በርትራንድ ረስል

ከውክፔዲያ
በርትራንድ ሩስል

በርትራንድ ሩስል (Bertrand Arthur William Russell ) (1872 – 1970) በስነ አምክንዮአዊ ሂሳብና በፍታሃታዊ ፍልስፍና ጥናት እውቅናን ያገኘ የ20ኛው ክፍለዘመን እንግሊዛዊ ፈላስፋ፣ ስነ አምክንዮ አዋቂ እና አጠቃላይ ትችት ጸሃፊ ነበር። ከሚታወቅባቸው የጥናት ውጤቶቹ መካከል፣ ማንኛውም ሂሳብ ወደ ስነ-አምክንዮ መለወጥ ይችላል በማለቱ፣ የጀርመኑን ፍሬገ ስነ አምክንዮ ስልት በማጥራት እንዲሁም ለኒውራል አንድዮሽ (አለም ከአንድ ነገር ብቻ ተሰርታ ስታበቃ ይህ አንድ ነገር ሙሉ ለሙሉ ምናባዊ ወይም ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ተጨባጭ አይደለም) ጥብቅና በመቆም...ወዘተ ይታወቃል።