ባልታዊ ቋንቋዎች

ከውክፔዲያ
የባልታዊ ቋንቋዎች ሥፍራ

ባልታዊ ቋንቋዎች ወይም ባልቲክ ቋንቋዎች አንድ የሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ቅርንጫፍ ናቸው። ከስላቫዊ ቋንቋዎች ጋራ አንድላይ የባልቶ-ስላቫዊ ቋንቋዎች ቅርንጫፍ ይሠራሉ።

ባልታዊ ቋንቋዎች ሁሉ ከቅድመ-ባልትኛ ደረሱ፤ እሱም ከቅድመ-ባልቶ-ስላቭኛ እንደ ደረሰ ይታስባል።

የባልታዊ ቅርንጫፍ ሁለት ክፍሎች ምሥራቅ ባልታዊ እና ምዕራብ ባልታዊ ነበሩ። በአሁኑ ሰዓት ምሥራቅ ባልታዊ ብቻ ቆይቷል።