ቤሉ-ባኒ

ከውክፔዲያ
(ከቤሉባኒ የተዛወረ)

ቤሉ-ባኒ ወይም ቤል-ባኒ ከ1672 እስከ 1662 ዓክልበ. ('ኡልትራ አጭሩ' አቆጣጠር) የአሦር ንጉሥ ነበረ።

የአሦር ነገሥታት ዝርዝር የተባለው ሰነድ እንደሚለው፣ ለ10 ዓመታት ከአሹር-ዱጉልና ከ፮ ሌሎች ተወዳዳሪዎች ቀጥሎ ነገሠ። ከነዚህ ፮ አንዱ የቤሉባኒ አባት አዳሲ ነበር።

ከሺህ ዓመታት በኋላ የነገሠው አስራዶን ከቤሉ-ባኒና ከአዳሲ ዘር እንደ ተወለደ ብዙ ጊዜ ይጠቅስ ነበር። ቤልባኒ አገሩን ከአሞራውያን ቀንበር እንዳስወጣው፣ መጀመርያው ኗሪ አሦራዊ ንጉሥ ይለዋል። ሆኖም የባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ብዙ ጊዜ በዚሁ ዘመን በአገሩ እንደ ዘመተ ይመስላል።

የቤል-ባኒ ልጅ ሊባያ ተከተለው።

የዓመት ስሞች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የያንዳንዱ አሦራዊ ዓመት ስም ለዚያ ዓመት የተሾመው የሊሙ ስም ነበረ። ከዚህ በታች የዓመቱ ሊሙ እና የሊሙ አባት ስም እንደ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ይዘርዝራሉ።

1671 ዓክልበ. - አያ
1670 ዓክልበ. - አዙቢያ
1669 ዓክልበ. - ኩርኩዳኒም፣ የሻማሽ-ረዒ ልጅ
1668 ዓክልበ. - ጻብሩም፣ የፑዙር-ሲን ልጅ
1667 ዓክልበ. - ሃዲዩ፣ የአሒያያ ልጅ
1666 ዓክልበ. - ዳዲያ፣ የኢዲን-ሲን ልጅ
1665 ዓክልበ. - ዛያ፣ የበላያ ልጅ
1664 ዓክልበ. - ዚዛያ፣ የአቢናራ ልጅ
1663 ዓክልበ. - አዳድ-ባኒ፣ የአዙመ ልጅ
1662 ዓክልበ. - ሐቢል-ከኑም፣ የጺሊ-እሽታር ልጅ
ቀዳሚው
አሹር-ዱጉል
የአሦር ንጉሥ
1672-1662 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሊባያ