ቅብብል
Appearance
የአስረካቢ ቅብብል ከሁለት ወይንም ከዚያ በላይ አስረካቢዎች የተሰራ ሲሆን፣ የአንዱ አስረካቢ ውጤት ለሌላኛው አስረካቢ እንደ ግቤት የሚያገለግልበት ስርዓት ነው። አስረካቢ ƒ: X → Y እና g: Y → Z እንዲህ ሲደረግ ሊቀባበሉ ይችላሉ፣ መጀመሪያ አስረካቢ ƒ ግቤት x ን ወስዶ ለውጤት y = ƒ(x) ያስረክባል፣ ከዚያ አስረካቢ g ይህን ውጤት y ወስዶ ለውጤት z = g(y) ያስረክባል። በዚህ መልኩ የተሰራ ቅብብል አስረካቢ በሒሳብ ቋንቋ እንዲህ ይጻፋል
ወይን በቀላሉ ሲጻፍ
- ፣ ሲነበብ ከƒ ለg የሚያቀብል አስረካቢ።
የቅብብሉ ቅደም ተከተል ወሳኝ ነው፣ ምክንያቱም ከ ƒ ለg ማቀበልና ከg ለƒ ማቀበል ብዙ ጊዜ የተለያዩ ግቤቶችንና ውጤቶችን ያመጣሉና። ለምሳሌ፦
- ƒ(x) = x2 እና g(x) = x+1 ቢሰጡን
- g(ƒ(x)) = x2+1, ከƒ ለg አቀባይ አስረካቢ
- ƒ(g(x)) = (x+1)2 = x2+2x+1, ከg ለƒ አቀባይ አስረካቢ
በዚህ አይነት መንገድ ብዙ ውስብስብ የሚመስሉ አስረካቢዎችን ከቀላል አስረካቢዎች ቅብብል መፍጠር ይቻላል።