Jump to content

ብርሃኑ ዘሪሁን

ከውክፔዲያ

ብርሃኑ ዘሪሁንኢትዮጵያውያን ደራሲያንና አንጋፋ እውቅ ጋዜጠኞች አንዱ ነው። በደርግ ዘመን እስርና እንግልት የተፈራረቁበት፣ መራራውን የዘመኑን ሥርዓትና ሳንሱር የታገለ ጀግና ነበር። ብርሃኑ ከአሥር በላይ መጻሕፍትን ጽፏል። ከነዚያም መሀል ታዋቂዎቹ ታሪካዊ ልብ ወለዶች፣ «የታንጕት ምስጢር» «ማዕበል ያብዮት ዋዜማ፣ መባቻና ማግስት»፣ የቴዎድሮስ እምባ፣ ጨረቃ ስትወጣ፣ አማኑዔል ደርሶ መልስ፣ ይገኙበታል። ባልቻ አባነፍሶ፣ ጣጠኛው ተዋንያንና ሌሎችንም ድንቅ ተውኔቶችንም ደርሶ አልፏል።