይሁን (ወአለይኩ ሙስሰላም)፥አብዱላህ ረዲየላሁ ዐንሁ>>ስትል መለሰችለት።፡<<የሃ ጃጅ ጦር ሃረም በሚገኘዉ ሠራዊ ትህ ላይ መዓት በሚያዘንበብትና የመካ ቤቶች በሚንቀጠቀጡበት በዚህ ቀዉጢ ሰዓት ወደዚህ ምን አመጣህ?>> ስትልም ጠየቀችዉ ።እርሱም <<ምክርሽን ፍለጋ መጣ ሁ ኡማ (እማየ)>>በማለት ለጥያቄ ዋ ምላሽ ሰጠ።

🔺 እርሷም በመደነቅ <<የኔን ም ክር ፍለጋ?ስለምንድነዉ የምመክ ርህ አብዱላህ ረዲየላሁ ዐንሁ?>> በማለት ጠየቀችዉ።


•<<ከጎኔ ተሰልፎ የነበረዉ ሕዝብ አብዛኛዉ ሃጃጅን በመፍራት ወይ ም በሚሰጠዉ ወሮታ በመጭበር በር ጥሎኝ ሸሸ።ልጆቼና መላዉ ቤ ተሰቤ እንኳን ከእኔ ተገለሉ።አብረ ዉኝ የቀሩት በጣም ትንሽ ሰዎች ሲሆኑ፥እነርሱም ምንም ያህል ጠካራና ቆራጥ ቢሆኑም የጠላትን ኃይል ሊቋቋሙ የሚችሉት ለአንድ ሰዓት ግፋ ቢል ለሀለት ሰዓት ያህ ል ነዉ።በኑ ኡመያዎች ከኔ ጋር ለ መደራደር መልእክተኞቻቸዉን ልከ ዋል።የምሻዉን አለማዊ ፀጋ (አዱን ያ)ሁሉ ሊሰጡኝ ፈቃደኛ መሆናቸ ዉንም ገልጸዉልኛል።ነገር ግን ለዚ ህ ዉለታቸዉ ጦሬን ላስቀምጥና ከአብዱል መሊክ ኢብን መርዋን ጋር የትብብር ቃል እንድገባ መስማማት አለብኝ።ታዲያ ስለዚህ ጉ ዳይ ምን ታስቢያለሽ?>>

  1. ድምጿን ከፍ በማድረግ፥ <<አብ

ዱላህ ይህ የአንተ ጉዳይ ነዉ፣ማን ነትህን ጠንቅቀህ የምታዉቅ ሰዉ ነህ።ትክክለኛና ለእዉነት የቆምኩ ነኝ ብለህ ካሰ ብክ፥ በባንዲራህ ስ ር በቆራጥነት ሲዋጉ እንደተገደሉ ት ጓደኞችህ ሁሉ በፅናትና በቆራ ጥነት ዉጊያህን ቀጥል።ይህን ትተ ህ አዱንያን ከመረጥክም ምንኛ አ ሳዛኝ ሰዉ ነህ! እራስህንም ሆነ ሰ ዎችህን እንደምታጠፋ ልብ በል። >>ስትል ምክሯን ለገሰችዉ።

•<<ግን እማየ እንደዚያ ካደረግሁ፥ ዛሬ ሟች ነኝ፣ምንም ጥርጥር የለዉም።>>

  1. ለሃጃጅ በፈቃደኝነት እጅህን ሰጥ

ተህ የበኑ ኡመያ አጫፋሪዎች መ ጫወቻ ከምትሆን፥የጀግንነት ሞት ለአንተ እጅጉን በላጭ ነዉ።>>

•<<ሞቴን አልፈራሁም፤የኔ ፍርሃት ሥጋዬን ይበጣጥቁታል ብዬ ነዉ።>>

  1. <<የሰዉ ልጅ ከሞቱ በኃላ በአካ

ሉ ላይ ስለሚፈፀመዉ ድርጊት ም ንም የሚያስፈራዉ ነገር የለም።የቆ ዳዉ መገፈፍ ምንም የሚያመጣ ዉ ህመም አይኖርም።>>አለችዉ።

✍አብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ ልብ የሚያጠነክረዉን የእናቱን ምክር እ ንደሰማ የሚከተለዉን እየተናገረ ፊ ቱ አንፀባረቀ።

  1. <<ምኝኛ የተባረክሽ እናት ነሽ(መ

ልካሙ ባህሪይሽ የተባረከ ይሁን)በ ዚህ ቀዉጢ ሰዓት ወደአንቺ የመ ጣሁት በጆሮዬ ያንቆረ ቆርሽዉን ምክር ለመስማት ነበር።እንዳልደከ ምኩና ተስፋ እንዳልቆጠረጥኩ አ ላህ ያዉቅልኛል።ለአዱኛ ፍቅር እን ዳልተሰለፍኩም በኔ ላይ ምስክሬ ነ ዉ።ገደብ የለሽ ቁጣየ የአላህ ሕግ በመጣሱ ነዉ።እናቴ! አንቺን ደስ ወደሚያሰኝሽ ለመሄድ እነሆ ዝግ ጁ ነኝ።ብሞት አትዘኝብኝ፤በፀሎት ሽ ብቻ አስታዉሽኝ።>>

•ቆራጧ አሮጊት አስማ ረዲየላሁ ዐ ንሁ <<ልጄ!የማዝንብህ ለማይረባ ዓላማ ተሰልፈህ ብትሞት ነዉ።>> አለችዉ።

  1. <<እርግጠኛ ሁኚ እማየ ልጅሽ ህገወጥ ዓላማን አልደገፈም።ፀያ

ፍ የሆነ ተግባርም አልከወነም። ሙስሊሞችንም ሆነ ሙስሊም ያል ሆኑ ዜጎች ፍትህ አላጓደለም።ለር ሱ ከኃያሉ ጌታ ዉዴታ የበለጠ አን ዳችም ነገር የለም።ይህን ያልኩት ንፅህናዬን በመግለፅ ለመመጻደቅ ሳይሆን ልብሽን ለማጠናከር ብቻ እ ንደተናገርኩ አላህ ያዉቅልኛል>>አ ላት።

<<አላህ ሱብሃን ወተአላህ ለሚወ ደዉና እኔም የምመኝልህን እንድት ፈፅም ስለረዳህ ምስጋና ይግባዉ! ና ልጄ ግንኙነቻችን የመጨረሻ ሊ ሆን ይችላልና እስኪ ሰዉነትህን ላ ሽትተዉ፥ልዳስሰዉም።>> አለችዉ ና ከፊቷ ተንበ ረከከ።ወደ እርሷ አስ ጠጋችዉ፤ አንገቱን ፥ፊቱንና እራሱን በእናትነት ስሜት ተዉጣ እየዳበሰ ች ሳመችዉ።ጣቶቿ ሰዉነቱን መ ጭመቃቸዉን ቀጠሉ።በድንገት እ ጇን ከሰዉነቱ አላቃ፦ <<ይህ የለበ ስከዉ ምንድን ነዉ? >>አለችዉ።< <የጦር ልብስ ነዉ>>አላት።<<ይህ ፥ሰማዕታትን የሚከጅል ሰዉ የሚ ለብሰዉ ልብስ አይደለም።አዉልቀ ዉ፥እንቅስቃሴህን ይበልጥ ቀላልና ቀልጣፋ ያደርግ ልሃል።በዚህ ምት ክ ሱሪ ልበስ።ብትገደልም ሃፍረተ ሥጋህ አይጋለጥም>>አለችዉ።

✍አብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ የጦ ር ልብሱን አዉልቆ ሱሪ አጠለቀ።ፍ ልሚያዉን ለመቀላቀል <<ሐረም> >ሲለቅ፦ <<እናቴ ሆይ!ዱዓሽ አይለ የኝ>> አላት።

✍እጇን ወደ ሰማይ ዘርግታ ዱዓ አደረገች፦ <<ጌታዬ ሆይ!...ለአባቱ ና ለእናቱ የእርሱን መልካም ሰሪነት ባርክላቸዉ።እርሱን ለአንተ ጉዳይ አበርክቻለሁ።ለእርሱ የወሰንክለት ነገር ያስተስተኛል።ለኔም ጽኑና ታጋ ሽ የሆኑ ሰዎችን ምንዳ ለግሰኝ።>>

🌹ፀሐይ ስትጠልቅ አብደላል ረዲ የላሁ ዐንሁ ለዘልዓለም አንቀላፍቶ ነበር።ልክ ከአሥር ቀናት በኃላ እና ቱን ተከተለችዉ።የመቶ ዓመታት እ ድሜ ባለፀጋ ነበረች።እድሜ የአላ ማ ጽናቷን አልዘረፋትም፤የአእምሮ ብሩህነቷን አላደበዘዘዉም።

ተጠናቀቀ!!