ቁስጥንጥንያ ጉባኤ
Appearance
ጉባኤ ቁስጥንጥንያ በዛሬዋ ግሪክ ውስጥ የተካሄደ ጉባኤ ነው ጉባኤው የተካሄደበት ዋነኛ ዓላማ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ሕጹጽ ብሎ የኑፋቄ ትምህርትን ሲያስተምር የነበረውን መቅዶንዮስን ለማውገዝ እና ተጨማሪ ሌሎች አምስት አንቀጸ ሃይማኖትን ለማርቀቅ ነው ጉባኤው በ150 ሊቃውንት የተደረገ ጉባኤ ነው ከ150 ሊቃውንት መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ አውሳብዮስ ከመቅዶዮስ ጋር የመከራከርያ ነጥብ አንስቶ ክርክር ገጠመው የመከራከርያ ሃሳቡም ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፮፣፫ ላይ የተፃፈው ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር የሚለው ቃል ነበር ቃሉ ፫ ጊዜ መደገሙ ሶስትነታቸውን ቃሉ አለመለወጡ አንድነታቸውን ይገልፃል እና የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 28፣19 እና 20 ላይ የተፃፈው ስልጣን ሁሉ በሰማይ እና በምድር ተሰጠኝ እነሆ ሂዱና አህዛብን በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃቹኃቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው ያዘዝኩኃችሁን እንዲጠብቁ አድርጓቸው በዚህም መንፈስ ቅዱስ አምላክ ባይሆን ኖሮ በአብ እና በወልድ ስም አጥሙቋቸው ተብሎ በተፃፈ ነበር ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ከአብ እና ከወልድ ባልተናነሰ መልኩ የባህርይ ገዥ እና አምላክ ነው