Jump to content
አማርኛ ውክፔድያን አሁኑኑ ማዘጋጀት ትችላላችሁ - ተሳተፉበት!

በቆሎ

ከውክፔዲያ

በቆሎ (ሮማይስጥZea mays) መጀመርያ በቅድመ-ታሪክመካከለኛ አሜሪካ የተደረጀ የእህል አይነት ነው። ከ1500 ዓም በኋላ ወደ ሌሎቹ አህጉራት ተስፋፋ። ቅንጣት ፍሬው ከስንዴ እጅግ እስከሚበልጥ ድረስ በመዝራት ተለማ።

የተለመደበት ወገን ወይም አውሬ በቆሎ ቴዮሲንቴ (Zea) የተባሉት የሣር ዝርዮች ናቸው። የቴዮሲንቴ ተክል ግን አንድያ አነስተኛ ቅንጣት ብቻ ያወጣ ሲሆን፣ በዘመናት ላይ የሜክሲኮ ኗሪዎች በግብርና ዘደዎች ጠቀሜታውን ዕጅግ አስፋፉ።


ሥነ ሕይወት ጥናት ዘንድ በሣር አስተኔ ውስጥ የበቆሎ ቅርብ ዘመዶች ማሽላ እና ሸንኮራ ኣገዳ ናቸው።

ቴዮሲንቴ (ላይ)፣ ክልሱ እና በቆሎ ቅንጣቶች ሲነጻጸሩ