ቅኝት

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ታገባዋት ሚስቴ ሊያውም በሰማኒያ

ትቅፍቅፍ ብለን ስንሄድ ገበያ

ነገሬም ሣንለው ያን የገበያ ሰዉ

ስንጣላ ውለን ታርቀን ስናበቃ

ደሞ በኩለ ሌት ወጥተን በጨረቃ

ያልታሠበ ድንጋይ ከቤታችን ጣራ

ዱብ ያለ ሲመስለኝ በዚያ አዚማም ለሊት

ፖሊስ መጣና አፈፍ ሲያደርገን በድንገት

በድንጋጤ መንፈስ በፍርሃት ስሜት

ልቤ ሲንሰፈሰፍ አፌ ሲርበተበት

እሷ ግን ብሶባት ይብስ ስታሽሟጥጥ

ፖሊስዬ እያለች ስታቆለማምጥ

ልቡ እየፈለገ ሊማታ እየዳዳው

እንዳይሰነዝር ህጉ እምቢ እያለው

አያይዞ ሲነዳን ልንደርስ ለፍርድ

አመል ያመል ነገር

ደሞ ተያያዝን እዛው ከዳኛው ስር

እንግዴህ ዘመኑ ነው ዘመኑ የሠጣት

ብሎ ሊፈርድላት እንዴት ይፍረድላት

ዕሷ ከላይ ሆና ስትወቃኝ ዕያያት።