Jump to content

በ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት

ከውክፔዲያ
ፍታቤሄር ህግ

በ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሕዝቡ መብቶች ክፍል

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  • አንቀጽ 37። ማንም ሰው በሕግ እኩል ሆኖ ይጠበቃል።
  • አንቀጽ 38። በብሔራዊ (ሲቪል) መብቶች በመጠቀም ረገድ፡ በኢትዮጵያውያኖች (የኢትዮጵያ ተገዦች) መካከል ምንም ልዩነት አይኑር።
  • አንቀጽ 39። የኢትዮጵያ ተወላጅነትንና የኢትዮጵያ ዜግነትን ለማግኘትና ለማጣት የሚያስችሉ ኹኔታዎችን ሕጉ ይቀምራል (ይወስናል)።
  • አንቀጽ 40። የሕዝቡን መልካም ጠባይ ወይም ፀጥታን ወይም በፖለቲካ ረገድ የሚያውክ ካልሆነ በቀር፡ በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ግዛት የሚኖሩ ሰዎች በሕግ መሠረት የሃይማኖታቸውን ሥርዓት አክብረው በነፃ ከመፈጸም አይከለከሉም።
  • አንቀጽ 41። በመላው የንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ውስጥ በሕግ መሠረት የንግግርና የጋዜጣ ነፃነት የተፈቀደ ነው።
  • አንቀጽ 43። ማንኛውም ሰው ከንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ግዛት ውስጥ ሕይወቱን ነፃነቱን ወይም ንብረቱን ያለ ሕግ አያጣም።
  • አንቀጽ 45። የኢትዮጵያ ዜጎች በሕጉ ተዘርዝሮ በሚወስነው መሠረት የጦር መሣሪያ ሳይዙ ሰላማዊ ስብሰባ ለማድረግ መብት አላቸው።
  • አንቀጽ 46። በሕግ ካልተከላከለ በቀር በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ውስጥ ከሥፍራ ወደ ሥፍራ የመዛወርና መኖሪያ ሥፍራን የመለወጥ ነፃነት ለንጉሠ ነገሥት መንግሥት ዜጎች ሁሉ ተረጋግጧል።
  • አንቀጽ 47። ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ በሕግ መሠረት ማናቸውም ዓይነት ሥራ እየሠራ ለመኖር፤ ማናቸውም የሥራ ማኅበር ለማቋቋምና በማናቸውም ማኅበር አባል ለመሆን መብት አለው።
  • አንቀጽ 49። ማንኛውም የኢትዮጵያ ተገዥ ከንጉሠ ነገሥት መንግሥት ግዛት ውጭ ለመሳደድ (ሌቅቆ እንዲወጣ) ሊገደድ አይችልም።