Jump to content

ባህር ዛፍ

ከውክፔዲያ
ባህር ዛፍ

ባህር ዛፍ (Eucalyptus) በተፈጥሮው ከአውስትራሊያ የሚገኝ አበባ ሚያብብ የዛፍ ወገን ነው። በአለም ላይ 700 አይነት የባህር ዛፍ ዝርያዎች አሉ፣ ከነዚህ ውስጥ 15ቱ ከአዉስትራሊያ ውጭ በተፈጥሮ ሲገኙ ከ700ው 9ኙ ዘር ብቻ አውስትራሊያ ውስጥ በተፈጥሮ አይገኝም። በኢትዮጵያ በተለይ የታወቁት፦

ናቸው።

አዲስ አበባ ከተማ ዳግማዊ ምኒልክ የባህር ዛፍ ፍሬ አስመጥተው ካስተከሉ በኋላ ይሄ አዲስ ዕጽ ዓየሩ ተስማምቶት ለከተማዋ የአረንጓዴ መቀነት ይመስል በጥቂት ዓመታት አሸበረቃት። በ፲፱፻፵ ዎቹ ይሄ መቀነት እስከ አርባ ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት በመያዙ ከተማዋን በሰፊው "Eucalyptopolis" (የባህር ዛፍ ከተማ) የተባለ ቅጽል ስምን አትርፎላት ነበር።[1]

በአሁኑ ወቅት ባህር ዛፍ አለም አቀፍ ተፈላጊነት አግኝቷል። ይህም የሆነበት ምክንያት

  • ቶሎ በማደግ አስፈላጊ እንጨት ይሰጣል
  • የዛፉ ዘይት ለጽዳት እና እንዲሁም በራሪ ትንኞችን ለማባረር እንዲሁም ለመግደል ይረዳል
  • አልፎ አልፎ ለወባ ትንኝ ማደግ ምቹ የሆኑ አረንቋወችን ለማድረቅ ይረዳል።

ሆኖም ግን ባህር ዛፍ ከላይ ለተጠቀሱት አላማወች ቢያገለግልም ትልቁ ችግሩ ውሃ በጣም ይወዳል። ስለሆንም እርሱ በተተከለበት ሌሎች አትክልቶች የማደግ እድላቸው ዝቅተኛ ነው። ኢትዮጵያም ውስጥ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ምንጮችን እንዳደረቀ መረጃ አለ።

አፄ ምኒልክ አዲስ አበባ የመንግሥታቸው መቀመጫ እንድትሆን መወሰን የቻሉት ከአውስትራሊያ የመጣው ባህር ዛፍ ለማገዶ ችግር አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጥ ሆኖ በመገኘቱ ነበር፡፡

ባህር ዛፍን ጨምሮ የደን ልማት ለአገርና ለሕዝብ ያለውን ጠቀሜታ የተረዳው የአፄ ኃይለሥላሴም መንግሥት ከሐምሌ 9 ቀን 1948 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ የደን በዓል ቀን ሆኖ እንዲከበር ወስኖ እንደነበር “ፍሬ ከናፍር 3ኛ መፅሐፍ” በሚል ርእስ በ1957 ዓ.ም የታተመው ጥራዝ ውስጥ ታሪኩ ተዘግቧል፡፡

በዘመኑ በሆለታ ከተማ በተከበረው የደን በዓል ቀን ላይ ንግግር ያደረጉት የእርሻ ሚኒስትሩ ባላምባራስ ማህተመሥላሴ ወልደመስቀል ለበዓሉ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ችግኝ መዘጋጀቱን፣ ችግኞቹን መትከያ 120,000 ሜትር ካሬ መሬት መሰናዳቱን፣ ከሚተከሉትም ችግኞች የሚበዙት ከውጭ አገር የመጡ መሆናቸውን፣ ለፕሮጀክቱ መሳካት የተባበሩት መንግሥታት የእርሻና የምግብ ድርጅት እገዛ ማድረጉን ገልፀዋል፡፡

የደን በዓል ቀን ተቆርጦለት መከበር ከመጀመሩ በፊት በተሰራው ሥራም ወደ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ እፅዋት መተከላቸውን ያመለከቱት አፄ ኃይለሥላሴ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር “አስፈላጊውን ችግኝ ምንም እንኳን የእርሻ ሚኒስቴር እንዲሰጥ ቢታዘዝ ከእርሻ ሚኒስቴር እየተወሰዱ የሚተከሉት ዛፎች ሁሉ የባለርስቱ ንብረት ናቸውና ይህን ሥራ ያለማቋረጥ በትጋት መፈፀም ግዴታ ነው፡፡”

የእርሻ ሚኒስትሩና ንጉሠ ነገሥቱ “በሆለታ ዛፍ ተክል መፈተኛ ጣቢያ” ተገኝተው ካደረጉት ንግግር መረዳት እንደሚቻለው ካለፈው ብቻ ሳይሆን ዛሬ ከሚታየውም እውነታ ጋር እያያዝን ብዙ ጥያቄ እንድናነሳ ግድ የሚሉ መረጃዎች ሰፍረዋል፡፡

ለሐምሌ 9 ቀን 1948 ዓ.ም የደን በዓል ቀን እንዲተከሉ የቀረቡት እፅዋት የሚበዙት ከውጭ የመጡ ከሆነ አሁን ባህር ዛፍን በአገር በቀል እፅዋት የመተካቱ ተግባር በዚያ ዘመን በብዛት ወደ አገር ውስጥ የገቡትንም ያካትት ይሆን? “የሆለታ ዛፍ ተክል መፈተኛ ጣቢያ” ጥናትና ምርምር ዛሬ ተግባራዊ እየሆነ ላለው ተግባር ምን አስተዋፅኦ አድርጓል? ለ1948 ዓ.ም የደን በዓል ቀን የተባበሩት መንግሥታት የእርሻና የምግብ ድርጅት እገዛ ዛሬም ለተመሳሳይ ዓላማ እያገኘናቸው ካሉ እርዳታዎች ጋር ስናነፃፅረው ስለነገ መድረሻችን ምን ያሳየናል? በዘመኑ አፄ ኃይለሥላሴና የእለቱ የክብር እንግዶች የተከሏቸው ችግኞች አሁን ይኖሩ ይሆን?

ዛፍ እንደ ቅርስ፣ እንደ ሐውልት ታሪክ ማስተላለፊያ ሆኖም አገልግሏል፡፡ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሕንፃ ፊት ለፊት በ”አፍሪካ ፓርክ” ውስጥ ያሉት እፅዋት በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ለአፍሪካ አንድነት ስብሰባ ወደ አዲስ አበባ የመጡ የአህጉሪቱ መሪዎች የተከሏቸው ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ሳይሆን በክልል ከተሞችም በታዋቂ ሰዎች የተተከሉ እፅዋት እንዳሉ መረጃ ከሚሰጡን መፃሕፍት አንዱ የሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው “ዐፈር ያነሳ ሥጋ” የግጥም ስብስብ መድብል ነው፡፡

በ1964 ዓ.ም የታተመው ይህ መፅሐፍ ጥር 24 ቀን 1961 ዓ.ም የተፃፈና “አንድ ያልታደለ ዛፍ” የሚል ርእስ ያለው ግጥምን ይዟል፡፡ በዘመኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ሆነው ያገለግሉ የነበሩት ኡ፡ታንት በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በደብረዘይት ከተማ የዛፍ ተከላ ሥነ ሥርዓት አከናውነዋል

የቅጠሉ ጥቅሞች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የቅጠሉ ተናኝ ዘይት ለጉንፋን ይረዳል። ትንኞችንም ለማባረር ይረዳል። ቅጠሎቹ በወለሎች ላይ የሚዘረጉ ናቸው። የቅጠሉም ውጥ ለማጅራት ገትር ተጉመጠመጠ።[2]

አውስትራሊያ ለቅጠሉ ሱስነት ያለ ኪሴ እንስሳ ወይም «ኮዋላ» ይገኛል።

  1. ^ History of Ethiopian Urbanization http://www.macalester.edu/courses/geog61/kshively/development.html/ Archived ዲሴምበር 20, 2010 at the Wayback Machine
  2. ^ አማራ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.

http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=3547:%E1%8B%A8%E2%80%9D%E1%8B%9B%E1%8D%8D%E2%80%9D-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E2%80%9C%E1%89%A3%E1%88%85%E1%88%AD-%E1%8B%9B%E1%8D%8D%E2%80%9D-%E1%8A%90%E1%8C%88%E1%88%AD