በጃቸው

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

በጃቸው

(18) አለቃ በጣም ሴሰኛ መሆናቸው ይነገራል። በአንድ ወቅት አንዲት ወጣት አይተዋት በመውደዳቸው ወላጆችዋን እንደምንም ብለው በማስፈቀድ ያገቧታል። አንሶላ የመጋፈፊያው ጊዜ ሲደርስ አለቃ ወረድ ብለው ስራ ሊጀምሩ ሲሉ እንትናቸው ተኝቶ አልነሳ እምቢ ይላቸዋል። ቢታገሉ ቢታገሉ አልተሳካላቸውም። ስለዚህ ሌላ አማራጭ በመውሰድ ለእጃቸው ተጨማሪ ስራ ሰጥተው ሲያሰሩ ያድራሉ። መከራዋን ስታይ ያደረች ልጅም ጠዋት ለሽንት እንደወጣች በዚያው ጠፍታ ወደ ወላጆችዋ ትሄዳለች። ችግሯን ግን ደፍራ አልነገረቻቸውም። ይሁንና አለቃ ሳያፍሩ ሽማግሌ ሰብስበው ወደ ልጂቱ ቤት ይመጣሉ። ሽምግልናም ይጀመራል። ለምን ትተሻቸው እንደመጣሽ፤ ምን እንደበደሉሽ ንገሪን ትባላለች። እንዴት ደፍራ ትናገር! ተቸገረች። በመጨረሻም ሲያዋክቧት ግራ ገባትና በእጃቸው .....ብላ የሚቀጥለውን መጨረስ ሳትችል ትቀራለች። አለቃም ምን ለማለት እንደፈለገች ይረዱና ወዲያውኑ ለሽማግሌዎች እስቲ እግዜር ያሳያችሁ! ድሮውንስ ላይበጀኝ ነው ያገባኋት በጃቸው የምትለኝ? ብለው ለጊዜው ጉዳቸው ሳይወጣ አሸንፈው ወሰዷት ይባላል።