Jump to content

ሻውሃው

ከውክፔዲያ

ሻውሃው (ቻይንኛ፦ 少昊) በቻይና ጥንታዊ ታሪክ ዘንድ የቻይና ንጉሥ ኋንግ ዲ ልጅና ተከታይ ነበረ። በሻውሃው መንግሥት ዋና ከተማው ከዥዎሉ ወደ ጩፉ ተዛወረ። መቃብሩ እስከ ዛሬ ድረስ በጩፉ እንደ ሆነ ይታመናል። በአንዳንድ ታሪክ ቻይናን የነገሠ 84 ዓመት እንደ ነበር ሲባል በሌላ ታሪክ ዙፋኑ ቀጥታ ከኋንግ ዲ ወደ ዧንሡ ተዛወረና ሻውሃው አልነገሠም። የቀርከሃ ዜና መዋዕል የተባለው መዝገብ እንደሚለው ሻውሃው ምናልባት ንጉሥ ከቶ አልነበረም፣ 7 አመት ኋንግ ዲ ካረፈ በኋላ ግን (በ2283 ዓክልበ ግድም) ሚኒስትሩ ጻንግችየ የቻንግዪ ልጅ ዟንሡን ወደ ዙፋኑ አስነሣው።

ስለ ሻውሃው ብዙ ተጨማሪ ግሩም አፈ ታሪኮች አሉ፤ ለምሳሌ በአዕዋፍ ላይ እንደ ነገሠ፣ ሚኒስትሮቹም አዕዋፍ እንደ ነበሩ የሚል ወሬ አለ።

ቀዳሚው
ኋንግ ዲ
ቻይና ንጉሥ ተከታይ
ዧንሡ