Jump to content

የቂሪሎስ አልፋቤት

ከውክፔዲያ
(ከቂርሊክ አልፋቤት የተዛወረ)

የቂርሎስ አልፋቤት በተለይ ስላቪክ ቋንቋዎችን ለመጻፍ የተደረጀ ጽሕፈት አይነት ነው። በተለይ ሩስኛዩክሬንኛቤላሩስኛቡልጋርኛሰርብኛ ወዘተ. ይጻፉበታል።

855 ዓም ቅዱስ ቂርሎስቅዱስ ሜቶዲዮስ ወደ ስላቮች በተላኩበት ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ወዘተ. በስላቭኛ ለመጻፍ ግላጎሊቲክ አልፋቤት የተባለውን ጽሕፈት ፈጠሩ። ይህም በስላቫዊ ብሔሮች ቶሎ ይስፋፋ ጀመር። በዚህ ግላጎሊቲክ ጽሕፈት ውስጥ፣ አብዛኞቹ ፊደላት የግሪክ አልፋቤት ተደረጁ፣ በግሪክኛ ለማይገኙት ድምጾች ግን አንዳንዱ ከዕብራይስጥ፣ አንዱም ከቅብጥኛ እንደ ተበደረ ይመስላል።

የቀድሞ ቂርሎስ አልፋቤት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከዚህ ትንሽ በኋላ በ878 ዓም ክርስቲያናዊው የፕረስላቭ ስነ-ጽሑፍ ትምህርት ቤትቡልጋሪያ ተመሠረተ። በዚህ ተቋም ከ885 ዓም ለስላቭኛ ከግላጎሊቲክ የተሻለ የተቀለለ ጽሕፈት፣ የቀድሞው ቂርሎስ አልፋቤት ተፈጠረ። በዚህ ጽሕፈት ፊደሎቹ ከግላጎሊቲክ ይልቅ እንደ ግሪኮቹ ፊደላት ይመሳሰሉ ነበር። በግሪክኛ ለማይገኙት ድምጾች አንዳንድ ግን ከግላጎሊቲክ ተወሰደ። ይህም የቀድሞው ቂርሎስ አልፋቤት በየጥቂቱ በስላቫዊ ብሔሮች መሃል የግላጎሊቲክ አልፋቤትን ፈንታ ተካ።

የቀድሞ ቂርሎስ አልፋቤት፣ 885 ዓም. ግድም (40 ፊደላት) (* = ለግሪክ ወይም ለባዕድ ቃላት ካልሆነ በቀር ብዙ አልታዩም)
ፊደላት а б в г д е ж ѕ и і к л м н о п р с т оу ф* х ѡ* ц ч ш щ ъ ь ѣ ю ѫ ѭ ѧ ѯ* ѱ* ѳ* ѵ*
ድምጽ ድዝ ሽት ኢው ኦኝ ዮኝ ኧኝ ክስ ፕስ ኢው

ከዚህ ትንሽ በኋላ ሌሎች የቀድሞ ፊደላት /ያ/፣ ѥ /የ/፣ ѩ /የኝ/ ተጨምረው ነበር።

ዘመናዊ ቂርሎስ አልፋቤት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከጊዜ ወደ ጊዜ የድሮ ቂርሎስ አልፋቤት ለየቋንቋው ተለወጠ፤ በተለይም የሩስያ ጻር ታላቁ ፕዮትር1700 ዓም አንዳንድ ለውጥ አስገባ።

ዘመናዊ ቂርሎስ ፊደላት ከ1700 ዓም. በኋላ
ፊደላት а б в г д е ё ж з и й к л м н о п р с т у ф х ц ч ш щ ъ ь э ю я
ድምጽ ሽች

ከነዚህ ጋራ ተራ ፊደላት በላይ፣ እያንዳንዱ ቋንቋ ለራሱ ተጨማሪ ልዩ ፊደሎች አሉት። ለምሳሌ፣ በዩክሬንኛ አልፋቤት «г» የሚለው ፊደል ለ/ሕ/ ያሰማል፣ ሌላውም ቅርጽ «Ґ» ለ/ግ/ ያገልግላል።

ሌሎችም ስላቫዊ ያልሆኑት ልሳናት በተለይም ሞንጎላዊ፣ ቱርኪክ ቋንቋዎች ወይም ሳይቤራዊ ቋንቋዎች ደግሞ በቂርሎስ ጽሕፈት ይጻፋሉ፣ ወይም ቀድሞ በቂርሎስ ጽሕፈት ተጽፈው ነበር።