Jump to content

በጌምድር

ከውክፔዲያ

አማራና_የብሔር_ብሔረሰቦቿ

#አብሮነት፦

⇣◢◤◥◣◢◤◥◣⇣

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት ውስጥ የተለያዪ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ያሉበት ክልል ነው።

የአማራ ክልል መንግስትም አማራን፣ የአገውአዊን፣ የኦሮሞን፣ የዋግእምራን፣ የአርጐባንና የቅማንትን ብሄር ብሔረሰቦች ወክሎ የተዋቀረ የክልል መንግስት ነው።በክልሉ የሚገኙት ሁሉም ብሔረሰቦች የራሳቸው ቋንቋ፣ባህልና ታሪክ እምነት ያላቸው ብሄረሰቦች ናቸው። በአብዛኛው ሁሉም በክልሉ የሚገኙ ብሄረሰቦች የአማርኛ ቋንቋን አቀላጥፈው ይናገራሉ፤የጋራ ማህበራዊ ህይወታቸውን ስንመለከት አጠቃላይ ማህበራዊ ክንዋኔዎችን የሚያደርጉ እና በአንድ አይነት ማህበራዊ ክንዋኔዎች የሚገለጹ ህዝቦች ናቸው፡፡በእምነት፣ በጥቃት ፣ በመልከ አምድራዊ አኗኗራቸው… ወዘተ ተከባብረውና ተደጋግፈው የሚኖሩ ሕዝቦች ናቸው። በጠቃላይ የክልሉ ህዝቦች በአብሮነት የክልሉን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በጋራ ና በአንድነት እኩል ተሳትፎ ያደርጋሉ።

********************

#የአማራ_ክልል_ብሔር_ብሄረሰቦችናሕዝቦችን አጠር አድርገን ዘርዝረን እንመልከት፦

①/፩)#የአማራ_ብሄረሰብ

"አማራ" የአማራ ክልል ብሄር አንድ አካል ነው፡፡ አብዛኛውን የክልሉን ህዝብ በመልከ ኣምድራዊ አቀማመጡ፣በቋንቋው ተናጋሪ ብዛት፣በሰፊው የሚሸፍን በመሆኑ የአጠቃላይ የክልሉ መጠሪያ ሆኗል፡፡"አማራዎች በአብዛኛው የክርስትና እምነት ተከታዮች ናቸው።በሸዋ፣በወሎ፣ በጐጃምና በጐንደር በስፋት ይገኛሉ። የራሳቸው ባህል ታሪክና ቋንቋ ያላቸው ብሔረሰቦች ናቸው። ከሁሉም ብሄረሰብ ጋር በአብሮነት ተቻችለው የሚኖሩ ህዝቦች ሲሆኑ የአማራ ብሔር እንደኔ እንደኔ ሁለት ተጨማሪ ተደራቢ ማንነቶች አሉት እነሱም፦

{፩.፩}#ቤተ_እስራኤል_አማራ(#ፈላሻ)ቤተ እስራኤል የአማራ ብሄር አንዱ ክፍል ነው፡፡ሆኖም ወደእስራኤል አገር ከመሄዳቸው በፊት #ፈላሻ ወይም ቤተ እስራኤል የሚል መጠሪያ ነበራቸው፡፡ የድሮ ቋንቋቸው ግን አማርኛ ነበር፡፡ አሁን ወደእስራኤል ከሄዱ በኋላ ግን የኋላኛው ትውልድ "እብራይስጥኛን" እንደ በዋና ቋንቋነት ይናገራል፡፡ ታሪካቸው የተወሳሰበ ቢሆንም ከአማራ ብሄር የተለዩ አይደሉም።

{፩.፪}#ወይጦ_አማራ "ወይጦ አማራ" ከመባሉ ውጭ በማንኛውም መስፈርት በህይማኖትም በባህልም አማራ እንደሆኑ ይገልፃሉ የታሪክ ፃሀፊዎች፡፡ ስለሆነም የአማራ ብሄር ነገድ አካል ነው፡፡

*******************

②/፬)#የኦሮሞ_ብሔረሰብ

ኦሮሞ በክልሉ መዋቅር ስር ከጥንት ጀምሮ በወሎ ምድር የሚኖሩ ማህበረሰቦች ናቸው።የራሳቸው ባህል ታሪክና ቋንቋ ያላቸው የእስልምና እምነት ተከታይ ማሕበረሰቦች ናቸው። የራስ አስተዳደራቸውን "የኦሮሚያ ልዩ ዞን" በሚል መስረተው ራሳቸውን በራሳቸው እያስተዳደሩ ይገኛሉ።

********************

③/፫)#የዋግእምራ_ብሔረሰብ

"ዋግእምራ" በአማራ ክልል ከሚገኙት ብሄር ብሄረሰቦች አንዱ ነው።በሰሜን ምስራቅ አማራ የሚገኙ ብሄረሰቦች ሲሆኑ የራሳቸው ልዩ የሆነ ባሕል፣ ቋንቋ ና ታሪክ ያላቸው ብሔረሰቦች ናቸው።በአሁኑ ሰአት የራስ አስተዳደር ዋግእምራ ልዩ ዞን መስርቶ ራሳቸውን በራሳቸው እያስተዳደሩ ይገኛል።

********************

④/፬)#የአገውአዊ_ብሔረሰብ

"አገውአዊ "የአማራ ብሄራዊ ክልል አንዱ ክፍል ነው፡፡ በምዕራብ አማራ የሚገኙ ብሔረሰቦች ሲሆኑ "የአገውኛ ቋንቋ" ን የሚናገሩ ና የራሳቸው ባህል ና ታሪክ ያላቸው ሕዝቦች ናቸው፡፡ የራሳቸው አስተዳደር "አዊ ልዩ ዞን" መስርተው ራሳቸውን በራሳቸው እያስተዳደሩ ይገኛሉ።

********************

⑤/፭)#የቅማንት_ብሔረሰብ

"ቅማንት" የአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት አንዱ ክፍል ነው፡፡ የቅማንት ማሕበረሰቦች የራሳቸው ባሕል ታሪክና ቋንቋ ያላቸው የክርስትና እምነት ተከታይ ማሕበረሰቦች ናቸው። ከአማራ ሕዝብ ጋር በአብሮነትና በፍቅር ተሰሳስረው በመተሳሰብ የሚኖሩ ማሕበረሰቦች ናቸው።ራስን በራስ ለማስተዳደር ጥያቄ አቅርበው በ2007 ዓ.ም በሰሜን ጐንደር ዞን "የቅማንት ልዩ ወረዳን" መስርተው ራስን በራስ እያስተዳደሩ ይገኛሉ።የልዩ ወረዳዋ ህዝቦች ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተከብሮ ቋንቋቸውን ለማሳደግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።ሙሉ በሙሉ መብታቸው ተከብሯል። ነገር ግን ከወረዳው ውጭ ባሉ አጐራባች ወረዳዎች የሚኖሩ የብሄረሰቡ አባላቶች የራስ አስተዳደር ጥያቄ አቅርበው ምላሽ እየጠበቁ ይገኛሉ።

*******************

⑥/፮)#የአርጎባ_ብሔረሰብ

"የአርጎባ ማሕበረሰብ"ከጥንት ዘመን ጀምሮ በአማራ ውስጥ ከሚገኙት ብሄሮች አንዱ ነው፡፡ የራሳቸው ባህል፣ ቋንቋ ናታሪክ ያላቸው የእስልምና እምነት ተከታይ ማህበረሰቦች ናቸው። ቋንቋቸውም "አርጐብኛ" ይባላል። በተለያዩ የአፄ ገዢዎች ምክኒያት ቋንቋቸው ቢዳከምም ዛሬ ድርስ የአርጐብኛ ቋንቋን በጥቂት አካባቢዎቻቸው ላይ ይናገራሉ።

ራስን በራስ ለማስተዳደር ለክልሉ ምክር ቤት ጥያቄ አቅርበው በ1998 ዓ.ም በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙት የብሄረሰቡ አባላቶች "የአርጐባ ልዩ ወረዳን" መስርተው ራሳቸውን በራሳቸው በከፊል እያስተዳደሩ ነው።

የብሄረሰቡ ተወላጆች በወረዳው ብዙም ደስተኛ አይደሉም ምክኒያቱም የይምሰል ልዩ ወረዳ ነው……። በብሄረሰቡ ጥቂት ተወላጆች አማካኝነት ቋንቋቸውን ለማሳደግ የተለያዩ መፅሀፍትንና ብሮሸሮችን በማዘጋጀት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ከወረዳው ወጭ ያሉ በወረዳው አጎራባች ቀበሌ የሚገኙት የብሄሩ አባላት የራስ አስተዳደር ጥያቄ አቅርበው ምላሽ በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።በኦሮሚያ ልዩ ዞንና በሰሜን ሸዋ ዞን በ12 ወረዳዎች ከ92 ቀበሌዎች በላይ የሚገኙት የብሄረሰቡ አባላትም ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ራስን በራስ ለማስተዳደር ጥያቄ አቅርበው ምላሽ መጠበቅ ከጀመሩ ሰነባብተዋል።

የአርጐባ ብሔረሰቦች ከማንኛውም ብሄር ብሄረሰብ ጋር በአብሮነት፣ በሰላምና በፍቅር ተቻችሎ በመኖር ከሚጠቀሱት የኢትዮዽያ ብሔር ብሔረሰቦችና ኅዝቦች ግንባር ቀደሞቹ ናቸው።ወሬ ላማሳመር ብዬ ሳይሆን በታሪክም ተግባርም የሚታወቅና የሚታይ ነገር ነው። በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሐረሪና በአፋር ክልል በብዛትና በስፋት በሚኖሩበት ሑሉ ከማንኛውም ብሄር ብሄረሰብ ጋራ ቋንቋውን፣ባህሉን ወረሰው የጋራ ማህበራዊ ትስስር ፈጥረው የሚኖሩ ብሔረሰቦች ናቸው።

********************

እነዚህ ከላይ ከ①/፩ኛ እስከ⑥/፮ኛ የተዘረዘሩት ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በአማራ ብሔረሰብ ስር በጋራ የሚኖሩ የአንድ ምድር ህዝቦች ናቸው።ሑሉም ባለፉት የአፄ መንግስታቶች ተፅዕኖ ቀንበር ውስጥ የነበሩ ብሔር ብሔረሰቦች ናቸው። ከሌሎች ብሔር ብሔረሶች ጋር በመሆን ባደረጉት ትግል በ1983 ዓ.ም አምባገነን መንግስት ድል አደረጉ። የፌደራሊዝም ስርዓት ተገንብቶ የሀገራችን ህገ መንግስት በህዝቦች ውሳኔ ከፀደቀ ቡሃላ ራስን በራስ የማስተዳደር የእኩልነት መብት ለሁሉም ለብሄር ብሄረሰቦች በሚል ፍትህ አገኙ። ይሁን እንጂ ይህን ስርኣት የሚጠሉት የአምባገነኑ ርዝራዦች ኢህአዴግን እንደጠላት አድርገው ይቆጥሩታል። ጭቁን የነበሩ ብሄር ብሄረሰቦች ግን ኢህአዴግን እያመሰገኑት እንደሆነ እርገጠኛ ነኝ።

የአርጎባ ማህበረሰቦች ራስን በራስ ለማስተዳደር በድርጅታቸው አሕዴድ ኢህአዴግ አማካኝነት ከ1986ዓ.ም ጀምረው በኦሮሚያ ልዩ ዞን፣ በደቡብ ወሎና ሰሜን ሸዋ ዞኖች ራስን በራስ የማስተዳደር የመብት ጥያቄያቸውን አቅርበው «በደቡብ ወሎ ዞን ጥቂት ቀበሌዎችን ብቻ» እንዲያስተዳድር ወሰኖ የተቀሩት ደግሞ ከሌሎቹ

ብሄረሰቦች በተለየ ሁኔታ ለህዝብ በማይታወቅና ግልፅ ባልሆነ ምክኒያት ምላሽ አላገኙም። ይሁን እንጂ የአርጐባ ብሔረሰቦች መብታቸውን በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ጥያቄያቸው አቅርበው አሁንም ምላሽ በመጠበቅ ላይ ናቸው! ግን ለምን? አባት ልጁን ድሮ ጎጆ እንደሚያወጣው ሁሉ…… ሑሉንም ብሔረሰቦች በእኩል አይኑ ሊመለከታቸው ይገባል።

____________________________

____________________________

#ማስታወሻ፦ በፅሁፌ ላይ ስህተት ካለበት ይቅርታ እየጠየቅኩ አስተያዬታችሁን እሻለሁ ይገነባኛልና በተመቻችሁ ሁኔዎች ሁሉ ልትገልፁልኝ ትችላላችሁ እወዳችሗለሁ ደህና ሁኑ!

____________________________

#የመረጃ_ምንጮቼ፦

1,Amhara community.org

2,Short History of Argoba.

3,ከአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ብሮሸር

≈≈≈≈≈≈ ≈≈≈≈≈≈ ≈≈≈≈≈≈

"የጣና ሐይቅን እንታደግ! የ"እቦጭ" አርምን ተባብረን እናስወግድ!"

"የብሔር ብሔረሰቦች መብት ተከብሮ በአንድነት፣በፍቅር፣ከሌሎች ሕዝቦች ጋር እኩል ተከባብረን የጋራ ኢትዮዽያችንን እንገንባ!"

የጋራ ጠላታችን ድህነትን እንዋጋ!

≈≈≈≈≈≈ ≈≈≈≈≈≈ ≈≈≈≈≈≈

©በሰዒድ አል ጀበርቲ ተፃፈ

አዲስ አበባ-ኢትዮዽያ