ባለአንጓ ትሎች

ከውክፔዲያ

ባለአንጓ ትሎች / ˈænəlɪdz / ( አኔሊዳ / ə ˈ nëlɪdə / ፣ በላቲን አኔሉስ _ _ _ _ anellus _ ፣ “ትንሽ ቀለበት” ማለት ነው። ) ፣እንዲሁም ባል ክፍልፍል ትሎች በመባል የሚታወቁ ሲሆን "ragworms"፣ የመሬት ትሎችን እና አልቅቶችን ጨምሮ ከ22,000 በላይ አሁንም ያሉ ዝርያዎች በስሩ ያሉት ግዙፍ ክፍልስፍን ነው። ዝርያዎቹ በተለያዩ ስርአተ ምህዳሮች ውስጥ ተላምደው ይገኛሉ። አንዳንዶቹ ማእበል እና ፍልውሃ ባለባቸው በባህር አካባቢዎች፣ ሌሎች በንጹህ ውሃ ውስጥ ፣ እና ሌሎች ደግሞ እርጥበት ባለው የየብስ አካባቢዎች ውስጥ ይገኛሉ።

ባለአንጓ ትሎች በሁለትዮሽ የተመጣጠነ ፣ ስሉስድርባዊ ፣ ወናአካላዊ ፣ ኢደንደሴ ዘአካላት ናቸው። ለእንቀስቃሴ ደግሞ ፓራፖዲያም አላቸው። አብዛኛዎቹ የመማሪያ መፃህፍት አሁንም ባህላዊውን ክፍፍል ወደ ፖሊቼቶች (ሁሉም የባህር ውስጥ ማለት ይቻላል)፣ ኦሊጎቼትስ (የምድር ትሎችን የሚያጠቃልሉ) እና ሊች -መሰል ዝርያዎችን ይጠቀማሉ። እ.ኤ.አ. ከ1997 ጀምሮ ክላዲስቲካዊ ምርምር ይህንን እቅድ በከፍተኛ ደረጃ ቀይሮታል፣ ሊችን እንደ ኦሊጎቼቶች ንዑስ ቡድን እና ኦሊጎቼቶችን ደግሞ እንደ ፖሊቼቶች ንዑስ ቡድን በመመልከት። በተጨማሪም ፖጎኖፎራ, ኢቺዩራ እና ሲፑንኩላ, ቀደም ሲል እንደ የተለዩ ክፍለስፍን ተደርገው ይታዩ የነበሩት፣ አሁን እንደ የፖሊቼቶች ንዑስ ቡድኖች ተደርገው ይቆጠራሉ። ባለአንጓ ትሎች የፕሮቶስቶምስ ዛጎል ለበሶችን ፣ ብራቺዮፖዶችን እና ኔመርቴያዎች የሚያጠቃልለውየሎፎትሮኮዞኣ አባላት ተደርገው ይወሰዳሉ።

የመሠረታዊ የባለአንጓ ትሎች ቅርጽ ብዙ አንጓዎችን ያካትታል። እያንዳንዱ አንጓ አንድ አይነት የአካል ክፍሎች ይሉት እና በአብዛኛዎቹ ፖሊቼቶች ውስጥ ብዙ ዝርያዎች ለመንቀሳቀስ የሚጠቀሙባቸው ጥንድ ፓራፖዲያ አላቸው። ምክፈሎች የበርካታ ዝርያዎችን አንጓዎች ይለያሉ፣ ነገር ግን በሌሎች ውስጥ በደንብ አልተገለጹም ወይም የሉም፤ በኢኩሪያ እና በኦቾሎኒ ትሎች ምንም ግልጽ የመለያየት ምልክቶች አያሳዩም። በደንብ የዳበረ ምክፈል ባላቸው ዝርያዎች ውስጥ, ደሙ ሙሉ በሙሉ በደም ሥሮች ውስጥ ይሰራጫል፣ እና በእነዚህ ዝርያዎች ከፊት ለፊት ባሉት አንጓዎች ውስጥ ያሉት የደምስሮች ብዙውን ጊዜ እንደ ልብ በሚሠሩ ጡንቻዎች የተገነቡ ናቸው። የእንደዚህ ዓይነቶቹ ዝርያዎች ምክፈሎች የእያንዳንዱን አንጓ ቅርጽ በመቀያየር በሞገደ ትፊት(በሰውነት ውስጥ በሚያልፉ “ሞገዶች”) አማካኝነት እንቅስቃሴን ለማሳለጥ ወይም ከፍና ዝቅ እያሉ የፓራፖዲያን ውጤታማነት ያሻሽላሉ። ምክፈሎች ባልተሟሉላቸው ወይም በሌሉአቸው ዝርያዎች ደሙ ምንም አይነት ፓምፕ ሳይኖር በዋናው የሰውነት ክፍተት ውስጥ ይሰራጫል። እና ብዙ አይነት የእንቅስቃሴ ስልቶች አሉ - አንዳንድ እራሳቸውን የሚቀብሩ ዝርያዎች ጉሮሯቸውን በመገልበጥ እራሳቸውን በደለል ውስጥ ይጎትታሉ።

የምድር ትሎች እንደ ታዳኝ በመሆንም ሆነ በአንዳንድ ክልሎች አፈርን በማበልጸግ እና አየር በመስጠት በምድር ላይ ያሉ የምግብ ሰንሰለቶችን የሚደግፉ ኦሊጎቼቶች ናቸው። በባህር ዳርቻ አካባቢ ከሚገኙት የሁሉም ዝርያዎች አንድ ሶስተኛውን ሊይዝ የሚችሉት እራሳቸውን የሚቀብሩ የባህር ፖሊቼቶች ውሃ እና ኦክሲጅን ወደ ባህር ወለል ውስጥ ዘልቀው እንዲገቡ በማድረግ የስነ-ምህዳር እድገትን ይደግፋሉ። ባለአንጓ ትሎች የአፈርን ለምነት ከማሻሻል በተጨማሪ ሰዎችን እንደ ምግብነትና ማጥመጃነት ያገለግላሉ። የሳይንስ ሊቃውንት የባህር እና የለጋ ውሃ ጥራትን ለመከታተል ባለአንጓ ትሎችን ይመለከታሉ። ምንም እንኳን የተበከል ደምን ማስወገድ በዶክተሮች ከቀድሞው በቀነሰ መልኩ ጥቅም ላይ የሚውል ቢሆንም፣ ባለፉት ጥቂት ምዕተ ዓመታት ውስጥ ለዚህ ዓላማ ከመጠን በላይ በመሰብሰብ ምክኒያት አንዳንድ የሊች ዝርያዎች ለመጥፋት የተቃረቡ ዝርያዎች ተደርገው ይወሰዳሉ። የራግዎርሞች መንጋጋዎች ለየት ባለመልኩ የጥንካሬ እና ቀላልነት ጥምረት ስለሚሰጡ አሁን በመሐንዲሶች እየተጠና ነው።

ባለአንጓ ትሎች ለስላሳ አካል ያላቸው በመሆኑ ቅሪተ አካላቸው እምብዛም አይገኙም በአብዛኛው መንጋጋ እና አንዳንድ ዝርያዎች ያወጡት በማዕድን የተሰሩ ቱቦዎች። ምንም እንኳን አንዳንድ ዘግይተው የነበሩት የኤዲካራን ቅሪተ አካላት ባለአንጓ ትሎችን ሊወክሉ ቢችሉም፣ በአስተማማኝ መልኩ የታወቀው እጅግ ጥንታዊው ቅሪተ አካል የመጣው ከ 518 ከሚሊዮን አመታት በፊት ቀደም ባለው የካምብሪያን ዘመን አካባቢ ነው። የአብዛኞቹ ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ፖሊቼቶች ቡድኖች ቅሪተ አካላት የታዩት በካርቦኒፌረስ ዘመን መገባደጃ ላይ ከ299 ሚሊዮን ዓመታት በፊት ነበር።  የቅሪተ አካል ጥናት ባለሙያዎች ከኦርዶቪሻን ዘመን አጋማሽ ከ472 እስከ 461 ሚሊዮን ዓመታት በፊት የሆኑ አንዳንድ የአካላት ቅሪቶች የኦሊጎቼቶች ቅሪት አካላት መሆናቸው እና አለመሆናቸው ላይ አይስማሙም። የመጀመሪያዎቹ የማያከራክሩ የቡድኑ ቅሪተ አካላት ከ66 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በጀመረው በፓሌኦጂን ዘመን ውስጥ ይታያሉ።[1]

ስርአተ ምደባ እና ተለያይነት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከ22,000 በላይ በአሁኑ ጊዜ የሚገኙ የባለአንጓ ትሎች ዝርያዎች አሉ [2] [3] መጠናቸው ከማይክሮስኮፓዊ እስከ አውስትራሊያ ግዙፍ ጂፕስላንድ የምድር ትል እና አሚንታስ መኮንጊያንስ ሁለቱም እስከ 3 ሜትር (9.8ጫማ) ማደግ የሚችሉ፣ [3] [4] [5] ወደ 6.7 ሜትር (22 ጫማ) ማደግ እስከሚችለው ትልቁ ባለአንጓ ትል፣ ማይክሮኬተስ ራፒ ድረስ ። ምንም እንኳን ከ 1997 ጀምሮ የተደረጉ ጥናቶች የሳይንስ ሊቃውንት ስለ annelids የዝግመተ ለውጥ የቤተሰብ ዛፍ ያላቸውን አመለካከት በእጅጉ ቢለውጡም [6] [7] አብዛኞቹ የመማሪያ መጽሃፎች በሚከተሉት ንዑስ ቡድኖች የሚከፍለውን ባህላዊውን ስርአተ ምደባ ይጠቀማሉ፡- [4] [8]

  • ፖሊቼቶች (12,000 ገደማ ዝርያዎች [9] ). ስማቸው እንደሚያመለክተው በአንድ አንጓ ብዙ ቼቴዎች ("ፀጉሮች") አሏቸው። ፖሊቼቶች እንደ እጅና እግር የሚሠሩ ፓራፖዲያ ፣ ደግሞም ኬሞሴንሰር ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ኒውካል አካላት አሏቸው። [10] ምንም እንኳን ጥቂት በለጋ ውሃ ውስጥ የሚኖሩ፣ ደግሞ በጣም ጥቂት በመሬት ላይ የሚኖሩ ዝርያዎች ቢኖሩም፤አብዛኛዎቹ የባህር ውስጥ እንስሳት ናቸው። [11]
  • ክላይተሌቶች(ወደ 10,000 ገደማ ዝርያዎች [12] ))እነዚህ በእያንዳንዱ አንጓ ጥቂት ቼቴ ሊኖራቸው ይችላል ወይም ወይም ደግሞ ምንም አይኖራቸውም። እና ደግሞ ምንም አይነት ፖሊቼቶችኒውካል አካላት ወይም ፓራፖዲያ የላቸውም። ሆኖም ግን፣ ልዩ የሆነ የዳበሩ እንቁላሎች እስኪፈለፈሉ ድረስ የሚያከማች እና የሚመግብ ኮኮን የሚያመርት በአካላቸው ዙሪያ የቀለበት ቅርጽ ያለው ክላይቴለም (" ፓኬት ኮርቻ ") የተሰኘ የመራቢያ አካል አላቸው። [13] [14]

ወይም በሞኒሊጋስትሮድስ ውስጥ ለፅንሶች ምግብን የሚያቀርቡ ባለአስኳል እንቁላሎች አሉ። . [12] ክላይተሌቶች በንዑስ የተከፋፈሉ ናቸው [15]ኦሊጎቼቶች (" ጥቂት ፀጉሮች ያሉሏቸው")፣የምድር ትሎችየሚያጠቃልል ነወ።

  • ኦሊጎቼቶች በአፋቸው ጣራ ላይ የሚለጠፍ ንጣፍ አላቸው። [16] አብዛኛዎቹ አካላቸውን የሚቀብሩ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የበሰበሱ ኦርጋኒክ ቁሶችን የሚመገቡ ናቸው። [17]
  • ሂሩዲኔያ ፣ የስሙ ትርጉሙ " የአልቅት ቅርጽ ያለው" ማለት ሲሆን በጣም የታወቁት አባላቶቹ አልቅቶች ናቸው። [16] የባህር ውስጥ ዝርያዎቻቸው በአብዛኛው ደም የሚመጥጡ (በተለይም በአሳ ላይ)ጥገኛ ተውሳኮች ሲሆኑ አብዛኛዎቹ የለጋ ውሃ ዝርያዎች አዳኞች ናቸው። [17] በሁለቱም የሰውነታቸው ጫፍ ላይ የመምጠጫ አካል ያላቸው ሲሆን፣ እነዚህን አካላት እንደ ኢንች ትሎች ለመንቀሳቀስ ይጠቀሙባቸው። [18]


አርኪአኔሊዳዎች በባህር ደለል ቅንጣጢቶች መካከል ባለው ክፍተት ውስጥ የሚኖሩ ጥቃቅን ባለኣንጓ ትሎች ሲሆኑ ቀለል ባለ የሰውነት አወቃቀራቸው ምክንያት እንደ የተለየ መደብ ተደርገው ይቆጠሩ ነበር፣ አሁን ግን እንደ ፖሊቼቶች ተደርገው ተወስደዋል። [19] ሌሎች አንዳንድ የእንስሳት ቡድኖች በተለያዩ መንገዶች ተከፋፍለው ነበር፣ አሁን ግን በሰፊው እንደ ባለአንጓ ትሎች ተቆጥረዋል።

  • ፖጎኖፎራ / ሲቦግሊኒዴ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኙት በ 1914 ነበር። እናም ለይቶ ለማወቅ የሚቻል አንጀት የሌላቸው መሆኑ ለምደባ አስቸጋሪ ሆኗል። ፖጎኖፎራ ተብለው እንደ የተለየ ክፍለስፍን ወይም ደግሞ ፖጎኖፎራ እና ቬስቲሜንቲፌራ ወደሚባሉ ሁለት ክፍለስፍኖች ተመድበው ነበር። በቅርብ ጊዜ በፖሊቼቶች ውስጥ ሲቦግሊኒዴ አስተኔ ተብለው በድጋሚ ተመድበዋል። [20] [21]


ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Renne, Paul R.; Deino, Alan L.; Hilgen, Frederik J.; Kuiper, Klaudia F.; Mark, Darren F.; Mitchell, William S.; Morgan, Leah E.; Mundil, Roland; Smit, Jan (7 February 2013). "Time Scales of Critical Events Around the Cretaceous-Paleogene Boundary" (PDF). Science. 339 (6120): 684–687. Bibcode:2013Sci...339..684R. doi:10.1126/science.1230492. PMID 23393261. S2CID 6112274.
  2. ^ Rouse, G. W. (2002). "Annelida (Segmented Worms)". Encyclopedia of Life Sciences. John Wiley & Sons. doi:10.1038/npg.els.0001599. ISBN 978-0470016176. 
  3. ^ Blakemore, R.J. (2012). Cosmopolitan Earthworms. VermEcology, Yokohama.. 
  4. ^ Ruppert, E. E. (2004). "Annelida". Invertebrate Zoology. Brooks / Cole. ISBN 978-0-03-025982-1. 
  5. ^ Lavelle. Diversity of Soil Fauna and Ecosystem Function. 
  6. ^ Struck. Annelid phylogeny and the status of Sipuncula and Echiura. doi:10.1186/1471-2148-7-57. 
  7. ^ Hutchings (2007). Book Review: Reproductive Biology and Phylogeny of Annelida. doi:10.1093/icb/icm008. 
  8. ^ Rouse, G. (1998). "The Annelida and their close relatives". Invertebrate Zoology. Oxford University Press. ISBN 978-0-19-551368-4. 
  9. ^ Rouse, G. W. (2002). "Annelida (Segmented Worms)". Encyclopedia of Life Sciences. John Wiley & Sons. doi:10.1038/npg.els.0001599. ISBN 978-0470016176. 
  10. ^ Ruppert, E. E. (2004). "Annelida". Invertebrate Zoology. Brooks / Cole. ISBN 978-0-03-025982-1. 
  11. ^ Rouse, G. (1998). "The Annelida and their close relatives". Invertebrate Zoology. Oxford University Press. ISBN 978-0-19-551368-4. 
  12. ^ Blakemore, R.J. (2012). Cosmopolitan Earthworms. VermEcology, Yokohama.. 
  13. ^ Rouse, G. (1998). "The Annelida and their close relatives". Invertebrate Zoology. Oxford University Press. ISBN 978-0-19-551368-4. 
  14. ^ Ruppert, E. E. (2004). Invertebrate Zoology. Brooks / Cole. 
  15. ^ Ruppert, E. E. (2004). "Annelida". Invertebrate Zoology. Brooks / Cole. ISBN 978-0-03-025982-1. 
  16. ^ Ruppert, E. E. (2004). "Annelida". Invertebrate Zoology. Brooks / Cole. ISBN 978-0-03-025982-1. 
  17. ^ Rouse, G. (1998). "The Annelida and their close relatives". Invertebrate Zoology. Oxford University Press. ISBN 978-0-19-551368-4. 
  18. ^ Ruppert, E. E. (2004). Invertebrate Zoology. Brooks / Cole. 
  19. ^ Rouse, G. (1998). "The Annelida and their close relatives". Invertebrate Zoology. Oxford University Press. ISBN 978-0-19-551368-4. 
  20. ^ Rouse, G. (1998). "The Annelida and their close relatives". Invertebrate Zoology. Oxford University Press. ISBN 978-0-19-551368-4. 
  21. ^ Halanych (2002). Unsegmented Annelids? Possible Origins of Four Lophotrochozoan Worm Taxa. pp. 678–684.