Jump to content

ቡሲሪስ

ከውክፔዲያ

ቡሲሪስ (ግሪክኛ፦ Βούσιρις) በጥንታዊ ግሪክ አፈ ታሪክሄራክሌስ ጋራ የታገለ የግብጽ ንጉሥ ነበር። የፖሠይዶንና የአኒፔ ልጅ ይባላል።

ዲዮዶሩስ ሲኩሉስ እንደ ጻፈው፣ ቡሲሪስ በጤቤስ መጀመርያው የነገሠው ፈርዖን ነበረ። በሌላ ቦታ ግን ኦሲሪስ አፒስ ቡሲሪስን በፊንቄ ላይ እንደ አገረ ገዥ ሾመው ይላል። ይህ ክፉ ንጉሥ የጎበኙትን ሁሉ አሥሮ ይገድል ነበር። ሄራክሌስ ግን በግብጽ ሲያልፍ ከርሱ አመለጠና ቡሲሪስን ሎሌዎቹንም ገደላቸው ይባላል።

ከዚህ በላይ ግሪኮች አራት ልዩ ልዩ ሥፍራዎች በግብጽ «ቡሲሪስ» ይሏቸው ነበር፤ ቡሲሪስ (ከተማ)ን ይዩ።