Jump to content

ቢትኮይን

ከውክፔዲያ
Bitcoin Logo

ቢትኮይን እስከዛሬ ከለመድነው እና ከምናውቀው የገንዘብ ስርዓት በእጅጉ የተለየ ነው። የተለመደው እና ለረዥም ዘመናት ስራ ላይ እየዋለ ያለው ገንዘብ ብሄራዊ ባንክ የሚያትመው እና የሚቆጣጠረው ፣ የራሱ የሆነ መለያ ያለው ፣ ከዚያም አለፎ የራሱ የሆነ የብር ኖት ያለው ሲሆን ቢትኮይን ግን ማዕከላዊ የሆነ የሚቆጣጠረው እና የሚያስተዳድረው አካል የለም። ገንዘቡ virtual በመሆኑ የብር ኖት እና ማከማቻ እቃ ሳያስፈልገው ግን እንደፈለጉ ስራ ላይ ማዋል የሚቻልበት ነው። ቢትኮይን በዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ማንኛውም ሰው እንደ ኮይን ቤዝ /Coin base/ ያሉ ገጾችን በመጠቀም የቢትኮይን ባለቤት መሆን ይችላል።

በማን እና እንዴት ተጀመረ?

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እንደ አውሮፓዊያኑ የዘመን ቀመር በ2008 ዓ.ም ሳቶሺ ናካሞቶ በተባለ ግለሰብ ወይም ግለሰቦች ስለ ቢትኮይን ምንነት እና አሰራር የሚገልጽ ጽሁፍ ከሶፍትዌር ፕሮግራሙ ጋር በበይነ መረብ ለአለም ይፋ ሆኗል። እስካሁን ድረስ ሳቶሺ ማን እንደሆነ ለማወቅ አልተቻለም። በርግጥ አንድ የአውስትራሊያ ዜግነት ያለው የኮምፒውተር ሳይንቲስት ሳቶሺ ማለት እኔ ነኝ ብሎ ብዙዎችን ለማጭበርበር ሙከራ አድርጓል[1]። ሳቶሺ የሚለው ስም የእውነት የአንድ ሰው ስም ይሁን ወይም ሶፍትዌሩን ያበለጸጉት ሰዎች የሚስጥር መጠሪያ ይሁን በውል የሚታወቅ ነገር የለም። የሆነው ሆኖ ስለቢትኮይን የሚገልጸው መረጃ ይፋ ከሆነ ከአመት በኋላ ስራ ላይ ውሏል።

የመጀመሪያው የቢትኮይን ብሎክ በሳቶሺ ማይን የተደረገው ጄኔሲስ ብሎክ (Genesis Block)[2][3] ይባላል። ጄኔሲስ ብሎክን ጨምሮ እስከዛሬ ድረስ የተደረጉት የቢትኮይን ሽያጭ እና ግዥዎች በሙሉ ኢንተርኔት ላይ ተመዝግበው አሉ። ስለዚህ ማንኛውም ኮምፒውተር ያለው ሰው እነዚህን ገቢ እና ወጪዎች ሁሉ ማየት ይችላል። ይህም አሰራሩ በአንድ ማዕከላዊ አስተዳደር ብቻ የተገደበ እንዳይሆን ይረዳል። የመረጃው ለማንም ሰው በየትም ቦታ እና በማንኛዉም ሰዓት ተደራሽ መሆን ማንኛውም ፈቃደኛ የሆነ ሰው ሁሉ የቢትኮይንን ግብይት እና ሽያጭ መከታተል ይችላል። ይህንን የሚያደርጉ ሰዎች ማይነርስ (Miners) በመባል ይጠራሉ። ማይነርስ እያንዳንዱን ግብይት በመመዝገብ እና ግብይቱ በአግባቡ መካሄዱን ያረጋግጣሉ። ይህም ብሎክቼይኖች በሚገባ እንዲሰሩ እና ትክክለኛ ግብይት መካሄዱን ለማጣራት ሲጠቅም በአንጻሩ ደግሞ ጊዜያቸውን ወስደው ማይን ያደረጉት ሰዎች ለሰሩበት 6.25 ቢትኮይን ይከፈላቸዋል።

ብሎኮችን ማይን ለማድረግ ከፍተኛ የፕሮሰሲንግ ያላቸው ኮምፒውተሮች ያስፈልጋሉ። ምክኒያቱም ውስብስብ የሆኑ አልጎሪዝሞችን ፕሮሰስ ለማድረግ GPU ስለሚያስፈልጋቸው ነው። ከዚህ በተጨማሪ ማይኒንግ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል ይወስዳል። ከዚህ የተነሳ የኤሌክትሪክ ዋጋ ርካሽ የሆነባቸው እና የኤለክትሪክ መቀራረጥ የማያስቸግራቸው ሀገራት ላይ ብዙ ማይነርስ አሉ። አብዛኛዎቹ ማይነሮች ቻይናዊያን ናቸው። ለዚህም ምክኒያቱ በኤሌክትሪክ ሀይል ዙሪያ ምንም ስጋት ስለሌለባቸው ነው። ነገር ግን የሀገሪቱ መንግስት ካለፈው አመት ጀምሮ ቢትኮይንን ስለከለከለ ማይነሮቹ ከቻይና ወደ ጎረቤት ሀገራት እየፈለሱ ይገኛሉ። በግል አንድን ብሎክ ማይን ለማደረግ ከሚወስደው ሰዓት አንጻር እንዲሁም በቶሎ ትርፋ ለመሆን ማይነሮች በግሩፕ በመሆን ይሰራሉ። ኮምፒውተራቸውን ዝግጁ አድርገው ይጠብቁ እና ልክ አንድ ግብይት ሲካሄድ ያንን ብሎክ ማይን በማድረግ እያንዳንዱ ሰው ለብሎክ ቼይኑ መሰራት ባደረገው አስተዋጽኦ ልክ ይከፈላዋል።

የቢትኮይን ደህንነት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እያንዳንዱ ትራንዛክሽን በአደባባይ ሁሉም ሰው ሊያየው በሚችለው መልኩ የሚቀመጥ፣ ለትክክለኛነቱ ደግሞ በተለያዩ የአለም ክፍል ያሉ ማይነሮች በየጊዜው የሚያረጋግጡት መሆኑ በመሆኑ ቢትኮይን ደህነነቱ የተጠበቀ ገንዘብ መሆን እንዲችል ይረዳዋል። ከዚህ ባለፈ እያንዳንዱ ደንበኛ ሁለት ቁልፎች አሉት። አንዱ የግል ቁልፍ (Private Key) ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የህዝብ ቁልፍ (Public Key) ነው። Private key የእያንዳንዱ ሰው የተለያየ እና በግለሰቡ ብቻ ሚስጥር ሊያዝ የሚገባው ቁልፍ ነው። Public Key ደግሞ ልክ እንደ አካውንት ቁጥር የሚያገለግል ነው። ስለዚህ ማንኛውም ተጠቃሚ የቢትኮይን ግብይት ሲያደርግ Public Keyውን ለማረጋገጥ በPrivate key sign ያደርገዋል። ይህ የግል ቁልፉ ልክ እንደመፈረም ያህል ያገለግላል። በተጨማሪም ቢትኮይን መረጃዎችን በኔትዎርክ ውስጥ የሚያስተላልፈው ክሪፕቶግራፊን በመጠቀም ነው። ክሪፕቶግራፊ ከጥንት ጀምሮ ነገስታት ለሰራዊቶቻቸው መልክት በሚያስተላልፉበት ጊዜ መልዕክታቸውን ከተፈለገው አካል በስተቀር ማንም እንዳይረዳዊ የሚያደርጉበት ስልት ነው። በአሁኑ ጊዜም ይሄ አነቱ አካሄድ ኮፕቂውተራይዝድ ሆኖ እና ዘምኖ ተግባር ላይ ይውላል። ክሪፕቶግራፊ Cryptos እና Graph ከሚሉ ሁለት የግሪክ ቃላት የመጣ ሲሆን Crypto ሚስጥር ወይም የተደበቀ ነገር እንዲሁም Graph ደግሞ ጽሁፍን ይወክላሉ። በክሪፕቶግራፊ አንድ ግልጽ የሆነ መልዕክት Encrypt በመሆን ወደ Cipher Text ይቀራል። Cipher Text የተለያዩ ፊደሎች፣ ምልክቶች እና ቁጥሮች የተዘበራረቀ ስብጥር ሲሆን ማንም ሰው መሀል ላይ ሰብሮ ቢገባ እና ይሄንን መልዕክት ቢያገኘው ምንም አይነት ትርጉም አይሰጠውም። ልክ መልዕክቱ ትክክለኛው ተቀባይ ጋር ሲደርስ ከCipher Text ወደ Plain Text Decrypt ይሆን እና ትርጉም ያለው ነገር ይሆናል።ይህም ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን አስችሎታል።

የቢትኮይን ስጋት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማንኛውም ሰው ከየትም ቦታ ሆኖ ለማንነቱ ማረጋገጫ ሳያስፈልገው አካውንት መክፈት፣ ገንዘብ መላክ፣ መሸጥ እና ማስተላለፍ መቻሉ ለወንጀለኞች ማንነታቸው ሳይታወቅ እንዳሻቸው ገንዘብ ማንቀሳቀስ እንዲችሉ አግዟቸዋል። እነዚህ ሰዎች በባንክ ቤት ገንዘብ ለማንቀሳቀስ ይችሉ ዘንድ አካውንት በሚከፍቱበት ጊዜ ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ የስራ መደብ ፣ ፎቶ እንዲሁም መሰረታዊ እነሱነታቸውን የሚያስረዳ ነገር ስለሚጠየቁ ቢትኮይንን እንደ ትልቅ በረከት በመቁጠር ገንዘባቸውን እንደ ልብ ያንቀሳቅሱበታል። በተለይም የዳርክ ዌብ /Dark Web/ ተጠቃሚዎች እንደ human trafficking እና drug deal አይነት ወንጀሎች በሰፊው ይጠቀሙበታል። ከዚህ ባለፈ ቢትኮይንን በበላይነት የሚቆጣጠር መንግስታዊ አካል አለመኖሩ ለመንግስታዊ አስተዳደር ትልቅ ፈተናን አምጥቷል። ተደራሽነቱ ሰፍቶ እና የአለም ህዝብ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የዚህ ስራዓት ተጠቃሚ ከሆኑ የሀይል ሚዛንን ከመንግስታዊ አስተዳደር ይነጥቃል፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውንም በእጅጉ ይቀይራል። ይሄም ይዞት የሚመጣው የራሱ የሆነ መልካም እና ክፉ አድሎች ይኖሩታል።

ቢትኮይን አሁን ላይ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

መጀምሪያ ተግባር ላይ ከዋለበት 2009 ዓ.ም አንስቶ እስካሁን ድረስ አስራ ሶስት አመታትን አስቆጥሯል። በመጀመሪያዎቹ አመታት ተቀባይነትን ያገኘው እና በሰፊው ተግባር ላይ የዋለው በጥቁር ገበያ ነጋዴዎች /Black Marketers/ ነው። ከ2013 ጀምሮ በዩናይትድ ስቴትስ የፍትህ ተቋማት እና መሰል ተቋማት ላይ ተግባር ላይ ውሏል። ከጊዜ ወደ ጊዜውም ሰዎች ስለ ቢትኮይን ያላቸው እወቀት እየጨመረ እና ተጠቃሚነትም እየጨመረ ሄዷል። በ2021 የ ኤልሳልቫዶር /El Salvador/ መንግስት ቢትኮይን በሀገሪቱ እንደ አንድ መገበያያ እንዲያገለግል አጽድቋል። በተከታዩ አመትም የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ይህንኑ አድርጓል። በቅርብ ጊዜም በሩሲያ እና በዩክሬይን መካከል በተነሳው ጦርነት ምክኒያት የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳት ገንዘብ እየተሰባሰበበት ይገኛል። ጦርነቱን ምክኒያት በማድረግ አብዛኛው የአውሮፓ ሀገራት ሩሲያ ላይ ማዕቀብ በመጣላቸው ምክኒያት ሩሲያ የነዳጅ ዘይት ምርቷ እንዳይጎዳ ለማድረግ ከዚህ ጋር ለተገናኙ ግብይቶች ቢትኮይንን እንደ ክፍያ አማራጭ መጠቀም ጀምራለች።

የቢትኮይን ዋጋ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቢትኮይን ወደ አሜሪካ ዶላር ሲመነዘር ያለው ዋጋ አንዳንድ ጊዜ ከፍተኛ ሌላ ጊዜ ደግሞ ዝቅተኛ ይሆናል። ለዚህም የተለያዩ ምክኒያቶች አሉት። የወቅቱ የኢንፍሌሽን ሁኔታ፣ አለም አቀፋዊ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ፣ እንደ ኮሮና ቫይረስ ያሉ ድንገተኛ አለም አቀፋዊ ተጽዕኖ ያላቸው ክስተቶች ይጠቀሳሉ። በ2011 የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ከ0.3 የአሜሪካ ዶላር ጋር እኩል ነበር። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በዚያው አመት ከ 32 ዶላር እኩል ነበር ብዙም ሳይቆይ ወደ ሁለት ዶላር ወርዶ ነበር። ይሄ ቪዲዮ በሚዘጋጅበት በአሁኑ ጊዜ የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ከ 19,922.3 ዶላር ጋር እኩል ነው።

ቀደም ብለን እንደጠቀስነው የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ይጨምራል ይቀንሳልም። ነገር ግን በግልጽ መናገር እንደሚቻለው ቢትኮይን በፊት ከነበረበት 0.3 ዶላር ተነስቶ አሁን ላይ ወደ 19,000 – 20,000 ባለው ከፍ እና ዝቅ እያለ ይገኛል። ከዚህ በግልጽ መረዳይ የሚቻለው የቢትኮይን ዋጋ በጥቅሉ ከፍተኛ የሚባል ጭማሬ እንዳሳየ ነው። በ2010 ግንቦት ወር ላይ አንድ ጄረሚ ስተርዲቫንት /Jeremy Sturdivant/ የተባለ የ19 አመት ወጣት አንድ ማስታወቂያ ያያል። በማስታወቂያው ላይ አንድ ግለሰብ ፒዛ ቤቱ ድረስ ላመጣለት ሰው 10,000 ቢትኮይን እንደሚከፍለው ይገልጻል። ያን ጊዜ 10,000 ቢትኮይን ማለት 41 ዶላር ነበር። ይሄም በአሁኑ ጊዜ ካለው የቢትኮይን ዋጋ ጋር ሲሰላ 19,922,300,000 ጋር እኩል ነው። በርግጥ ጄረሚ ገንዘቡን አላስቀመጠውም። ቢያስቀምጠው ኑሮ ቢሊዮነር ሊሆን እንደሚችል ግልጽ ነው።ስለዚህ ዛሬ ላይ የምትገዛ አንዲት ቢትኮይን ወደፊት በብዙ ዶላሮች ትመነዘራለች ማለት ነው።

  1. ^ https://www.euronews.com/next/2021/12/09/computer-scientist-claiming-to-be-bitcoin-creator-satoshi-nakamoto-wins-50bn-crypto-disput
  2. ^ http://blockexplorer.com/block/000000000019d6689c085ae165831e934ff763ae46a2a6c172b3f1b60a8ce26f
  3. ^ http://blockexplorer.com/block/000000000019d6689c085ae165831e934ff763ae46a2a6c172b3f1b60a8ce26f