በከራ
Appearance
በከራ ከሽክርክር እና ምሰሶ የተሰራ ሲሆን ብዙ ጊዜ ገመድ በሽክርክሩ ላይ በማረፍ የጉልበትን አቅጣጫ ለመቀየር ያገለግላል። የበከራወች ስብስብ የጉልበትን አቅጣጫ ለመቀየር ብቻ ሳይሆን፣ ጉልበትን ለማብዛት ሁሉ ሊጠቅም ይችላል።
በገመድ ላይ የሚገኘው ወጥረት በነጻው የገመዱ መጨረሻ ላይ ከሚያርፈው ጉልበት ጋር እኩል ስለሆነ፣ ገመዱን በበከራወች በማጣጠፍ ጉልበትን በብዙ ቁጥር ማብዛት ይቻላል። በዚህ አይነት መንገድ ከክርስቶስ ልደት 300ዓመት በፊት የነበረውአርኪሜድስ፣ ወታደሮች የተጫኑ የጦር መርከቦችን በበከራና ገመድ ከምድር ወደ ባህር ያጓጉዝ ነበር።
-
ስዕል 1 - የበከራው ምሶሶ ላይ የሚያርፈው ጉልበት ገመዱ ውስጥ ካለው ውጥረት 2 እጥፍ ነው
-
ስዕል 2 - የሸክሙን ክብደት ግማሽ በገመዱ ላይ በማሳረፍ ሸክሙን በዚህ መልኩ በበከራ ማንሳት ይቻላል
-
ስዕል2 ሀ - ከስዕል 2 ጋር አንድ አይነት የሆነ የጉልበት ስርጭት ሲኖር ነገር ግን ጉልበቱ ወደ ላይ ሳይሆን ወደ ታች እንዲያመልከት 3ኛ በከራ ያገለግላል
-
በተግባር ላይ የዋለ የስዕል2 አይነት በከራ ስርዓት
-
ስዕል 3 - በዚህ መንገድ እቃውን ለማንሳት የክብደቱን 1/3ኛ ብቻ ይፈልጋል።
-
ስዕል 3ሀ - ከስዕል3 ጋር አንድ አይነት ሲሆን ነገር ግን ክብደቱን አንሺው ጉልበት ወደ ታች ያመለክታል።
-
ስዕል 4 - በዚህ ሁኔታ እቃውን ለማንሳት የክብደቱን 1/4ኛ ብቻ ይፈልጋል። ተጨማሪው በከራ ጉልበቱን ወደታች እንዲያመልከት ያደርጋል።
-
ስዕል 4ሀ - ተግባራዊ የበከራ ስርዓት