ቀበጧ እመቤት

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ቀበጧ እመቤት

እመቤቲቱ የባለቤታቸው ጦር ሜዳ መቆየት አላስችል ይላቸውና ከአንዱ ባሪያቸው ጋር ይቀብጣሉ። እንዳይደርስ የለም ባል ሳይጠበቁ ከች ይላሉ። ሚስጥራቸው እንዳይወጣ ያሰቡት ሚስትም ስራተኛቸውን ባፋጣኝ ወደባሪያቸው እንዲህ ብለው ይልካሉ፤"ባለፈው የተፈጠረውን ነገር ለማንም እንዳትናገር"። ሰራተኛይቱም ብዙ ስዎች ይሰሩበት ወደ ነበረ እርሻ ሄዳ አፋፉ ላይ ትቆምና ስሙን ጠርታ፤"እመቤቴ የባለፈውን ነገር ለማንም እንዳትናገር ብለውሃል" ትለዋለች። እሱም መለስ ያደርግና "ምንም ችግር የለም እኔ ምኔ ሞኝ ነው እመቤቴን አወጣሁ ብዬ የማወራው" ብሏት እርፍ። ተፈጸመ