ቀጋ

ከውክፔዲያ
የቀጋ ፍሬዎችና ተክሉ
የቀጋ ፍራፍሬ ውጤት ከጎንጅ ቆላላ ወረዳ

ቀጋ (Rosa abyssinica) በኢትዮጵያ ብቻ የሚበቅል የአፍሪካ ብቸኛ ጽጌረዳ ነው። ከቀጋ ውጭ ያሉት ጽጌረዶች በሙሉ ከሌላም አለም አሉ።

የቀጋ ጥቅም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የዛፉ ፍሬ ሲበስል ከላይ ያለው ቆዳው ቢጥምም ውስጡ የማይቆረጠም ፍሬወች ያለው ተክል ነው። ፍሬው እጅግ ብዙ ቨታሚን አለው። ለህጻናት በተለይ ጥሩ ነው።

የዛፉ ቅጠል ገምቦ፣ ጋንና የመሳሰሉትን እቃወች ለማጠን ያገለግላል።[1]

ፍሬውም የኮሶ ትልና ድቡልቡልን ትል ለማስወጣት ጥሩ ነው።[2] እንዲሁም ለሆድ ቁርጠት መጠቀሙ ተዘግቧል።[3]

ለቀጋ ተስማሚ የሆነ አየር ጠባይና መሬት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ፀሐያማ ሆኖ ጥላ ያለበት ቦታ ይመርጣል። አሸዋማ ወይንም መካከለኛ ለም አፈር ይወዳል። ከደረቅ እስከ መካከለኛ እርጥብ መሬት ተክሉ ይፈልጋል።

የቀጋ አስተዳደግና እንክብካቤ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ተጨማሪ ንባብ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ http://www.lrrd.org/lrrd21/7/ayen21097.htm
  2. ^ አማረ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
  3. ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች