ቤንጃሚን ፍራንክሊን

ከውክፔዲያ
ፍራንክሊን፣ 1770 ዓም ተሳለ

ቤንጃሚን ፍራንክሊን ጃንዋሪ 17 1706 እ.ኤ.አ. - አፕሪል 17 1790 እ.ኤ.አ.፦ ከአሜሪካዊ አብዮት ጀምሮ ዜግነቱ አሜሪካዊ ሲሆን የአሜሪካ 100 ዶላር ኖት ላይ በሚገኘው ምስሉ ይታወቃል። የአሜሪካ መስራች አባቶች ከሆኑ እውቅ የሃገሪቱ ሰዎች አንዱ ነው። እኚህ ሰው ለአሜሪካ ጸሃፊ፣ ፖለቲከኛ፣ ዲፕሎማት፣ ወታደር፣ ተመራማሪ፣ ፍጥረት ፈልሳፊ ወዘተ. ነበሩ።

ፍራንክሊን ስለ ኅሊና ነጻነትና ስለ ግብረ ገብ ማስተማር የነበራቸው ፍቅር ከፍተኛ ነበረ። የአሜሪካን ሕገ መንግሥት ከነደፉት ዋና ሰዎች አንዱ ነበሩ። ካስፋፉት ምሳሌዎች መሃል «የክርስቶስን አራያ ምሰል» ("Emulate Christ") አንዱ ነው።