Jump to content

ብጉንጅ

ከውክፔዲያ

ብጉንጅ ብጉር መስለ የቆዳ በሽታ ፡ የቆዳ ማበጥ ወይም መደደር ነው።

ብጉንጅ/ boils ብጉንጅ አንድና ከዚያ በላይ የሆኑ የፀጉር መዉጫ ቀዳዳዎች በባክቴሪያ ምክንያት እንፌክሽን በሚፈጥርበት ወቅት ቆዳ ስር በመቆጣት፣መግል በመያዝና በማበጥ ህመም እንዲከሰት የሚያደርግ ችግር ነዉ፡፡ እብጠቱ በፍጥነት በማደግና በመግል በመሞላት የህመም ስሜቱ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ የህመሙ ምልክቶች ብጉንጅ በየትኛዉም የሰዉነት ክፍል ሊወጣ ቢችልም በብዛት ግን የሚታየዉ/የሚወጣዉ በፊት ቆዳ፣ አንገት፣ ብብት ስር፣ መቀመጫና ታፋ ላይ ነዉ፡፡ • ህመም ያለዉና ቀላ ያለ እብጠት መታየት • በእብጠቱ ዙሪያ የቀላና ያበጠ ቆዳ መታየት • እብጠቱ መግል እየሞላዉ ሲመጣ መጠኑ እየጨመረ መምጣት • ነጭ ወይም ቢጫ ነገር በእብጠቱ ጫፍ ላይ መታየት ከዚያን መፈንዳትና መግሉ መዉጣት የህክምና ባለሙያ ማይት የሚገባዎ መቼ ነዉ? የብጉንጁ መጠን አነስተኛ ከሆነ እርስዎ እራስዎ እንክብካቤ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የሚከተሉት የህመም ምልክቶች ካለዎት የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡ • ብጉንጅ የፊት ቆዳዎ ላይ ከወጣ • ከመጠን በላይ ካበጠ ወይም በፍጥንት ከተባባሰ • ትኩሳት ካለዎ • መጠኑ ከ5 ሳንቲሜትር በላይ ከሆነ • በሁለት ሳምንት ዉስጥ የማይድን ከሆነ • ከጠፋ በኃላ ተመልሶ ከመጣ ናቸዉ፡፡

ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች ምንም እንኳ ማንኛዉም ጤነኛ የሆነ ሰዉ ብጉንጅ ሊይዘዉ ቢችልም የሚከተሉት ነገሮች ግን ይበልጥ ተጋላጭ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡ • ስታፍሎኮካል ባክቴሪያ እንፌክሽን ከያዘዉ ሰዉ ጋር የቅርብ ግንኙነት መኖር • የስኳር ህመም • የሰዉነት የበሽታ መከላከል መቀነስ ናቸዉ፡፡

የህይወት ዘይቤ ለዉጥና የቤት ዉስጥ ህክምና ትናንሽ ብጉንጆችን የሞቀ ዉሃ እላዩ ላይ በመያዝና በራሱ እንዲፈርጥ በመተዉ እራስዎ ሊያክሙትና እንዲሻሻል ማድረግ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም • የሞቀ ነገር እላዩ ላይ መያዝ • ኮንታሚኔሽንን መከላከል፡- ብጉንጁን ከነኩ በኃላ እጅዎን በደንብ መታጠብ፡፡ ብጉንጅ የነኩ ልብሶች ካለዎና ብጉንጅ በተደጋጋሚየሚያስቸግርዎ ከሆነ ልብሱን በካዉያ መተኮስ • ብጉንጁን እራስዎ ያለማፍረጥ፡- ይህን ማድረግ ብጉንጅ ሌላ ቦታ እንዲዛመትያደርጋሉና፡፡