Jump to content
አማርኛ ውክፔድያን አሁኑኑ ማዘጋጀት ትችላላችሁ - ተሳተፉበት!

ባልጩት ዋቅላሚዎች

ከውክፔዲያ
ባልጩት ዋቅላሚዎች
ባልጩት ዋቅላሚዎች

ባልጩት ዋቅላሚዎች “diatoms” ባሲላሮፋይታዎች የሚባሉት ናቸው፡፡ በአስደናቂ ሁኔታ ውብ የሆነ የሲሊካ ቅርፊት ወይም ፍሩስቱል “frustules” ያላቸው ሲሆን ባልጩት ዋቅላሚዎች በጣም ከሚወደዱ ደቂቅ ቅሪተዓካላት ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ደግሞም እጅግ በጣም አስፈላጊ የሚባሉ የውሃ ውስጥ ደቂቅ አካላት ናቸው፡፡ ጨዋማ በሆኑ እና ባልሆኑ የውሃ ስርዓተ ምህዳሮች ውስጥ በመንሳፈፍ እንዲሁም በደለል ውስጥ እጅግ በስፋት ይገኛሉ፡፡ በብርሃን አስተፃምሮ ምግብ ማምረት የሚችሉ በመሆናቸው ለውሃ ውስጥ ፍጥረታት እንደ ምግብነት ያገለግላሉ፡፡ እንደውም አንዳንዶቹ በአፈር ውስጥና እርጥበታማ በሆኑ ሳረንስቶች ላይ ይገኛሉ፡፡[1]

  1. ^ https://ucmp.berkeley.edu/chromista/bacillariophyta.html