Jump to content

ቅጽል

ከውክፔዲያ

ቅጽል - ዓይነትንና ግብርን፣ መጠንንም ለመግለጽ በስም ወይም በተውላጠ ስም ላይ የሚጨመር ቃል "ቅጽል" ይባላል። ስሙ እንደሚያመለክተው ቅጽል ማለት ቅጥያ ወይም ተጨማሪ ማለት ነው።

ምሳሌ - ጥቍር ፈረስ፣ ብርቱ ፈረስ፣ ዐጭር ፈረስ።

እነሆ! ቅጽል የተባሉት "ጥቍር፣ ብርቱ፣ ዐጭር" ናቸው። ፈረስ የአንድ እንስሳ ስም ነው። ጥቍር ፈረስ ሲል ዓይነቱንብርቱ ፈረስ ሲል ግብሩንዐጭር ፈረስ ሲል መጠኑን የቅጽሉ ቃል ያስረዳል። ስለዚህም በስምና በተውላጠ ስም ላይ እየተቀጠለ ዓይነቱን፣ ግብሩን፣ መጠኑን የሚገልጽ ቃል ሁሉ "ቅጽል" ይባላል።

"ያማርኛ ሰዋስው"፣ ፲፱፵፰ ዓ.ም፣ ከብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ