ቤናዚር ቡቶ

ከውክፔዲያ
ቤናዚር ቡቶ በ መስከረም 2004 እኤአ

ቤናዚር ቡቶ (ስንድኛ፦ بينظير ڀُٽو, ሰኔ 21, 1953 – ታህሳስ 27, 2007 እኤአ) የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ነበረች። ቤናዚር ከ1989 እስከ 1990 አስራ አንደኛ እና ከ1993 እስከ 1996 እኤአ አስራ ሶስተኛ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆና ተሹማለች። ይህ መጀመርያ ጊዜ በታሪክ የእስልምና መንግሥት በሴት መሪ የተመራ ነበር። ቤናዚር በፓለቲካ ለዘብተኛ እና ዴሞክራሲያዊ ስርአትን ትደግፍ ነበረ። ቤናዚር በ ጥቅምት 18, 2007 እኤአ ከ ለንደን ወደ ካራሳስ አየር ማረፊያ ስደርስ ባልታወቁ ታጣቂዎች በፈንጂ ገለዋት ነበር። ነገር ግን ከስፍራው ስለወጣች ፍንዳታውን ባለማግኘቷ ልተርፍ ችላለች። በ ታህሳስ 27, 2007 እኤአ ቤናዚር በተሳካ ሁኔታ በፓኪስታን ፑንጃብ የ2008 ብሄራዊ ምርጫ ቅስቀሳ አድርጋ ከጨረሰች በኋላ ወደ አጃቢ መኪና ስትገባ በሶስት ተኳሽና በአንድ አጥፍቶ ጠፊ በፈንጂ ተገደለች። ወዲያውኑ የሷ ደጋፊዎች በቤናዚር ሞት ከፍተኛ ረብሻ አስነስቷል። አልቃይዳና ታሊባን በቤናዚር ሞት ተጠያቂ ሆነዋል።