Jump to content

ቡርጂ

ከውክፔዲያ

ቡርጂኢትዮጵያ ብሔር ነው።

ቡርጂ በደቡባዊ የኢትዮዽያ ክፍል የሚኖር ሕዝብ ሲኾን የራሱ የኾነ ባህል ታሪክ ቋንቋ አመለካከት የአኗኗር ዘይቤ ያለው ሕዝብ ነው።

☞አጠቃላይ ገጽታ


ወረዳው በቀድሞ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ከሚገኙ 14 ዞኖች አንዱ በሆነው በሰገን አከባቢ ሕዝቦ ዞን ውስጥ ካሉ 5 ወረዳዎች አንዷ የነበረችና በአሁኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ብህራዊ ሕዝቦች ክልል ውስጥ ካሉ ዞኖች አንዷነች፡፡ -ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ በደቡባዊ ምሥራቅ በ5ዲግር 13’ 18’’ እና 5ዲግር 42’ 00” ‹‹ላቲትዩድ መስምርና በ35ዲግር 34’ 2” እና 37ዲግር 58’ 2” ምስራቅ ሎንግትዩድ መሀከል ይገኛል፡፡ የድንበር አዋሳኞች -በምሥራቅ እና በደቡብ ከኦሮሚያ(ቦረና ዞን) ሀ/ማርያም -በምዕራብ ከኮንሶ ወረዳ -በሰሜን ከአማሮ ወረዳ ጋር ይዋሰናል፡፡ የወረዳው የቆዳ ስፋት -ጠቅላላ የወረዳው ቆዳ ስፋ 1877.6 ካሬ ኪ.ሜ/187760 ሄክታር ሲሆን የሕዝብ ብዛት 87789 አካባቢ ነው፡፡ -የመስተዳደር መዋቅር በ24 የገጠር ቀበሌያትና ሁለት የከተማ ቀበሌያት አንድ 5ኛ ደረጃ ማዘጋጀ ቤት እና ሦስት ታዳጊ ማዘጋጃ ቤቶች በድምር በ26 ቀበሌያት ተዋቅረዋል፡፡ የአየር ንብረቷን በተመለከተ -አማካይ የዓመታዊ የዝናብ መጠን 801-1000 ሚ.ሜትር፣ አማካይ የሙቀት መጠን 15.1 ዲ.ሴ -27.5 ዲ.ሴ ሲሆን *ከባህር ወለል በላይ ያለው ከፍታ ከ810-2852 ሜትር ነው፡፡ የአየር ፀባይ ቆላ 38-40፣ወይና ደጋ 46 እና ደጋ 14 በመሆን ሦስት የአየር ፀባያት ይኖረዋል፡፡በወረዳዋ ጤፍ፣ቡራ ቡርጂ፣በቆሎ፣ስንዴ፣እንሴት፣ሙዝ፣ሽምብራ፣ገብስ፣ካዛቫ፣አተር፣ምሥር. . . .ወዘተ ይበቅልበታል፡፡

         *መሠረተ-ልማትን በተመለከተ

በሀ/ማሪያም(ቡሌ-ሆራ)ከሚያልፈው ዋና አስፋልት መንገድ ጀምሮ እስከ ሶያማ ከተማ 61ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ፣ከዲላ እስከ ቡርጂ 159ኪ.ሜ በከፊል አስፋልት በከፊል የጠጠር መንገድ እና ከቡርጂ እስከ ኮንሶ 80 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ ተጠቃሚ ነው፡፡ በሌሎችም የልማት መስኮች የወረዳው ዋና ከተማ የ24 ሰዓት የመብራት፣የአውቶማቲክ ተንቀሳቃሽ(ሞባይል)ስልክ አገልግሎት እና የገጠር ቀበሌያት ጨምሮ በአጠቃላይ 31.5 ንፁሕ የመጠጥ ውኃ አገልግሎ ተጠቃምና በአሁኑ ጊዜ 12 ቀበሌ የማብራት ተጠቃም ሲሆኑ ሌሎች በቅርብ ጊዜ መጠቀም ይጀምራሉ፡፡

✍ወረዳዋ ቡርጂ የምል የወረዳ ስያሜ ያላት ስትሆን ዋናው ከተማ ሶያማ ተብላ ትጠራለች።

ቡርጂ የራሶ የሆነ መጠሪያ ያላት ስትሆን ቡርጂ Dashate የምል የራሶ ብቸኛ ቋንቋ ባለበት ነች፣ ስለዚ ቡርጂ የራሶን ማንነት የምገልፅ ባህል፣ ወግና ስርዓት ያለች በብሔሩ የሰውን ነገር መንካት አፀይፋ የምትመለከት የምትኖር ብሔር ነች ።በመሆኑም ቡርጂ የምትታወቅባት 27 ቀበሌያት ሶያማ 01 ፣ሶያማ 02፣ ሐራወንጄ፣ ትሾ፣ ሙሬ፣ ኦቶሞሎ፣ ወርደያ ጉዴ፣ ድንቤቾ፣ ራሌያ ጎቼ፣ ብላ፣ ገራ፣ ዋለያ ጩሉሴ፣ ሐራሌ፣ ነዴሌ(አበላ) ፣ ሐላሜ ፣ ላድሼ፣ የበኖ፣ ዳልኦ፣ ገምዮ፣ ክልቾ፣ ሰጎ፣ ለሞ፣ እና (አዋር) ቀበሌያት ጎበዜ፣ ትንሿ ቀያተ፣በረቅ ና በኔያ ቀበሌያት ስሆኑ ትንሿ ቀያተ በሰገን ዞን ከተማነት ተቀላቅላ የነበረች ቢሆንም ዞኑ በመፍረሱ ተመልሳ ወደ ነበርችበት ተመልሳለች፡፡ ስለዝህ አጠቃላይ እኝህ ቀበሌ ውስጥ የምኖሩት 85% አርሶ አደር ናቸው። በወረዳው የምመረቱ አብዛኛው የጤፍ ምርትና በቡራ ቡርጄ (አማራ) በመሆኖ ቡርጂ እስከ ናዝረት አዳማ እና እስከ ናይሮብ ቦንቦሳ ማርሳቤት ድረስ ይታወቃሉ። ለላው በዞኑ የቦቆሎ ፣ የስንደ፣ የገብስ እህሎች ይመረታሉ። ✍በወረዳችን የሚታወቁ ነገሮች ማራክና አትራክትቭ መንፈሶን የምያድሱበት አይተው በተፈጥሮ የምደሰቱበት ለላኛው ከቅርብ ጊዜ የተፈጠረው የኬላሌ ሐይቅ ፣ የሚንሞና ዋሻ፣ የወዮ ደን አና የኤርዶያ ተራራ በከፍተኛው በወረዳችን የምታወቁ በመሆናቸው ቀጣይ ላይ እኝህ መስህቦች ብለሙ ከፍተኛ ለወረዳ ገብ ስለምያስገኝ ወረዳው ጠንክረው የምሰሩበት ስራ ነው። ስለዝህ ወረዳዋን መታችሁ ጎብኙ መልዕክታችን ነው። ። ።

በወረዳ ከሚገኙ መስህቦች በከፊል ሚና-ሞና ዋሻ


የሚገኝበት ቦታ-በቡርጂ ወረዳ በየበኖ ቀበሌ ከወረዳው ዋና ከተማ ያለው ርቀት 15ኪ.ሜትር ከቀበሌው ያለው ርቀት 15ኪ.ሜትር ከቀበሌው በእግር ጉዞ የሚፈጅበት ጊዜ 30 ደቂቃ መስብነቱ፡-ይህ ዋሻ በወረዳው ካሉት ዋሻዎች በይዜት፣በስፋቱና በግዙፍነቱ ልዩ ከመሆኑም በላይ ከሦስት ትላልቅና ሰፋፊ ኣለቶች አንዱ በሌላኛው ላይ ተነባብሮ ሦስት ክፍል የሠራና ከዘመናዊ ፎቅ ቤት ጋር ተመሳሳይ ይዜት ያለው መሆኑ ነው፡፡ -ሌላው አስደናቂና ማራኪ የሚያደርገው ይህ ግዙፍ ባለሦስት ክፍል ዋሻ በሰንሰለታማ ገደል አፋፍ ተንጠልጥሎ ያለምንም ድጋፍ መቀመጡ ነው፡፡ ዋሻው ባጠቃላይ በሦስቱ ክፍሎች እስከ 50 ሰዎች የመያዝ አቅም ሲኖረው በአንደኛው ክፍል 8 ፣ በሁለተኛው ክፍል 5 እና በሦስተኛው ክፍል እስከ 27 ሰዎችን ይይዛል፡፡ ሚንሞናን ሲጎብኙ ከየበኖ እስከ ሐላሜ ያለውን ሰንሰለታማ የመሬት አቀማመጥ በከፊል፣ማራኪ ሸንተረሮችና የሠገን የተፈጥሮ ደንና የዱር እንስሳት ያሉበት ሜዳ እንዲሁም ከቡርጂና ከአማሮ ምዕራብ ክፍል ገባር ወንዞች የዳበረና ሜዳውን ሰንጥቆ የሚጓዘውን በጎማሬና በሌሎች እንስሳት የተካነውን ትልቁን የሠገን ወንዝ የመጎብኘት ዕድል ይኖርዎታል፡፡ 2.ከየበኖ እስከ ሐላሜ ሰንሰለታማ የመሬት አቀማመጥ በከፊል -የሚገኝበት ቦታ፡- በቡርጂ ወረዳ ከየበኖ እስከ ሐላሜ ቀበሌ ድረስ የሚዘልቅ -ከወረዳዋ ዋና ከተማ ያለው ርቀት 15-30 ኪ.ሜ -ከእያንዳንዱ ቀበሌ ያለው ርቀት 1.2-1.5 ኪ.ሜ


-መስህብነቱ፡- ተፈጥሮአዊ ይዜትና ከ15-20 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ነው፡፡ ከሠገን የተፈጥሮ ደንና የዱር እንስሳት ሜዳ ወደ ላ አሻቅበው ሲጎብኙ ሰንሰለታው የመሬት አቀማመጡ እጅግ ማራኪ ዓይን የሚሰብና ወጥነት ያለው ከአናት ላይ የማይበላለጥና በእኩል ርቀት3 የተደረደረ መወጣጫ መሰላል የሚመስል እይታ ያለው ነው፡፡ . . ይህን የተፈጥሮ መስህብ ሲጎብኙ ሌሎች እንደ ሚንሞና ዋሻ የሠገን የተፈጥሮ ደንና የዱር እንስሳት ሜዳ እና የተለያዩ የመልከዓምድር አቀማመጦችን የመጎብኘት ሰፊ ዕድል ይኖርዎታል፡ 3. ዲቃቼ ፏፏቴ

ከወረዳዉ ዋና ከተማ በ12 ኪ.ሜ ርቀት  የምገኙ ዲቃቹ ፏፏቴ ከቀበለው በስተምዕራብ ሰገን ወንዝ ምስራቃዊና ዳገታማ መልክዓ ምድርን ተንተርሰው በ1.5ኪ.ሜትር  ከቀበለው ርቀው ይገኛል፡፡በእግር 40-50 ደቅቃ ያስከዳል፡፡

ፏፏቴው የራሱ ታርክ አለው፡፡ዲቃ/ዲቂ ማጠብ፣ጓል…የምል ፊቺ ብኖረውም ከፏፏቴ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ መታጠብ ቀጥተኛ ገላጭ ነው፡፡ መስህብነቱ፡- በአከባቢው ሸማግለዎች እንደምነገረው ለግርዝ ዕድሜያቸው የደረሱ ወጣት ወንዶች በእለተ ግርዝ ማልደው ፏፏቴ ይወረዱና ገላቸውን በደንብ ይታጠባሉ ፡፡ይህም ግርዝ የሚገባው በስለት ስለሆነ ተያይዘው ከምከሰት ማናቸውም በሽታና ‹‹ልክፍት››(እንድነሱ) ሁሉንም በመነጻጻት ለመታደግ ስባል ነው፡፡አሁን ከግንዛቤ መዳበርና ባዕድ አምልኮ ልየታ ደረጃ እያደገ መምጣት ጋር ቢቀርም ተጋቢ ሙሽራዋና ምዘዎቾ ከአንድ ቀን በፍት በፏፏቴ መታጠብ ግድ ነበር ይላሉ እነዚህም ተራክዎች፡፡ኮረዳዎችም እንደ ወንዶች አስተዳደጋቸው‹‹ንጹህ›› ስለነበረ አሁን ደግመው ወግ ማዕረግ ለማየት በመቃረባቸው ከታዳግነት ወደ እማወራነት መሸጋገርያ ማሳያው ፏፏቴውን በቅድሜ ጋቢቻ መጎብኘት ነው፡፡ከዚህም በኃላ የቤትና ቤተሰብ ሀላፍነትን ከእናቶቻቸው ለመረከብ ብቁ ስለመሆናቸውና እነሱም በተራቸው ለማሰረከብ ትውልዳዊ አደራና ኃላፍትነት የመከወን ተግባር ቃል ኪዳን ነው፡፡ወንዶችም ራሳቸውን አሳችለው መስራትን በመለማመድ የዛሬው ወጣት የነገው አባወራ መሆኑን ራዕይ መሰነቅያ ባህል ያዳብራሉ፡፡ 4. ኤርዶያ ተራራ የሚገኝበት ቦታ፡- በቡርጂ ወረዳ በክልቾ ቀበሌ ከዋና ከተማ የሚገኝበት ርቀት 2ኪ.ሜ መስህብነቱ፡- ይህ ተራራ ሰፊና የተንጣለለ ሜዳ በአናቱ ስላለው የመዝናኛ ሎጅ ለመገንባት ጠቀሜታ አለው፡፡ በሰንበለጥና በደን የተሸፈነ በመሆኑ ለዱር እንስሳት መጠለያነትም ያገለግላል በተጨመሪም ታሪካዊ መስህብነቱ እንደዛሬ መገናኛ በልነበረበት ዘመን የቡርጂና የኮንሶ አጎራባች ብሔረሰቦች በተራራው ጫፍ እሳት በመለኮስ በምልክት መገናኛ መልዕክት ይለዋወጡበት ነበር፡፡


5. ወዮ የተፈጥሮ ደን ወዮ በቡርጂ ወረዳ በዋለያ ቀበሌ ይገኛል፡፡ ከዋና ከተማ ያለው ርቀት 21ኪ.ሜ ከቀበሌው ያለው ርቀት 1.5ኪ.ሜ

ወዮ በቡርጂ ብሔረሰብ ነውር፣ለመተግበር ጾያፍ የሆነ የተከለከለና አሳፋሪ ድርጊት ማለት ነው፡፡ የወዮ ደን ያለበት አከባቢ የሕዝብ አካልና ወገን3 የነበሩ ጎሳዎችና ሰዎች በበሽታ ተጠቅተው ያለቁበት በመሆኑ ሌሎች ግለሰቦች፣ቡድኖችና ጎሣዎች መጠቀም ወይም በይዞታነት መያዝ በነውርነት ስተፈረጀ ሳይታረስ ለብዙ ጊዜያት በመቶየቱ የተለያየ የዛፍ ዝርያ ያለበት ደን በቅሎና ለምቶ ከትውልድ ትውልድ እየተላለፈ መምጣቱን እነዚህን የተረኩልን ሽማግሌዎች ይመሰክራሉ፡፡ ደኑ በኤሳው(ባህላዊ ባለሥልጣን)አማካይነት ያምንም ክፍያ ለማህበረሰቡ እንደጠያቂው ፍላጎት በህዝብ ተወካዮች አመኔታ ለቤትና ለሌሎች አገልግሎቶች ይውላል፡፡ አሁንም በህብረተሰቡ እየተዳደረና ጥቅም እየሰጠ ይገኛል፡፡ ወዮ የተፈጥሮ ደን ወሎ በሚል ስያሜ ከምኒልክ ወረራ ጋር ተያይዞ ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የመጡ ግለሰቦች ከአገራቸው ወሎ ክ/ሀ አንጻር ስያሜ አንዲኖረው አድርገው እንደሰየሙት በአከባቢው ነዋሪ የሆኑ አባቶችና ሽማግሌዎች ይናገራሉ፡፡ ስለዝህ ወዮ የተፈጥሮ ደን ከብዙ ዘመናት ቆይታ የተነሳ የተለያዩ የዛፍ ዓይነቶችና የዱር እንስሳቶች የምገኙበትና ለአከባቢው ለተፈጥሮ ሚዛን ለመጠበቅ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠሩም በላይ ለመስብህነትም የጎላ ጠቀመታ ይኖረዋል፡፡ 6. ሠገን ኬላሌ ሐይቅ የምገኝበት ቦታ በቡርጅ ወረዳ ክልቾ ቀበሌ ስሆን ከወረዳ ዋና ከተማ ያለው ርቀት 42ኪ.ሜ ከቡርጅ-ኮንሶ ጠጠር መንገድ ከዋናው መኪና መንገድ 1.5ኪሜ ላይ ይገኛል፡፡

መስህብነቱ ፡-የሐይቅ አቀማመጥ በሁለቱ ተራሮች መካከል የተቀመጠ በመሆኑ እይታ የሚማርክ መሆኑ በዋና/በጀልባ/ መዝናናት ለሚፈልግጉ ጎብኝዎች በሐይቁ በበመዝናናት መንፈሶችውን ያድሳሉ የተለያዩ የውሃ አካላትንም በሐይቁ ውሰጥ እየተፈጠሩ ስላሉ ዓሣ፣አዞና ጉማሬ የመጎብኜት ዕድል ይኞራሉ፡፡ በየሬሾና ጉበለቾ ተራራ ላይ ሎጂ ብገነባ ሐይቁን ሊጎበኙ ለምመጡ ቱርስቶች ማረፊያ ከመሆኑም በላይ የተሻለ እኮኖም የምያገኙበት ምቹ አጋጣም የገኛሉ፡፡ የሥራ አጥ ወጣቶች በጀልባ ስራና በዓሣ አስገራ ተግባራት ላይ በሥራ ዕደድል ፈጠራ በር የምከፍት ሆኖል፡፡ በውሃ አካላት ላይ ጥናትና ሚርምር ለሚያደርጉ ሆኖል ይቀጥላል ። ። ። ። ሪፖርተር Dambi burji