Jump to content

ቦብ ዲለን

ከውክፔዲያ

ቦብ ዲለን (Bob Dylan) እውቅ አሜሪካዊ ዘፋኝ፣ ደራሲ እና አርቲስት ነው።

Music ሮበርት ቦብ ዳይለን የዓመቱ የኖቤል ሽልማት ተሸላሚ አቀንቃኝ


ምንጭ፡- ;ታምራት ሀይሉ/ ;ቁም ነገር መፅሔት  2009 ዓ.ም

script html bucin የዓለማችን ከፍተኛው ክብርና ዝና የሚያጎናፅፈው የኖቤል ሽልማትን ለመሸመልም የታጨውና ሽልማቱም ይገባዋል የተባለው የዛሬ 20 ዓመት ነበር፡፡ በዘንድሮው የ2016 የኖቤል ሽልማት ላይ አሜሪካዊው አቀንቃበኝና የዘፈን ግጥም ደራሲ ቦብ ዳይልንን ይሸለማል ብሎ የጠበቀ አልነበረም- ራሱም ጭምር፡፡ ግን ሆነ፡፡ የመጀመሪያው የዘፈን ግጥም ፀሐፊና አቀንቃኝ ሆኖ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆኖ ተመረጠ፡፡ የስዊዲን የስነ ፅሑፍ አካዳሚ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ የ2016 የኖቤል ሽልማት አሸናፊ የሆነውን ቦብ ዳይለንን ስም ሲጠራ ከጋዜጠኞች ግምት ውጪ ሆኖ ነበር፡፡ የአካማዳሚው ቋሚ ዋና ፀሐፊ የሆኑት ሚስስ ሳራ ዴኑስ እንዳሉት ‹ በአሜሪካ የዘፈን ድርሰት ውስጥ አዲስ የመግለፅ ብቃት ያለው ደራሲ› ሲሉ ነበር ያስተዋወቁት፡፡ የ75 ዓመቱ አንጋፋ አርቲስት ቦብ ዳይለን ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በፖፕ ሙዚቃ ውስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነ ባለሙያ ነው፡፡ የስዊዲን አካዳሚ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ‹‹ቦብ ዳይለን በስራው ተምሳሌት የሆነ ስራ የሰራ ሰው ነው፡፡ በግጥሙ ስዕል መሳል የሚችል ነው፡፡›› የአካዳሚው አባል የሆኑት ፒተር ዋትስበርግ ‹‹ቦብ ዳይለን ማለት በአሁኑ ወቅት በህይወት ያለ ባለቅኔ ነው› ታዋቂው የኒውስ ዊክ መፅሔት የቦብ ዳይለንን በየኖቤል ሽልማት ማሸነፍ ተከትሎ "The Einstein of pop music." ነው ያለው፡፡ በአሜሪካ የፖፕ ሙዚቃ ውስጥ አይረሴ የሆኑ ዜማዎችን በማቀንቀን የሚታወቀው ቦብ ዳይለን በአሜሪካውያን ዘንድ እንደ ብሔራዊ መዝሙር የሚዘፈኑ የተለያዩ ተወዳጅ ድርሰቶችን ሰርቶ በማንጎራጎር ይታወቃል፡፡ በዘፈኖቹ የተመሰጡ ሌሎች አዘቀንቃኞችም የዳይለንን ዘፈኖች በተለያዩ መድረኮች ላይ በማንጎራጎር ለዘፈኖቹ ያላቸውን አድናቆት ሲያሳዩ ተስተውሏል፡፡ ዳይለን ካቀነቀናቸውና በበርካታ አሜሪካውያን ዘንድ ከሚታወቁት ዘፈኖቹ መሀከል ‹"Blowin 'In the Wind," "The Times They Are A-Changin" and "Like a Rolling Stone." ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ቦብ ዳይለን የዘንድሮውን በሥነ ፅሑፍ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት ከማግኘቱ በፊት በርካታ ሽልማቶችንና እውቅናዎችን ተጎናፅፏል፡፡ ሁለት የክብር ዶክተሬትት ድግሪ ከሁለት የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ያገኘው ዳይለን እ.ኤ.አ በ2008 በሙዚቃ ስራዎቹ በብዙዎች ዘንድ ለፈጠረው ተፅእኖ የፑልቲዘር ሽልማትን ተቀብሏል፡፡ እ.ኤ.አ ደግሞ የአሜሪካ ከፍተኛውን ለሲቪሎች የሚሰጠውን የነፃነት መዳሊያ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ተቀብሏል፡፡ የዋንጫ ሽልማቶቹና የክብር ሰርተፍኬቶቹን ሳንቆጥር በሙዚቃውና በፊልሙ ዘርፍ የተለያዩ ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡ የ11 የግራሚ አሸናፊ፤የጎልደን ግሎብ ተሸላሚና የአካዳሚ አዋርድ አሸናፊ የሆነው ቦብ ዳይለን ለተለያዩ ፊልሞች ማጀቢያ በሰራው የሙዚቃ ስራውም ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ሜይ 24 ቀን 1941 እ.ኤ.አ የአይሁድ ዝርያ ካላቸው ቤተሰቦቹ በአሜሪካ ሜኖሶታ የተወለደው ሮበርት ቦብ ዳይለን እስከ 1950 ዎቹ አጋማሽ ድረስ በትምህርት ቤት ቆይታው የሮክ ኤንድ ሮል ሙዚቃዎችን ይጫወት ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ከግሪን ዊች ወደ ኒዩዎርክ የመኖሪያ አድራሻውን የቀየረው ዳይለን በኒዩዎርክ የምሽት ክበቦች ውስጥ በጊታሩ እየታጀበ ልዩ ልዩ ሙዚቃዎችን ያቀርብ ነበር፡፡ ዳይለን ለመጀመሪያ ጊዜ ጆአና ከምትባል ወጣት ጋር በፍቅር የወደቀው በምሽተ ክበብ ውስጥ ይሰራ በነበረበት ጊዜ ሲሆን ጆአን የፍቅር ዜማዎች በዳይለን አጃቢነት ታቀነቅን ነበር፡፡ እርሱ ግን በሚፅፋቸው ግጥሞችና በሚያቀነቅናቸው ዜማዎቹ እራሱን እንደ ፓለቲካ አቀንቃኝ ይገልፅ እንደነበር የህይወት ታሪኩ ያስረዳል፡፡ በዘፈኖቹ ይዘት ያልተደሰቱ ሰዎች ባቀነባበሩበት ክስም ወደ ማረሚያ ቤት ተወስዶ ነበር፡፡ ዳይለን ከጆአና ጋር ሆኖ ታላቁ የነፃነት ሰልፍ በተባለውና እ.ኤ.አ በ1963 በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደበት ወቅት በጋራ ባቀነቀኑበት ወቅት ታላቅ አድናቂዎት አግኝተው ነበር፡፡ የቦብ ዳይለን አልበሞች በከፍተኛ ደረጃ የሚሸጡና እስከ ቅርብ ዓመታት ድረስ የሙዚቃ ሽያጭ ሰንጠረዡ ላይ ይገኙ ነበር፡፡ ባለፉት 50 ዓመታት ተደማጭ ከነበሩት አልበሞቹ መሀከል "Rolling Stone" ranks two Dylan albums - "Blonde on Blonde" and "Highway 61 Revisited" በከፍተኛ ደረጃ ተወዳጆች ናቸው፡፡ ከ100 ሚሊዮን በላይ የአልበም ሽያጭ በማስመዝገብም ሪከርድ አስመዝግቧል፡፡ የሙዚቃ ብቻ ሳይሆን የስዕል ችሎታ ባለቤት የሆነው ዳይለን የሳላቸው ስዕሎች በታላላቅ የስዕል ማሳያ ሙዚየሞች ውስጥ ቦታ አግኝተዋል፡፡ ዳይለን እ.ኤ.አ በ1966 ከሞተር ሳይክ ላይ ወድቆ አደጋ ከደረሰበት በኋላ ለተወሰኑ ዓመታት ከሙዚቃ ስራው ራሱን አግልሎ ነበር፡፡ከመጀመሪያ ሚስቱ ሳራ ላውረንስ ጋር በመሆንም ልጆቹን በማሳደግ ነበር ጊዜውን ያሳልፍ የነበረው፡፡ ያም ሆኖ ግን ይህ ጊዜ ተወዳጅና አይረሴ ስራዎችንና ድርሰተችን እንዲፅፍ የተመስጦ ጊዜው እንደነበር የሙያ ባልደረቦቹ ይናገራሉ፡፡ የቦብ ዳይለን አስቸጋሪ ጊዜያዓት የጀመሩት በ1970ዎቹ ከባለቤቱ ጋር ተከለያየ በኋላ ነው፡፡ ሃይማኖቱን የቀየረው ዳይለን ሁለት መንፈሳዊ አልበሞችን አሳትሟል፡፡ ሀይማኖታዊ የመዝሙር ስልቱንም በአር ኤንድቢ በመጫወት ለመንፈሳዊ ሙዚቃ የራሱን አስተዋፅኦ ማበርከቱን ብዙዎች ያምናሉ፡፡ ያም ሆኖ ግን ከትዳር ፍችው ጋር በተያያ ዘ የአልኮል ሱሰኛ ሆኖ ነበር፡፡ በሙዚቃ ስራው አድናቂዎችን ለጥቂት ዓመታት ለማስደሰት ባይችልም ራሱን ከሙዚቃ ስራ ለማግለል ግን ሳይችል ቀርቷል፡፡ ጊታር፤ሐርሞኒካና ኪ ቦርድ የሚጫወተው ቦብ ዳይለን ለዜማ ፈጠራውም እነዚህኑ መሳሪያዎች እንደሚጠቀም ይታወቃል፡፡ የአምስት ልጆች አባት የሆነው ዳይለን ማሪያ የተባለች ልጅንም በጉዲፈቻ ያሳድጋል፡፡ በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይም ሁለተኛ ሚስት አግብቶ ሙሉ ጊዜውን ለሙዚቃ ስራ የሰጠው ቦብ ዳይለን በተከታታይ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን በተለያዩ ከተሞች በማካሄድ የቀድሞ ዝናውን ለመመለስ ችሏል፡፡ "Never Ending Tour," የሚል ስያሜ ያለው 100 ኮንሰርቶችን በማካሄድም አድናቆትን አግኝቷል፡፡ ምንጭ፡- ቁም ነገር መፅሔት 2009 ዓ.ም


› Music ሮበርት ቦብ ዳይለን የዓመቱ የኖቤል ሽልማት ተሸላሚ አቀንቃኝ


Music

ሮበርት ቦብ ዳይለን የዓመቱ  የኖቤል ሽልማት ተሸላሚ አቀንቃኝ

የዓለማችን ከፍተኛው ክብርና ዝና የሚያጎናፅፈው የኖቤል ሽልማትን ለመሸመልም የታጨውና ሽልማቱም ይገባዋል የተባለው የዛሬ 20 ዓመት ነበር፡፡ በዘንድሮው የ2016 የኖቤል ሽልማት ላይ አሜሪካዊው አቀንቃበኝና የዘፈን ግጥም ደራሲ ቦብ ዳይልንን ይሸለማል ብሎ የጠበቀ አልነበረም- ራሱም ጭምር፡፡ ግን ሆነ፡፡ የመጀመሪያው የዘፈን ግጥም ፀሐፊና አቀንቃኝ ሆኖ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆኖ ተመረጠ፡፡

የስዊዲን የስነ ፅሑፍ አካዳሚ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ የ2016 የኖቤል ሽልማት አሸናፊ የሆነውን ቦብ ዳይለንን ስም ሲጠራ  ከጋዜጠኞች ግምት ውጪ ሆኖ ነበር፡፡ የአካማዳሚው ቋሚ ዋና ፀሐፊ  የሆኑት ሚስስ ሳራ ዴኑስ እንዳሉት ‹ በአሜሪካ የዘፈን ድርሰት ውስጥ አዲስ የመግለፅ ብቃት ያለው ደራሲ› ሲሉ ነበር ያስተዋወቁት፡፡

የ75 ዓመቱ አንጋፋ አርቲስት ቦብ ዳይለን ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በፖፕ ሙዚቃ ውስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነ ባለሙያ ነው፡፡  የስዊዲን አካዳሚ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ‹‹ቦብ ዳይለን በስራው ተምሳሌት የሆነ ስራ የሰራ ሰው ነው፡፡ በግጥሙ ስዕል መሳል የሚችል ነው፡፡›› የአካዳሚው አባል የሆኑት ፒተር ዋትስበርግ ‹‹ቦብ ዳይለን ማለት በአሁኑ ወቅት በህይወት ያለ ባለቅኔ ነው› ታዋቂው የኒውስ ዊክ መፅሔት የቦብ ዳይለንን በየኖቤል ሽልማት ማሸነፍ ተከትሎ "The Einstein of pop music." ነው ያለው፡፡

በአሜሪካ የፖፕ ሙዚቃ ውስጥ አይረሴ የሆኑ ዜማዎችን በማቀንቀን የሚታወቀው ቦብ ዳይለን በአሜሪካውያን ዘንድ እንደ ብሔራዊ መዝሙር የሚዘፈኑ የተለያዩ ተወዳጅ ድርሰቶችን ሰርቶ በማንጎራጎር ይታወቃል፡፡ በዘፈኖቹ የተመሰጡ ሌሎች አዘቀንቃኞችም የዳይለንን ዘፈኖች በተለያዩ መድረኮች ላይ በማንጎራጎር ለዘፈኖቹ ያላቸውን አድናቆት ሲያሳዩ ተስተውሏል፡፡ ዳይለን ካቀነቀናቸውና በበርካታ አሜሪካውያን ዘንድ ከሚታወቁት ዘፈኖቹ መሀከል ‹"Blowin 'In the Wind," "The Times They Are A-Changin" and "Like a Rolling Stone." ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ቦብ ዳይለን የዘንድሮውን በሥነ ፅሑፍ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት ከማግኘቱ በፊት በርካታ ሽልማቶችንና እውቅናዎችን ተጎናፅፏል፡፡  ሁለት የክብር ዶክተሬትት ድግሪ ከሁለት የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ያገኘው ዳይለን እ.ኤ.አ በ2008  በሙዚቃ ስራዎቹ  በብዙዎች ዘንድ ለፈጠረው  ተፅእኖ የፑልቲዘር ሽልማትን ተቀብሏል፡፡ እ.ኤ.አ ደግሞ የአሜሪካ ከፍተኛውን ለሲቪሎች የሚሰጠውን የነፃነት መዳሊያ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ተቀብሏል፡፡ የዋንጫ ሽልማቶቹና የክብር ሰርተፍኬቶቹን ሳንቆጥር በሙዚቃውና በፊልሙ ዘርፍ  የተለያዩ ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡ የ11 የግራሚ አሸናፊ፤የጎልደን ግሎብ ተሸላሚና የአካዳሚ አዋርድ አሸናፊ የሆነው ቦብ ዳይለን ለተለያዩ ፊልሞች ማጀቢያ በሰራው የሙዚቃ ስራውም ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ሜይ 24 ቀን 1941 እ.ኤ.አ  የአይሁድ ዝርያ ካላቸው ቤተሰቦቹ በአሜሪካ ሜኖሶታ የተወለደው ሮበርት ቦብ ዳይለን እስከ 1950 ዎቹ አጋማሽ ድረስ በትምህርት ቤት ቆይታው የሮክ ኤንድ ሮል ሙዚቃዎችን ይጫወት ነበር፡፡  እ.ኤ.አ ከግሪን ዊች ወደ ኒዩዎርክ የመኖሪያ አድራሻውን የቀየረው ዳይለን በኒዩዎርክ የምሽት ክበቦች ውስጥ በጊታሩ እየታጀበ ልዩ ልዩ ሙዚቃዎችን ያቀርብ ነበር፡፡ ዳይለን ለመጀመሪያ ጊዜ  ጆአና ከምትባል ወጣት ጋር በፍቅር የወደቀው በምሽተ ክበብ ውስጥ ይሰራ በነበረበት ጊዜ ሲሆን ጆአን የፍቅር ዜማዎች በዳይለን አጃቢነት ታቀነቅን ነበር፡፡ እርሱ ግን በሚፅፋቸው ግጥሞችና በሚያቀነቅናቸው ዜማዎቹ  እራሱን እንደ ፓለቲካ አቀንቃኝ ይገልፅ እንደነበር የህይወት ታሪኩ ያስረዳል፡፡ በዘፈኖቹ ይዘት ያልተደሰቱ ሰዎች ባቀነባበሩበት ክስም ወደ ማረሚያ ቤት ተወስዶ ነበር፡፡ ዳይለን ከጆአና ጋር ሆኖ ታላቁ የነፃነት ሰልፍ በተባለውና እ.ኤ.አ በ1963 በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደበት ወቅት በጋራ ባቀነቀኑበት ወቅት ታላቅ አድናቂዎት አግኝተው ነበር፡፡

የቦብ ዳይለን አልበሞች በከፍተኛ ደረጃ የሚሸጡና እስከ ቅርብ ዓመታት ድረስ የሙዚቃ ሽያጭ ሰንጠረዡ ላይ ይገኙ ነበር፡፡  ባለፉት 50 ዓመታት ተደማጭ ከነበሩት አልበሞቹ መሀከል "Rolling Stone" ranks two Dylan albums - "Blonde on Blonde" and "Highway 61 Revisited"  በከፍተኛ ደረጃ ተወዳጆች ናቸው፡፡ ከ100 ሚሊዮን በላይ የአልበም ሽያጭ በማስመዝገብም ሪከርድ አስመዝግቧል፡፡ የሙዚቃ ብቻ ሳይሆን የስዕል ችሎታ ባለቤት የሆነው ዳይለን የሳላቸው ስዕሎች በታላላቅ የስዕል ማሳያ ሙዚየሞች ውስጥ ቦታ አግኝተዋል፡፡

ዳይለን እ.ኤ.አ በ1966 ከሞተር ሳይክ ላይ ወድቆ አደጋ ከደረሰበት በኋላ ለተወሰኑ ዓመታት ከሙዚቃ ስራው ራሱን አግልሎ ነበር፡፡ከመጀመሪያ ሚስቱ ሳራ ላውረንስ ጋር በመሆንም ልጆቹን በማሳደግ ነበር ጊዜውን ያሳልፍ የነበረው፡፡ ያም ሆኖ ግን ይህ ጊዜ ተወዳጅና አይረሴ ስራዎችንና ድርሰተችን እንዲፅፍ የተመስጦ ጊዜው እንደነበር የሙያ ባልደረቦቹ ይናገራሉ፡፡ የቦብ ዳይለን አስቸጋሪ ጊዜያዓት የጀመሩት በ1970ዎቹ ከባለቤቱ ጋር ተከለያየ በኋላ ነው፡፡ ሃይማኖቱን የቀየረው ዳይለን  ሁለት መንፈሳዊ አልበሞችን አሳትሟል፡፡ ሀይማኖታዊ የመዝሙር ስልቱንም በአር ኤንድቢ በመጫወት ለመንፈሳዊ ሙዚቃ የራሱን አስተዋፅኦ ማበርከቱን ብዙዎች ያምናሉ፡፡ ያም ሆኖ ግን ከትዳር ፍችው ጋር በተያያ ዘ የአልኮል ሱሰኛ ሆኖ ነበር፡፡ በሙዚቃ ስራው አድናቂዎችን ለጥቂት ዓመታት ለማስደሰት ባይችልም ራሱን ከሙዚቃ ስራ ለማግለል ግን ሳይችል ቀርቷል፡፡ ጊታር፤ሐርሞኒካና ኪ ቦርድ የሚጫወተው ቦብ ዳይለን ለዜማ ፈጠራውም እነዚህኑ መሳሪያዎች እንደሚጠቀም ይታወቃል፡፡ የአምስት ልጆች አባት የሆነው ዳይለን ማሪያ የተባለች ልጅንም በጉዲፈቻ ያሳድጋል፡፡

በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይም ሁለተኛ ሚስት አግብቶ ሙሉ ጊዜውን ለሙዚቃ ስራ የሰጠው ቦብ ዳይለን በተከታታይ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን በተለያዩ ከተሞች በማካሄድ የቀድሞ ዝናውን ለመመለስ ችሏል፡፡ "Never Ending Tour,"  የሚል ስያሜ ያለው  100 ኮንሰርቶችን በማካሄድም  አድናቆትን አግኝቷል፡፡

ምንጭ፡- ;ታምራት ሀይሉ/ ;ቁም ነገር መፅሔት  2009 ዓ.ም