Jump to content

በርጫ

ከውክፔዲያ

በርጫ በአጠቃላይ የጫት መቃምን ስነ-ሥርዓት ያጠቃልላል። በርጫ ሲጀመር በፈጣሪ ምስጋና ይከፈትና፡ ወደ ጫት የመቃሙ ሂደት ይገባል። የዘወትር ቃሚዎች ለመቃም ትንሽ ሲቀራቸው ጀምሮ እስከ መጀመሪያው የጫት ጉርሻ ባሉት ሰዓታት ውስጥ ድምፃቸውን የማጉላት፣ እርስበእርስ የመተራረብ፣ አልፎ አልፎም የመሳደብና የመጣላት ባሕሪ ይታይባቸዋል። የሙዚቃ ምርጫቸውም ሞቅ ያለ ነው በዚህ ስዓት።

ሁለተኛው የበርጫ ክፍለ ጊዘ ቁምነገርም ሆን አልሆነ፡ በተጀመረው አርዕስት ላይ ጥልቀት ያለው ውይይትና ክርክር በማድረግና ኃሣብ የማመንጫትና የማብራራት በቃሚዎች ላይ ይታያል። ሦስተኛውና የመጨረሻው ክፍል ዝምታ የሰፈነበት የምርቃና ክፍለ ጊዘ ሲሆን በዚህም ወቅት ቃሚዎች ረብሻ አይፈልጉም። በግል ኃሣባቸው የመዋጥ፣ የማንበብ ወይም ጸጉር የመጠቅለል፣ የጫት እንጨት የመስባበርና ወዘተ ድግግም ነገሮችን የሚስሩበት ወቅት ነው።