በላ ልበልሃ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

በላ ልበልሃ ማለት በኢትዮጵያ ዘመናዊ ፍርድ ቤቶች ሳይቋቋሙና የወንጀለኛ መቅጫ እና የፍታ-ብሄር ህግ ተረቆና በአዋጅ ፀድቆ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ህዝቡ በሃገር ሽማግሌዎች የሚዳኝበት ባህላዊ የፍርድ ሂደት ነው፡፡ ይሁንና "በላ ልበልሃ" እስካሁንም በተለይ ከከተሞች ርቀው በሚኖሩ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች እየተጠቀሙባቸው ከሚገኙት ባሕላዊ ሽምግልናዎች የተለየ የሚያደርገው መሰረታዊ ልዮነት ያለው የዳኝነት ስርዓት አለው፡፡ ይኸውም በዳይና ተበዳይ /ከሳሽና ተከሳሽ/ ዳኞች ፊት ቀርበው ክርክር የሚያደርጉት በስነ ግጥምና በቅኔ መሆኑ ነው፡፡ ህዝቡም ዙሪያቸውን በመታደም የፍርድ ሂደቱንና ክርክሩን የሚከታተል ሲሆን፤ በተለይ "በበላ ልበልሃ" ክርክር አሸናፊ የሆነ ሰው በሙግት አዋቂነቱና በግጥም ችሎታው ከህብረተሰቡ ከፍተኛ አድናቆትንና ከበሬታን ያገኛል፡፡

ውጭ መያያዣ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]