Jump to content

ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ ገብረ ማርያም

ከውክፔዲያ

በአዲስ አበባ ከተማ በ፲፱፲፱ ዓ.ም. የተወለዱት ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ የቄስ ትምህርትን ከማይጨው ዘመቻ በፊት አጠናቅቀዋል፡፡ በጣሊያን የወረራ ወቅት በኢጣልያን ትምህርት ቤት ገብተው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በ፲፱፴፭ ዓ.ም. በጦር ሠራዊት ውስጥ ወታደርነት በመግባት ወታደራዊ ትምህርት ተምረዋል፡፡


ከዚያም በ፲፱፴፯ ዓ.ም. ሐምሌ 10 ቀን በክብር ዘበኛ መድፈኛ ክፍል የከፍተኛ ቴክኒክ ት/ቤት ገብተው የአምስት ዓመታት ኮርስ ተከታትለዋል፡፡ በመድፈኛ መኮንንነት ደረጃ ተመርቀዋል፡፡ እስከ ሻምበልነት ማዕረግ ደርሰው የነበሩት ሻምበል አፈወርቅ በ፲፱፶፫ ዓ.ም. የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ ተካፋይ ሆነዋል በመባል ለሦስት ዓመታት በእስራትና በግዞት ቆይተዋል፡፡ ከ፲፱፶፮ ዓ.ም. ጀምሮ በሬዲዮ ጋዜጠኝነት አገልግለዋል፡፡


ሻምበል አፈወርቅ በ፲፱፶፯ ዓ.ም. ግጥሞች፣ ለዘፈን ለትካዜ፣ ለደስታ እና ልዩ ልዩ ታሪኮች በሚል የሥነ ግጥም መጽሐፍ፤ በ፲፱፶፯ ዓ.ም. ችግረኞች በሚል ርዕስ ከዓለም ታላላቅ ድርሰቶች ተጠቃሽ የሆነውን ልብወለድ መጽሐፍ ተርጉመው አሳትመዋል፡፡ የኔ ግጥሞች፣ የዓለም አስደናቂ ልዩ ልዩ ታሪኮች፣ ፍቅር በሰዎች ዘንድ፣ የሞራል ግዴታ ስሜታዊ ግጥሞችንም አሳትመው አልፈዋል፡፡

የደራሲው ሥራዎች
 ችግረኞች(ትምህርት)
 ግጥሞች፣ ለዘፈን ለትካዜ፣ ለደስታ እና ልዩ ልዩ ታሪኮች (ግጥምና ቅኔ)
 የኔ ግጥሞች(ግጥምና ቅኔ)
 የዓለም አስደናቂ ልዩ ልዩ ታሪኮች(ታሪክ)
 ፍቅር በሰዎች ዘንድ(ምርምር)
 የሞራል ግዴታ (ትምህርት)
 ስሜታዊ ግጥሞች(ግጥምና ቅኔ)
 እውነት አትሞትም(ተውኔት)


ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ

ተጨማሪ እትመት

ሀዘን እና ደስታ (ታላላቅ የአለም አጫጭር ታሪኮች ትርጉም)[1]