ሽክርክርና ዘንግ

ከውክፔዲያ
ውሃ ለመቅዳት የሚያስችል ሽክርክርና ምሰሶ

ሽክርክር እና ምሰሶ ከስድስቱ ቀላል ማሽን አንዱ ነው። ቀላል ሽክርክር እና ምሰሶ አንድ ሽክርክርና ከርሱ ጋር በጥብቅ የተገናኘ ምሰሶ ይኖረዋል። በዚህ ሁኔታ ትልቁን ሽክርክር በመጠቀም ከፍተኛ ቶርክ ወይም ጉልበት በትንሽየ ጉልበት መፍጠር ስንችል (ይሄ እንግዲህ ውሃ ለመቅዳትና ከባድ ነገሮችን ለማንቀሳቀስ ይጠቅመናል)፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ ምሶሶውን በመጠቀም በአንስተኛ እንቅስቃሴ (ከፍተና ጉልበት)፣ ብዙ እንቅስቃሴን ከትልቁ ሽክርክር እናገኛለን (ምሳሌ፡ የብስክሌት ፔዳል)።

ስሌዚህ እንደምናዞረው ሽክርክር፣ አንድ ጊዜ ፍጥነትን ለማብዛት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጉልበትን ለማብዛት ይጠቅመናል ማለት ነው። ሁለቱን በአንድ ላይ ማድረግ ግን በተፈጥሮ ህግ ክልክል ነው።