ቀጥቃጭ

ከውክፔዲያ

ኢትዮጵያን ባህላዊ የብረትነሓስ እቃዎች እንዴት እንደሚሰሩ የሚያውቅና በተግባርም የሚተረጉም ምሁር ቀጥቃጭ ይባላል። ግን ያን የሚያደርጉና ይህን የመሰለ የጅ ጥበብ ያላቸው እነኚህ ባለሙያዎች በህብረተሰቡ ዘንድ የተናቁና የተገፉ ናቸው ይህ ደግሞ ከጥንት ጀምሮ የመጣ ነው የሚገርመው ነገር አሁንም ድረስ እነዚህ ወርቅ እጅ ያላቸው ማህበረሰቦችን በተለያየ መንገድ በተለያየ ስያሜ ይጠሯቸዋል በተለይ በጉራጌ ክልል ውስጥ እነዚህ ጥበበኞችን (ነፉረ )እያሉ ነው የሚጠሯቸው ይህ ማለትም ብረት ቀጥቃጭን ቡዳ ከሰው የማይቀላቀል ይሉቱል ባጠቃላይ የጎነ ሰብ እያሉ ይጠሩታል ይሄ ማለት ደግሞ በሀገሩ ላይ መብት የሌለው እና የተገፋ ነው ማለት ነይ እኔ ከሁሉም የሚገርመኝ ደግም እነሱ በሰሩት ቢላዋ አርደው ከትፈው እየበሉ እነሱ በሰሩት ምጣድ ቆልተው ጋግረው እየበሉ እነሱ በሰሩት ድስት ሰርተው አብስለው እየበሉ ይሏቸዋል የተናቁ ታድያ ምን ይሉታል ጥበበኛውን ንቆ ጥበቡን ማድነቅ በጃቸው ጥበብ በተሰራ መሳርያ እየተጠቀሙ እነሱን መግፋት ታድያ እስኪ ፍረድ ይሄ ምን የሚሉት ነገር ነው ይህ ማለት ልጅን ወዶ እናትን መጥላት ነው ለኔ ወገኔ ንቃ ይሄኮ ጥበብ ነው ይሄኮ እድገት ነው ይሄ ማለት ባደጉት ሀገራት የተከበረ ስራ ነው ታድያ ለምን እኛ እርስ በርሳችን ያንተ ዘር ይሄ የኔ ደግሞ ይሄ እያልን ያንተጎሳ የዘቀጠ የኔ ደግሞ ከፍ ያል እየተባባልን እስከመቼ እንኖራለን እኛ ሁላችንም ያዳም እና የሄዋን ዘሮች ነን ስለዚህ ጥንት አባቶቻችን ባለመማርና በለማወቅ በፈጠሩት አፈታሪ እኛም ተተብትበንበታል ወገኔ ንቃ ይሄ ሙያ ነው !!!!!!!!!!!!