በቅመም የተዘፈዘፈ አትክልት
Appearance
- ግማሽ ኩባያ በቀጭኑ ሆኖ በክብ የተከተፈ ዝኩኒ
- ግማሽ ኩባያ ቀይ የፈረንጅ ቃሪያ በክብ የተከተፈ
- ግማሽ ኩባያ ቢጫ የፈረንጅ ቃሪያ በክብ የተከተፈ
- ግማሽ ኩባያ ዱባ በክብ የተከተፈ
- ግማሽ ኩባያ በክብ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
- 16 ትልልቅ ፍሬ ፍሬሽ መሽሩም
- 16 ትንንሽ ቲማቲም
- ግማሽ ኩባያ ኦሊቭ ኦይል (የወይራ ዘይት)
- ግማሽ ኩባያ ሶያ ሶስ (ቀዩ)
- ግማሽ ኩባያ የሎሚ ጭማቂ
- አንድ ትልቅ የነጭ ሽንኩርት ዘለላ የተፈጨ
- 1. አትክልቶቹን በሙሉ ትልቅ ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ መጨመር
- 2. አነስ ባለ ዕቃ ደግሞ ዘይት፣ ሶያ ሶስ፣ የሎሚ ጭማቂው እና ነጭ ሽንኩርቱን ቀላቅሎ፣ በአትክልቱ ውስጥ መጨመር፤ ከዚያ ሳህኑን ሸፍኖ ለግማሽ ሰዓት ያህል ፍሪጅ ውስጥ በመክተት እንዲዘፈዘፍ ማድረግ፡፡
- 3. ከዚያም የግሪል መጥበሻን ካሞቁ በኋላ በዘይት መለቅለቅ፤ አትክልቱን ከተዘፈዘፉበት እያወጡ ከ12 - 15 ደቂቃ መጥበስ ወይም ደግሞ እስከሚበስሉ ድረስ በመጥበሻው ላይ ማቆየት፡፡