Jump to content

ባህረ ሀሳብ

ከውክፔዲያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተውሃዶ ቤ/ክ በብቸኝነት ከምትታወቅባቸው ኣንዱ የራስዋ የሆነ የዘመን ኣቆጣጠር ወይም ባሕረ ሐሳብ መኖርዋ ነው። ይህውም ከዓለም የተለየች እንድትሆን ኣስችሏታል። ይህም ባሕረ ሐሳብ ለድሜጥሮስ በገለጸለት መሰረት በየጊዜው በተነሱ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ ቆይቷዋል። በኣሁኑ ወቅት ዘመኑ የመረጃ ዘመን በመሆኑና ሊቃውንቱ ሳያልፉ ቴክኖሎጂውን በመጠቀም መስራት ከሚኖርብን ኣያሌ መንፈሳውያን ስራዎች ውስጥ ባሕረ ሐስብ አንዱ ነው። ምክንያቱም የአሁኑ ትውልድ በቀላሉ ሊረዳው ባለመቻሉ ማወቅና መረዳት እየፈለገ ከቁጥሩ ስሌት ረቂቅነት ኣንፃር ብዙ ሲቸገር ይታያል። ስለሆነም በዚህና በተመሳሳይ ጽሁፎች የተቻለንን ለማሳወቅ እንሞክራለን።[1]

የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  1. አዲሱ ዓመት በየትኛው ወንጌላዊ እንደሚሰየም

ዘመኑ: ዘመነ ማቴዎስዘመነ ማርቆስዘመነ ሉቃስ፣ ወይም ዘመነ ዮሐንስ መሆኑን ለማወቅ በመጀመሪያ ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረውን 5500 ዘመንን እና ከክርስቶስ ልደት በኋላ ለማስላት (ለማወቅ) የምንፈልገውን ዓመተ ምህረት እንደምራለን። ከዚያ ድምሩን ለ4 እናካፍላለን። ወይም በቀላሉ ከክርስቶስ ልደት በኋላ የምንፈልገውን ዓመተ ምህረት ለ4 አካፍለን ቀሪው (1 ከሆነ ዘመነ ማቴዎስ፣ 2 ከሆነ ዘመነ ማርቆስ፣ 3 ከሆነ ዘመነ ሉቃስ፣ 0 (ዜሮ) ከሆነ ወይም ቀሪ ከሌለው ዘመነ ዮሐንስ) ይባላል። ምሳሌ፦ 2009ን ብንወስድ 5500+2009= 7509 ይሆናል። ለ4 ስናካፍለው 7509/4 = 1877 ደርሶ ቀሪ 1 ይሆናል። ወይም በቀላሉ መንገድ 2009/4 = 502 ደርሶ ቀሪ 1 ይሆናል። ስለዚህ በ2009 ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ ነው።

  1. አዲሱ ዓመት የሚውልበት ዕለት

ሰኞማክሰኞረቡዕሐሙስአርብቅዳሜ፣ ወይም እሁድ መሆኑን ለማወቅ አሁንም በመጀመሪያ ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረውን 5500 ዘመንን እና ከክርስቶስ ልደት በኋላ ለማስላት (ለማወቅ) የምንፈልገውን ዓመተ ምህረት እንደምራለን። ከዚያ ድምሩን ለ4 እናካፍልና ድርሻውን ከመጀመሪያው ድምር ላይ እንደምረዋለን። ከዚያ ድምሩን ለ7 ስናካፍል ቀሪው (0 ከሆነ ሰኞ፣ 1 ከሆነ ማክሰኞ፣ 2 ከሆነ ረቡዕ፣ 3 ከሆነ ሐሙስ፣ 4 ከሆነ አርብ፣ 5 ከሆነ ቅዳሜ፣ 6 ከሆነ እሁድ) ዕለት መስከረም 1 ቀን ይሆናል። ምሳሌ፦ 2009ን እንውሰድ 5500+2009=7509 ከዛም 7509/4 = 1877 (ድርሻ ነው) ዕለቱን ለማወቅ 7509+1877=9386 ይህንን ለሰባት እናካፍለው 9386/7=1340 ቀሪ 6 ነው። ስለዚህ በ2009 ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ ዕለቱ ዕለተ እሁድ ይሆናል።[2] ለማረጋገጥ የፈለጉትን ዓመተ ምህረት እና ዕለት ይሞክሩት!!!

ተጨማሪ መረጃዎችም ኣሉ። [3]

ማመዛገቢያዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  1. ^ W/Silassia Kidanu, Semire (29/07/2016). Bahire Hasab. Ethiopian Orthodox Tewahido Church. pp. 1-6. 
  2. ^ www.zabraham.blog.com
  3. ^ https://archive.today/20121205071902/http://www.ethiopic.com/calendar/ethiopic.htm]